Get Mystery Box with random crypto!

‍ ‍ ስድስቱ የሸዋል ቀናት قـَالَ العَلّامَة صَالِح الفَوْزَان - | 💫ፈዕለም የቁርአን ማእከል💫

‍ ‍ ስድስቱ የሸዋል ቀናት

قـَالَ العَلّامَة صَالِح الفَوْزَان -حَفِظَهُ الله

«ﻭﻣﻦ ﻋﻼﻣﺎﺕِ ﺍﻟﻘﺒﻮﻝِ ﻓﻲ ﺭﻣﻀﺎﻥَ ﻭﻓﻲ ﻏﻴﺮﻩ ﺍﺗﺒﺎﻉُ ﺍﻟﺤﺴﻨﺔِ ﺑﺎﻟﺤﺴﻨﺔ ﻓﺈﺫﺍ ﻛﺎﻧﺖ ﺣﺎﻟﺔُ ﺍﻟﻤﺴﻠﻢِ ﺑﻌﺪَ ﺭﻣﻀﺎﻥَ ﺣﺎﻟﺔً ﻃﻴﺒﺔً، ﻳﻜﺜﺮُ ﻣﻦ ﺍﻟﺤﺴﻨﺎتِ وﺍﻷﻋﻤﺎﻝِ ﺍﻟﺼﺎﻟﺤﺔ ﻓﻬﺬﺍ ﺩﻟﻴﻞٌ ﻋﻠﻰ ﺍﻟﻘﺒﻮﻝ،

የረመዷን ተቀባይነቱ ምልክቱ ፣በሌላ ጊዜ መልካምን ነገር በመልካም ማስከተሉ ነው። የሙስሊም ሁኔታው ከረመዷን በሇላ ጥሩ የሆነች ጊዜና ጥሩ ነገሮች፣ ከመልካም ስራዎች የሚያበዛ ከሆነ ይህ ለተቀባይነቱ አመላካች ነው።

ﺃﻣَّﺎ ﺇﻥ ﻛﺎﻥ ﺍﻟﻌﻜﺲ، ﻳﺘﺒﻊ ﺍﻟﺤﺴﻨﺎﺕِ ﺍﻟﺴﻴﺌﺎﺕِ، ﻓﺈﺫﺍ ﺧﺮﺝَ ﺭﻣﻀﺎﻥ ﺃﺗﺒﻌﻪ ﺑﺎﻟﺴﻴﺌﺎﺕِ ﻭﺍﻟﻐﻔﻼﺕِ ﻭﺍﻹﻋﺮﺍﺽ ﻋﻦ ﻃﺎﻋﺔِ ﺍﻟﻠﻪ ﻓﻬﺬﺍ ﺩﻟﻴﻞٌ ﻋﻠﻰ ﻋﺪﻡ ﺍﻟﻘﺒﻮﻝ
[ﻣﺠﺎﻟﺲ ﺷﻬﺮ ﺭﻣﻀﺎﻥ ❪١١٩❫ ]

በተቃራኒው ከሆነማ ረመዷን ወጣ ጊዜ ጥሩን ነገር መጥፎን የሚያስከትልበት፣ በዝንጋቴዎች ፣አላህን ከመታዘዝ በመሸሽ (የሚያስከትለው ከሆነ) ይህ ተቀባይነቱን ማጣቱን አመላካች ነው።»

قال الشيخ صالح الفوزان حفظه الله أيضا: -
« لئن انتهى شهر رمضان فإن حق الله لا ينتهي إلا بالموت»

«የረመዳን ወር ቢያልቅ የአሏህ ሐቅ አያልቅም በሞት እንጂ።»

قال الله تعالى: {وَاعْبُدْ رَبَّكَ حَتَّىٰ يَأْتِيَكَ الْيَقِينُ} [الحجر : 99]

عن أبي أيُّوب الأنصاري رضي الله عنه أن رسول الله ﷺ قال: ((مَن صام رمضان ثم أتبَعَه ستًّا من شوَّال، كان كصيام الدهر)) رواه مسلم

“ረመዳንን ፆሞ ከሸዋል ስድስት ቀን ያስከተለ ልክ አመት እንደፆመ ነው፡፡”

أن الحسنة تضاعف بعشر أمثالها

አንድ ሐሰና በአስር ይባዛል።

قال تعالى፡ ﴿من جاء بالحسنة فله عشر أمثالها﴾

"በመልካም ስራ የመጣ ሰው ለእርሱ አስር ብጤዎቿ አሉት፡፡"

ስለዚህ 30 የረመዳን ቀናት + 6 የሸዋል ቀናት = 36 ቀናት

36 x 10 = 360 ቀናት
360 ቀናት ማለት ደግሞ 1 አመት ሙሉ ማለት ነው።

የሸዋል ስድስቱን ቀናት ከዒድ አልፊጥር በኋላ አስከትሎ መፆሙ በላጭ ቢሆንም እስከ ወሩ መጨረሻ ድረስ መፆም ይቻላል የረመዳን ቀዳ ካለብን ቶሎ ቀዷውን ከፆምን በኃላ።

ቀዷ ወይም ከረመዳን የተወሰኑ ቀናት ያሉበት ሰው ቅድሚያ ረመዳንን ሊሞላው ይገባል ለምን ከተባለ የአንድ አመት ፆም ምንዳ ለማግኘት አጅሩን እንደሚያገኝ ቃል የተገባለት ረመዳንን ካሟላ በኋላ የፆመው ሰው ስለሆነ፤ ቅድሚያ ረመዳንን መፆም አለበት ስለዚህም በተቻለን መጠን ከሸዋል ሱና በፊት የረመዳንን ቀዷ ለማጠናቀቅ መሞከር ይኖርብናል።

نسأل الله تعالى أن يوفقنا لما يحب ويرضى
https://t.me/fe_ilmquran