2022-07-11 10:07:54
«አላህ አደምን በመልኩ ፈጠረው»
ነቢዩ (ዐሰወ) ስለ አደም አፈጣጠር ሲናገሩ እንዲህ አሉ፦
«አላህ አደምን በራሱ መልክ ፈጠረው። ቁመቱም ስድሳ ክንድ ነው።»
(ቡኻሪይ 6227)
በሌላ ሐዲስ ደግሞ እንዲህ አሉ፦
«ከወንድሙ ጋር የተጣላ ሰው ፊቱን አይምታው። አላህ አደምን በመልኩ ፈጥሮታልና።
(ሙስሊም 2612)
በሁለቱም ሰሂህ ሐዲሶች ላይ የተጠቀሰው የአረቢኛ ቃል «ሱራህ» ሲሆን ትርጉሙም መልክ ማለት ነው።
ኢብን ተይሚያህ ሐዲሱን ሲያብራሩ እንዲህ ይላሉ፦
«በዚህ ሐዲስ ሱራህ ተብሎ የተገለፀው ቃል እንደ ሌሎቹ የአላህ ባህርያት ከፍጡራን ጋር በስም ብቻ የሚመሳሰል ነው።
አላህ አዋቂ ነው፣ ሰሚ ነው፣ ተመልካች ነው፣ ፊት አለው፣ እጅ አለው፣ እግር አለው፣ ከአርሹ በላይ ነው ሲባል ከፍጡራን ጋር ከስም የዘለለ ይመሳሰላል ማለት አይደለም።
ማንኛውም ህልውና ያለው አካልም መገለጫ መልክ ወይም ገፅታ አለው። መልክ ወይም ገፅታ የሌለውን ነገርም አልለ ማለት አንችልም።
ይህ ሐዲስም በተለያዩ ሰሃባዎች የተላለፈና በቀደምት ሰለፎች ምንም ጥያቄ ያላስነሳ ነው።
ነገርግን በ300 ሒጅራ በኋላ የተነሱት ጀህሚያዎች ቃሉ አላህን ከፍጡራን ጋር ያመሳስላል በማለት የተሳሳተ ትርጓሜ ውስጥ ገቡ።»
(ነቅድ አል-ተዕሲስ 3/282,396)
ኢብን ቀይምም እንዲህ ብለዋል፦
«የአላህ መልክ መኖር ከሁለት እጆቹ ከጣቶቹ ወይም ከዓይኖቹ የተለየ እንግዳ ነገር አይደለም። የሚለየው መልክ የሚለው ቃል በቁርአን አለመጠቀሱ ብቻ ነው። ነገርግን በተረጋገጠ ሐዲስ የመጣ ስለሆነ እንዴት የሚል ጥያቄ ሳናነሳ እንቀበለዋለን።»
(ተዕዊል ሙኽተሊፍ አል-ሐዲስ 221)
ኢብን ባዝም ስለ ሐዲሱ ተጠይቀው እንዲህ አሉ፦
«ዑለማዎች እንደፈሰሩት አላህ አደምን የማየት የመስማት የመናገር ችሎታን ሰጥቶታል። እነዚህ ባህሪያት ደግሞ የአላህም ናቸው። ነገርግን የአላህ ባህሪያት ፍፁማዊ ሲሆን የፍጡራን ግን የተገደበ ነው።»
(መጅሙዕ አል-ፈትዋ ኢብን ባዝ 4/226)
ኢብን ዑሰይሚንም እንዲህ ብለዋል፦
«አላህ አደምን በመልኩ ፈጠረው ማለት ከእሱ ጋር በስም የሚመሳሰል ባህሪያትን ሰጥቶታል ማለት እንጅ አምሳያው ነው ለማለት አይደለም። ለምሳሌ ጀነት የሚገቡት የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ሙሉ ጨረቃን ይመስላሉ ተብሏል። ነገርግን በመልክ አንድ ናቸው ማለትን አያስይዝም።»
(ሸርህ አል-አቂዳል አል-ወሰጢያህ 1/107)
ሰል ማን
https://t.me/fethmedia
https://t.me/fethmedia
https://t.me/fethmedia
70 views07:07