Get Mystery Box with random crypto!

Eyosi book's ✍🏿

የቴሌግራም ቻናል አርማ eyosc1 — Eyosi book's ✍🏿 E
የቴሌግራም ቻናል አርማ eyosc1 — Eyosi book's ✍🏿
የሰርጥ አድራሻ: @eyosc1
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 864
የሰርጥ መግለጫ

የተለያዩ PDF መፅሐፎችን ለማግኘት @eyoslibrarybot
☎ 0922788490

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-04 16:37:08 የደርግ ሽልጦ - ክፍል 2
አበበ ባልቻ እንዳነበበው

━━━━━━✦✗✦━━━━━━
ከ አሌክስ አብርሃም
ተራኪ አበበ ባልቻ


አዘጋጅ፦⇨@Eyos18

ቸር ጊዜ!

ግሩፑን ለማግኘት

@Mtshaf_bicha
@Mtshaf_bicha
ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
አሰተያየት ካላችሁ
@Eyos18 አድርሱን

Join&share
@EyosC1
ማንበብ ባህላችን ይሁን
┄┉┉✽‌»‌ ••✿•• »‌
✽‌┉┉
8.5K viewsEyosi, 13:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-03 16:49:24 የደርግ ሽልጦ - ክፍል 1
አበበ ባልቻ እንዳነበበው

━━━━━━✦✗✦━━━━━━
ከ አሌክስ አብርሃም
ተራኪ አበበ ባልቻ


አዘጋጅ፦⇨@Eyos18

ቸር ጊዜ!

ግሩፑን ለማግኘት

@Mtshaf_bicha
@Mtshaf_bicha
ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
አሰተያየት ካላችሁ
@Eyos18 አድርሱን

Join&share
@EyosC1
ማንበብ ባህላችን ይሁን
┄┉┉✽‌»‌ ••✿•• »‌✽‌┉┉
8.1K viewsEyosi, 13:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-02 17:27:55 አንዴ ከሄዱ ብትለምኗቸው የማይመለሱ አራት ነገሮች!

ምንጩ ያልታወቀ አንድ ማስታወሻ፡-

በሕይወታችሁ እንደገና ለመመለስ የሚያስቸግሯችሁ አራት ነገሮች፡-

“እድል” - አንዴ ካመለጣችሁ በኋላ!

“ቃል” - አንዴ ከአንደበታችሁ ከወጣ በኋላ!

“ጊዜ” - አንዴ ሳትጠቀሙበት ካለፈ በኋላ!

“አመኔታ” አንዴ ከጎደለ በኋላ ለመመለስ አስቸጋሪ ነው፡፡

1. “እድል” - በአጋጣሚም ሆነ ጠንክራችሁ በመስራታችሁ የመጣን እድል መለየት፣ ማክበርና በተገቢው ሁኔታ መጠቀም፡፡

2. “ቃል” - ሁኔታዎች ሲገፋፏችሁም ሆነ እንዲሁ ስለለመደባችሁ በቀላሉ የምትናገሯቸውን ሰው ጎጂ ንግግሮች በሚገባ ማሰብና ራስን መግታት፡፡

3. “ጊዜ” - በሆነ ባልሆነ የምታባክኑትና አሁን ባላችሁ እድሜ ማድረግ የሚገባችሁን ነገር ባለማድረግ የምታባክኑትን ጊዜ በጥንቃቄ መያዝ

4. “አመኔታ” - ሰዎች ሲያምኗችሁና ራሳቸውንም ሆነ ነገሮቻቸው በእናንተ ላይ ሲጥሉ እምነት ከማጉደል መጠበቅ፡፡

በሉ እንግዲህ፣ ያለፈው አልፏል፣ የባከነው ባክኗል፡፡ የተራረፈውን እንሰባስበውና ሕይወትን እንደገና በአዲስ መልክ እንጀምር፡፡

ዶ/ር እዮብ ማሞ

ቸር ጊዜ!

#መልካም ምሽት !!

ግሩፑን ለማግኘት
@Mtshaf_bicha
@Mtshaf_bicha
ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
አሰተያየት ካላችሁ
@Eyos18 አድርሱን

Join&share
@EyosC1
ማንበብ ባህላችን ይሁን
┄┉┉✽‌»‌ ••✿•• »‌✽‌┉┉
9.0K viewsEyosi, 14:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-31 16:46:48 "ጠላታችን ሥም ነው!"

