Get Mystery Box with random crypto!

💫ፈዕለም የቁርአን ማእከል💫

የቴሌግራም ቻናል አርማ fe_ilmquran — 💫ፈዕለም የቁርአን ማእከል💫
የቴሌግራም ቻናል አርማ fe_ilmquran — 💫ፈዕለም የቁርአን ማእከል💫
የሰርጥ አድራሻ: @fe_ilmquran
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 258
የሰርጥ መግለጫ

''ቁርአን ከ አሊፉ ጀምረዉ ይማሩ''

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-05-15 08:03:47 *የዱንያ ነገር!!*
~~~
ዐልይ ኢብኑል ሀይሠም እንዲህ ይላሉ:–
"አምሳያ ያላየሁለት የዘመን መገለባበጥ፣ የጊዜ መለዋወጥ አይቻለሁ።
★ የአልፈድል ኢብኑ ረቢዕ ንብረት በአንድ ሺህ ግመል ተጭኖ አይቻለሁ። ሌላ ጊዜ ግን ጠቅላላ ንብረቱ አንዲት ዘንቢል ውስጥ ሆና ተደብቄ አይቻለሁ። በውስጧ መድሃኒቶቹ ተጨምረው።

★ አልሐሰን ኢብኑ ሰህልን ደግሞ ጠቅላላ ንብረቱ አንዲት ዘንቢል ውስጥ ሆና ተመልክቻለሁ። ከዚያ ግን ንብረቱ በአንድ ሺ ግመል ላይ ተጭኖ አይቼዋለሁ።"

||

ዱንያ እንዲህ ነች። መርጋት የማታውቅ ወላዋይ!!
ሃያላን ይዋረዳሉ። ደካሞች ይነግሳሉ።
ሀብታሞች ጎዳና ላይ ይወድቃሉ። ምንዱባን በሰማይ ጠቀስ ህንፃ ይንፈላሰሳሉ።
ሳር ቅጠሉን የተፀየፈው ጨፍጫፊ አረመኔ አለም ጠባው ከአይጥ ጎሬ ሲያደፍጥ ታየዋለህ። የትላንቱ ተሳዳጅ ተራውን ሲያሳድድ ትመለከታለህ።

ይሄው ነች ዱንያ!! ብልጭ ብላ ድርግም፣ ቦግ ብላ እልም የምትል። ሁሌ ሳቅ የለም! ሁሌ ድል የለም።
|
በድር ላይ ለያዥ ለገናዥ ያስቸገሩ፣ ጥጋብ ያስከራቸው ቁረይሾች፣ 70 መኳንንቶቻቸው ትላንት ሲያሳድዷቸው በነበሩ ሶሐቦች ሰይፍ ተበልተው፣ ሌላ 70 ደግሞ በምርኮ አስረክበው የሐዘን ማቅ ለብሰዋል። መካ በዋይታ ተንጣለች።
|
ኡሑድ ሌላ ቀን ነው። ሌላ ተራ!! አጋሪዎች የፈነደቁበት፣ እነ ሐምዛን፣ እነ ሙስዐብን ጨምሮ ከ70 በላይ ታላላቅ ጀግኖች ወድቀው ሌላ 70 የቆሰሉበት፣ አሳዝኝ ክስተት እውን የሆነበት ቀን። ሶሐቦች አካላቸው በስለት፣ ልባቸው በሐዘን ቢቆስል ጊዜ አላህ እንዲህ ሲል አሳሰባቸው: –

(إِنْ يَمْسَسْكُمْ قَرْحٌ فَقَدْ مَسَّ الْقَوْمَ قَرْحٌ مِثْلُهُ ۚ وَتِلْكَ الْأَيَّامُ نُدَاوِلُهَا بَيْنَ النَّاسَ)

"ቁስል ቢያገኛችሁ ሰዎቹንም መሰሉ ቁስል አግኝቷቸዋል፡፡ እናም እነዚህን ቀናት በሰዎች መካከል (በመልካምና በሌላ) እናቀያይራቸዋለን፡፡" [ኣሉ ዒምራን: 140]

|||

ዱንያ አመሏ ነው። ዛሬም እንዲሁ ናት።
ግን ማነው የሚማረው? ግን ማነው የሚመረምረው? ግን ማነው የዱንያን ከንቱነት ተገንዝቦ ለዘላለም ቤቱ ከልብ የሚጨነቀው?
እስከ መቼ ነው የምናንቀላፋው?
እስከ መቼ ነው የምንዘናጋው?
እስከ መቼ ነው በከንቱ የምንባዝነው?
ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን!!
ኢላሂ ልብ ስጠን!!
—————————-
የቴሌግራም አድራሻ
https://t.me/IbnuMunewor
480 views05:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-10 05:25:20 ⇘ፉዶይል ዒብኑ ዒያድ ( አላህ ይዘንላቸው)ሁለት ልዩ ነገሮች ልብን
ያደርቃሉ፡–


"ምግብ ማብዛትና ንግግር ( ወሬ) ማብዛት"
ﻗﺎﻝ ﺍﻟﻔﻀﻴﻞ ﺑﻦ ﻋﻴﺎﺽ ﺭﺣﻤﻪ ﺍﻟﻠﻪ : ﺍﻟﻌﺠﺐ ﻛﻞ ﺍﻟﻌﺠﺐ ﻟﻤﻦ ﻋﺮﻑ ﺍﻟﻠﻪ ﺛﻢ
ﻋﺼﺎﻩ ﺑﻌﺪ ﺍﻟﻤﻌﺮﻓﺔ .
⇘ፉደይል ኢብኑ ኢያድ ይላሉ፡–" በጣም የሚገርመኝ አላህን ያወቀ
ሰው ከዚያም ካወቀው በኋላ ያመፀው ነው"።
ﻗﺎﻝ ﺍﻟﻔﻀﻴﻞ ﺑﻦ ﻋﻴﺎﺽ ﺭﺣﻤﻪ ﺍﻟﻠﻪ:
ﺫﻛﺮ ﺍﻟﻨﺎﺱ ﺩﺍﺀ، ﻭﺫﻛﺮ ﺍﻟﻠﻪ ﺷﻔﺎﺀ .
⇘ፉደይል ኢብኑ ኢያድ ይላሉ፡– ሰወችን ማውሣት በሽታ ሲሆን አላህን
ማውሣት ግን መድሀኒት ነው።
https://t.me/fe_ilmquran

https://t.me/fe_ilmquran
384 views02:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-03 08:48:06 ‍ ‍ ስድስቱ የሸዋል ቀናት

قـَالَ العَلّامَة صَالِح الفَوْزَان -حَفِظَهُ الله

«ﻭﻣﻦ ﻋﻼﻣﺎﺕِ ﺍﻟﻘﺒﻮﻝِ ﻓﻲ ﺭﻣﻀﺎﻥَ ﻭﻓﻲ ﻏﻴﺮﻩ ﺍﺗﺒﺎﻉُ ﺍﻟﺤﺴﻨﺔِ ﺑﺎﻟﺤﺴﻨﺔ ﻓﺈﺫﺍ ﻛﺎﻧﺖ ﺣﺎﻟﺔُ ﺍﻟﻤﺴﻠﻢِ ﺑﻌﺪَ ﺭﻣﻀﺎﻥَ ﺣﺎﻟﺔً ﻃﻴﺒﺔً، ﻳﻜﺜﺮُ ﻣﻦ ﺍﻟﺤﺴﻨﺎتِ وﺍﻷﻋﻤﺎﻝِ ﺍﻟﺼﺎﻟﺤﺔ ﻓﻬﺬﺍ ﺩﻟﻴﻞٌ ﻋﻠﻰ ﺍﻟﻘﺒﻮﻝ،

የረመዷን ተቀባይነቱ ምልክቱ ፣በሌላ ጊዜ መልካምን ነገር በመልካም ማስከተሉ ነው። የሙስሊም ሁኔታው ከረመዷን በሇላ ጥሩ የሆነች ጊዜና ጥሩ ነገሮች፣ ከመልካም ስራዎች የሚያበዛ ከሆነ ይህ ለተቀባይነቱ አመላካች ነው።

ﺃﻣَّﺎ ﺇﻥ ﻛﺎﻥ ﺍﻟﻌﻜﺲ، ﻳﺘﺒﻊ ﺍﻟﺤﺴﻨﺎﺕِ ﺍﻟﺴﻴﺌﺎﺕِ، ﻓﺈﺫﺍ ﺧﺮﺝَ ﺭﻣﻀﺎﻥ ﺃﺗﺒﻌﻪ ﺑﺎﻟﺴﻴﺌﺎﺕِ ﻭﺍﻟﻐﻔﻼﺕِ ﻭﺍﻹﻋﺮﺍﺽ ﻋﻦ ﻃﺎﻋﺔِ ﺍﻟﻠﻪ ﻓﻬﺬﺍ ﺩﻟﻴﻞٌ ﻋﻠﻰ ﻋﺪﻡ ﺍﻟﻘﺒﻮﻝ
[ﻣﺠﺎﻟﺲ ﺷﻬﺮ ﺭﻣﻀﺎﻥ ❪١١٩❫ ]

በተቃራኒው ከሆነማ ረመዷን ወጣ ጊዜ ጥሩን ነገር መጥፎን የሚያስከትልበት፣ በዝንጋቴዎች ፣አላህን ከመታዘዝ በመሸሽ (የሚያስከትለው ከሆነ) ይህ ተቀባይነቱን ማጣቱን አመላካች ነው።»

قال الشيخ صالح الفوزان حفظه الله أيضا: -
« لئن انتهى شهر رمضان فإن حق الله لا ينتهي إلا بالموت»

«የረመዳን ወር ቢያልቅ የአሏህ ሐቅ አያልቅም በሞት እንጂ።»

قال الله تعالى: {وَاعْبُدْ رَبَّكَ حَتَّىٰ يَأْتِيَكَ الْيَقِينُ} [الحجر : 99]

عن أبي أيُّوب الأنصاري رضي الله عنه أن رسول الله ﷺ قال: ((مَن صام رمضان ثم أتبَعَه ستًّا من شوَّال، كان كصيام الدهر)) رواه مسلم

“ረመዳንን ፆሞ ከሸዋል ስድስት ቀን ያስከተለ ልክ አመት እንደፆመ ነው፡፡”