ሥም ከወላጅ የሚሰጠን
ቅርስ ነው። በውስጡ ፍላጎት፣ እምነት፣ ፍቅር፣ ተስፋ…ያጨቁ እንድምታዎች
ሊኖሩት ይችላሉ። በግብር የምንወርሳቸው ሥሞችም አሉ። የሆነ ተግባር ፈፅመን
የምንደርባቸው አይነት። የሥም ዋና ጥቅሙ አንዱን ከአንዱን ለመለየት
ይመስለኛል። ይህ ሆኖ ሳለ ግን ሥምን እንደ ማነፃፀሪያ መቁጠሩ እየተለመደ
መጥቷል። የምናከብረው፣ ዋጋ የምንሰጠው፣ የምናስቀድመው የግለሰብ
ማንነት ቀርቶ ሥምን ሆኗል። ሐብታም ለሚባል ስያሜ እናሸረግዳለን፤ የኔ
ቢጤውን እናንቋሽሻለን። ለዶክተሩ ክብር ይኖረናል፤ ተራውን ዜጋ እንንቃለን።
አንዱን ሰው ከሌላው፣ አንዱን ብሄር ተወላጅ ከሌላው፣ አንዱን ሐይማኖት
ተከታይ ከሌላው የምንወደው፣ የምንጠላው…የምናከብረው፣ የምንንቀው…
የምንቀርበው፣ የምንርቀው ማንነትን መሰረት አድርገን ሳይሆን ሥምን ተከትለን
ነው። ግን ያልተገለፀልን ከሥም ሰው የመሆን ማንነት እንደሚቀድም ነው።
በእኩል አይን ለመመልከት ሥም አያስፈልጋችሁም፤ ማንነት በቂ መሠረት ነው።
፧
ሥም የለኝም፣ ሥም የለኝም በቤቴ
አንዱ እምዬዋ ሲለኝ፣ አንዱ ሲለኝ አከላቴ
ጎኔ ሽታዬዋ ሲሉኝ
በፍቅራቸው ሲጠሩኝ…(ጂጂ)
ሥም ከሌለህ ሁሉም ሥሞችህ ይሆናሉ። ይሄ ደግሞ ሰውነት ይባላል። አየህ
ጠቢቧ ቀድማ ተናግራ ነበር።
፧
በGame of Thrones ተከታታይ ፊልም ላይ ከብዙዎቹ ውስጥ አንድ የምወዳት
ወሳኝ ጭብጥ አለች። Jaqen H'gar የሚባለው ገፀ-ባህሪ አንዲት የመሳፍንት
ዘር ያለባትን እንስት ፊት የለሽ (face less) እንድትሆን ሲያሰለጥናት ይታያል።
ይሄም ፊትን በቀላሉ እየቀያየሩ ሰዎችን ለመግደል እንዲያመች ነው። አዚች ጋር
ፋንጣዚ (fantacy) ነገር አለበት። እናም ፊት የለሽ ለመሆን በቅድሚ ከበፊት
ሥሞችህ ጋር መፋታት ይኖርብሃል። ማንም፣ ሥም የለሽ (No one) መሆን
አለብህ።
በስልጠናው ሒደት የምትሰለጥነው ጉብል Arya Stark ከበፊት ሥሟ በቀላሉ
መለያየት የሚሆንላት አልሆነም። ተልኮ ቢሰጣትም የበፊት ሥሟ ተፅኖ
እያደረገባት ሳትፈፅም ቀርታ አሰልጣኟ አይነ-ስውር ያደርጋታል። በዚህም በብዙ
ትፈተናለች። ትራባለች፣ ትታረዛለች…። መምህሯ በመጨረሻ ይመጣና "ልጅቷ
ሥሟን ከነገረችኝ ምግብ፣ መጠለያ እሰጣታለሁ፤ ብሎም የአይን ብርሃኗን
እመልስላታለሁ?" እያለ ይፈትናታል። ልጅቷም "ማንም (No one) ነኝ" እያለች
ትፀናለች። እንዲያ ከሆነ ይልና ጤና የሚሰጠውን (ዓይንን የሚያበራውን) ውሃ
መሳይ ፈሳሽ እንድትጠጣ ይሰጣታል። በእርግጥ ፈሳሹ ሞትም አምጪ መሆኑ
መታወቅ አለበት። በዚህ ወቅት ማቅማማት (እንዳትሞት ፈርታ) ሲታይባት ወሳኝ
ነጥቧን ያነሳል "ልጅቷ የእውነት ማንም ከሆነች ምንም የሚያስፈራት ነገር
የለም" (If a girl is truly 'no one', she has nothing to fear.)
ብዙሃኑ ሰው በልቡ ፍርሃት እንዲነግስበት የሚያደርገው እንደካባ ደርቦ ደራርቦ
የሚዞረው ሥሙ ነው። በአብዛኛው ሰው የሚፈራው ለማንነቱ ሳይሆን ለሥሙ
ነው። የሚጠነቀቀውም ለሥሙ ነው። የሚታመነውም እንደዛው። እንዳልሰደብ፣
እንዳልበለጥ፣ እንዳልወድቅ፣ መጠቋቆሚያ እንዳልሆን። መሞት የምትፈሩትም
ለሥማችሁ ነው። ወልጄ ከብጄ የምትሉትም ነገር አለ። የምትወልዱትም
ለሥማችሁ ነው። ተሽቀዳድማችሁ ዶክተር፣ ኢንጂነር፣ ዳኛ መሆን
የምትፈልጉትም ለሥማችሁ ነው። ከሰው በላይ እንዲጠራ፤ በለጥኩኝ ለማለት
ነው። አያችሁ ማንም (No one) ከሆናቹ ግን ሁሉም ሥሞች መጠሪያዎቻችሁ
ይሆናሉ። ያኔ ሥሞቻቹ ማንነታችሁ አይሆንም፤ ማንነታችሁ ሥሞቻችሁ ይሆናሉ
እንጂ።
፧
ከዚህ ሐሳብ ጋር ቀጥተኛ ተዛምዶ ባይኖራትም ኤሚኒዬም የሚላትን አንድ
አባባል ማንሳት ተገቢ ይመስለኛል። "የምታጣው ምንም ነገር ከሌለ ፣
ምታገኘው ሁሉንም ነው" (When you have nothing to lose, you have
everything to gain)። የኔ ሐበሻ ጠቢቡ "የበሰበሰ ዝናብ አይፈራም"
እንዳለው ማለት ነው።