أن الحسنة تضاعف بعشر أمثالها

አንድ ሐሰና በአስር ይባዛል።

قال تعالى፡ ﴿من جاء بالحسنة فله عشر أمثالها﴾

"በመልካም ስራ የመጣ ሰው ለእርሱ አስር ብጤዎቿ አሉት፡፡"

ስለዚህ 30 የረመዳን ቀናት + 6 የሸዋል ቀናት = 36 ቀናት

36 x 10 = 360 ቀናት
360 ቀናት ማለት ደግሞ 1 አመት ሙሉ ማለት ነው።

የሸዋል ስድስቱን ቀናት ከዒድ አልፊጥር በኋላ አስከትሎ መፆሙ በላጭ ቢሆንም እስከ ወሩ መጨረሻ ድረስ መፆም ይቻላል የረመዳን ቀዳ ካለብን ቶሎ ቀዷውን ከፆምን በኃላ።

ቀዷ ወይም ከረመዳን የተወሰኑ ቀናት ያሉበት ሰው ቅድሚያ ረመዳንን ሊሞላው ይገባል ለምን ከተባለ የአንድ አመት ፆም ምንዳ ለማግኘት አጅሩን እንደሚያገኝ ቃል የተገባለት ረመዳንን ካሟላ በኋላ የፆመው ሰው ስለሆነ፤ ቅድሚያ ረመዳንን መፆም አለበት ስለዚህም በተቻለን መጠን ከሸዋል ሱና በፊት የረመዳንን ቀዷ ለማጠናቀቅ መሞከር ይኖርብናል።

نسأل الله تعالى أن يوفقنا لما يحب ويرضى
https://t.me/fe_ilmquran
486 views05:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-01 22:25:01 ኢድ ሙባረክ!

እንኳን አደረሳችሁ!

አላህ መልካም ስራችንን ይቀበለን። መልካም በዓል ይሁንላችሁ።

ፈዕለም የቁርኣን ንባብና የተጅዊድ ማዕከል
175 views19:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-30 19:00:46 . ሰበር

ሳዑድ ዐረቢያ የሸዋል ጨረቃ ባለመታየቷ ነገ ረመዷን 30 ሲሆን ዒድ አል-ፊጥር ሚያዚያ 24 ሰኞ እለት ይሆናል።
366 views16:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-29 06:17:39 اللهم أعز الإسلام والمسلمين وأذل الشرك والمشركين ودمر أعداءك من مجرمي غوندر أعداء الدين يا رب العالمين
الدعاء سلاح المؤمن لا تستهينوا بالدعاء إخواننا
199 views03:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-24 22:12:09 ለይለተልቀድር በአይን ትታያለች

አንዳንዶች እግራቸውን ዘርግተው ወሬያቸውን እየፈጩ ሰማይ ሰማይ ያንጋጥጣሉ፡፡ የሚጠባበቁት ተወርዋሪ ኮከብ ነው፡፡ እሱን ሲያልፍ ሲመለከቱ “አኑረን አክብረን” ብለው በህብረት ይንጫጫሉ፡፡ ይሄ እዚህ ግባ የማይባል ባዶ እምነት ነው፡፡ ለይለተልቀድር አላህ በአንዳንድ ባሮቹ ቀልብ ላይ ከወትሮው ለየት ባለ መልኩ የመረጋጋት ወይም የመለየት ስሜት ከማሳደሩ ውጭ በአይን የሚታይ ነገር አይደለም፡፡ የሚታየው ምልክቶቿ እንጂ እራሷ አይደለችም።

ነገር ግን ሰዎች ሊጠመዱ የሚገባቸውም በዒባዳ፣ በዚክር፣ በሶላት፣ በዱዓእ፣ በቁርኣን እንጂ በወሬ መሆን የለበትም፡፡ ሰዎች የሚጠበቅባቸውን ከተወጡ ለሊቱ ለይለተልቀድር መሆኑን ባያውቁ እንኳን ትሩፋቷን አያጡም፡፡

ለይለተልቀድር እንደሆነ ውስጡ ያደረ ሰው ምን ያድርግ?