ዳዊት ወንድማገኝ (ዶ/ር)

የተዝናና የፈካ ምሽት ይሁንልን

ግሩፑን ለማግኘት

@Mtshaf_bicha
ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
አሰተያየት ካላችሁ
@Eyos18 አድርሱን

Join&share
@EyosC1
ማንበብ ባህላችን ይሁን
10.5K viewsEyosi, 13:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-28 14:23:10
ዛሬ ደግሞ ስለ ኦሾ ጥቂት እንበል።
የኦሾ ትምህርቶች ለአመዳደብ አይመቹም። ከግላዊ የፍቺ ፍለጋ ጀምሮ እጅግ
አንገብጋቢ እስከሆኑ የዘመኑ ማህረሰብ የተጋፈጣቸውን ጉዳዮች ይሸፍናሉ።
መፅሀፎቹ ለመፅህፍ አንባቢ ተብለው የተፃፉ ሳይሆኑ በሰላሳ አምስት አመታት
ጊዜ ውስጥ ለአለም አቀፍ ታዳሚዎች ካቀረባቸው ያልተዘጋጀባቸው የድምፅና
የቪዲየ ንግግሮች በፅሁፍ የተገለበጡ ናቸው።
ኦሾ በለንደኑ ሰንዴይ ታይምስ "ከ1000ዎቹ የ20ኛው ክ/ዘመን ተጽእኖ
ፈጣሪዎች አንዱ› እንዲሁም በአሜሪካዊው ዴራሲ በቶም ሮቢንስ "ከክርስቶስ
በኋላ የተፈጠረ በጣም አደገኛ ሰው ተብሎ ተነግሮለታል።
ኦሾ ስለ ገዛ ራሱ ሲናገር ለአዲስ የሰው ልጅ መወለድ አመቺ
ሁኔታዎችን እየፈጠረ መሆኑን ይናገራል። አብዛኛውን ጊዜ ይህንን አዲስ የሰው
ልጅ "ዞብራ ዘ ቡድሃ" ብሎ ይገልፀዋል።
ትርጉሙም የግሪኩን የዞብራን ዓለማዊ ደስታና የጉተማ ቡድሃን ፀጥ ያለ
የመንፈስ እርጋታ አጣምሮ የሚደሰት ማለት ነው። በኦሾ ስራዎች አጠቃላይ ገፅታ
ላይ ጊዜ የማይሽረውን የምስራቁን ዓለም ጥበብ እና በምዕራቡ አለም ሳይንስና
ቴክኖሎጂ እምቅ ሀይል ያቀፈ ራዕይ እንደክር ተጠምጥሞ ይታያል።
ኦሾ በተጨማሪም ለውስጣዊ ለውጥ ባበረከታቸው አብዮታዊ አስተዋፅዎችም
ይታወቃል። በዚህ አስተዋፅኦው በተመስጦ ማስላሰልን በፈጣን ለውጥ ላይ
የሚገኘው ተዛማጅ ህይወት ላይ ጠቀሜታ እንዲኖረው አስችሎታል።
በአይነት ልዩ የሆኑት የ'አክቲቭ ሜዲቴሽንስ'(ብርቱ የሆኑ በተመስጦ የማሰላሰል)
እሳቤዎቹ በመጀመሪያ ደረጃ የተከማቹትን የአካልና የአእምሮን ውጥረቶች
በማስወጣት ላይ ያነጣጠሩ ናቸው።
በዚህም የተነሳ ከሀሳብ ነፃ የሆነ እና ዘና ያለ በተመስጦ የማሰላሰል ተግባርን
ለመለማመድ ቀላል ይሆናል።