በተለይ ደግሞ ለሊቱ ለይለተልቀድር እንደሚሆን ውስጣችንን ከተሰማን ይበልጥ ልናተኩርበት የሚገባን ዱዓእ “አልሏሁመ ኢንነከ ዐፉውዉን ቱሒቡልዐፍወ ፈዕፉ ዐኒ” (“ጌታዬ ሆይ! አንተ በርግጥም ይቅር ባይ ነህ፡፡ ይቅር ማለትን ትወዳለህ፡፡ ስለሆነም ከኔ ይቅር በለኝ” የሚለው ነው።
[አልባኒ ሶሒሕ ብለውታል]

ስለዚህ ዋናው ልናተኩርበት የሚገባን በዱንያም በአኺራም ከአላህ ይቅርታን እንድናገኝ መጣጣር ነው፡፡

ግን ለምን አላህ ለይለተልቀድርን ስውር አደረጋት?

ዑለማዎች እንደሚሉት ታላላቅ ትሩፋቶች በሚገኝባቸው የረመዳን የመጨረሻ ለሊቶች ሙስሊሞች በዒባዳህ ይበራቱና ይጠናከሩ ዘንድ ነው አላህ ይቺን ለሊት ስውር ያደረጋት፡፡ እናም ለይለተልቀድርን እንዳታመልጣቸው ሲጣጣሩ ለይተው ቢያውቋት ሊኖራቸው ከሚገባው በበለጠ ይበልጥ በዒባዳህ ላይ ይቆያሉ፣ ይነቃቃሉም፡፡ በዚህም ይበልጥ ይጠቀማሉ፡፡ ለይተው ቢያውቋት ግን እሷ ብቻ ላይ አነጣጥረው ሌሎቹን ለሊቶች ሊዘናጉ ይችሉ ነበር፡፡ እናም መሰወሯ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዳሉት ለኛ ኸይር ነው፡፡ [ቡኻሪ]

አላህ ይቺን ታላቅ ለሊት ያድለን፡፡ የምንጠቀምባትም ያድርገን፡፡ ኣሚን፡፡
መልካም ሆኖ ካገኙት ሼር ማድረግ እንዳይረሱ፡፡ ሌሎችንም ተጠቃሚ ያድርጉ፡፡

(ኢብኑ ሙነወር...ሰኔ 29/2007

@IbnuMunewor
633 views19:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-24 22:09:36 አላህ ሆይ ... !

ተፈቃሪው ወርህ እየሮጠ ነው ፣ ከሱ እኩል መሮጥ አልቻልንምና አንተው አግዘን !!
ወደ ፍቅርህ ሳበን ፣ ውዴታህን ቸረን !!

https://t.me/fe_ilmquran
389 views19:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-27 12:17:47 ~ «ታላላቅ ሰዎች ራሳቸውን ፍጹም ከፍ አድርገው አያውቁም፡፡

~ ራሳቸውን ከመጠን በላይ ከፍ አድርገው የሚያዩ ሰዎች ለአላህ ክብር አላቸው ብለህ አትጠብቅ፡፡

~ ታላቅነት ከቅልጥፍናና ከአፈ ጮሌነት ጋር ብቻ አይገናኝም፡፡

~ ለራስ ከሚሰጥ ክብርና ውዳሴም ክብር አይመነጭም»

(የሰዓድ ጥበቦች)

https://t.me/fe_ilmquran
501 viewsedited  09:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