#ኦሾ


Join&share
@EyosC1
ማንበብ ባህላችን ይሁን
13.1K viewsEyosi, 11:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-28 14:18:18 የመሲሆች እድር

ቡርሃን አዲስ በቅርቡ የመሲሆች እድር በሚል ርዕስ ለህተመት ያበቃውን
መጽሐፍ አስመልክቶ የተሰጠ አስተያየት።
(ዳግም)
ለቡርሃን አዲስ (ደራሲ)
'ሰው ተጠንቶ ያላለቀ ፍጡር ነው!' 'አገር በወሬ አይገነባም!' 'ሰው በባህሪው
አሳቡ እንዲሳካለት ይፈልጋል ግን ራሱ እንዳይሳካለት እያጠቃው
ይኖራል!' ....የሚሉት ዲስኩሮችኽ ይበልጥ ይስቡኛል።
ደምስር ነዛሪነታቸው፣ ልብም ገፍታሪነታቸው ይልቃል።
...ወደ መሲሆች እድር (አዲሱ ህትመት) ስመለስ...! መጽሐፉ ለአንባቢያን
ተደራሽ እንዲሆን ታስቦ በድጋሜ ለህተመት መብቃቱ እጅግ በጣም ደስ
የሚያሰኝ ነው። ምክንያቱም ካንተ ፍቃድ ውጪ መጽሐፉን ለህትመት ሰድደው
የነበሩን ግለሰቦች ተቆጣጥረህ በድጋሜ ለህትመት ማብቃት መቻልህ በራሱ
ትልቅ የሞራል ግንባታ ከመሆኑም ባለፈ ለአንባቢ፣ አድናቂዎች መነቃቃትን
ይፈጥራል።
የመሲሆች እድር መጽሐፍን
...እንደ ዳዊት ደጋግመን ልናነበው የሚገባ መጽሐፍ ነው ብዬ አምናለሁ።
የመሲሆች እድር ወቅታዊነቱን የጠበቀ መሰረታዊና በጣም አስፈላጊ መጽሐፍ
እንደ መሆኑ መጠን "Classic Book" ብዬ ከመረጥኳቸው ምርጥ መጽሐፍቶች
ተርታ ሰድሬዋለሁ። በተለይ መዝለቂያው አካባቢ ሰላምና አንድነትን በተጨባጭ
የፍልስፍና አይን የቃኘኽበት መንገድ ለሁሉ አንባቢ፣ ንባብ ወዳድ፣ እንዲሁም
በልዩ ልዩ ዘርፍ ተሰማርተው ለሚሰሩ ፣ ለዩኒቨርስቲ ኮሌጅ ተማሪዎች ሁሉ
አስፈላጊነቱ በጣም መሰረታዊ ነው።
ስለ መሲሆች እድር መጽሐፍ ሁለገብነት ሳስብ ከዚህ ቀደም ለህትመት
አብቅተኻቸው ከነበሩ 34/35 መጽሐፍቶች መካከል መሲሆች ይለያል። 'ረ
እንደውም ግነት ካልሆነብኝ ከሁሉ መጽሐፍቶችህ ተጨምቆና ተውጣጥቶ
የተሰደረም ይመስለኛል። የመሲሆች እድር ከሁሉ መጽሐፍቶች የመጨረሻው
ስራኽ እንደመሆኑ መጠን ዛሬ ያለው ቡርሃን አዲስ በመጽሐፉ ውስጥ ይገኛል።
መጽሐፉን አንብቤ ለመረዳት ሙከራ ባደረኩት ጥረት አብዛኛውን ላይ
ወጥተሃል፣ ጥቂትም ታች ወርደሃል (መግቢያ አካባቢ) መሃል ላይ ሆነህ
ሚዛንህን እንደጠበቅህ አቅርበሃል። ሶስቱንም የአንባቢ ደረጃ ፍላጎት አሟልተህ
አቅርበሀል። ይህ ደግሞ በጣም ድንቅና ተመራጭ ውሳኔ ነው። በ'ትኛውም
ደረጃ ላይ ያሉ አንባቢያን መጽሐፉን ገዝተው አቅማቸው በፈቀደ ልክ በማንበብ
መጽሐፉ ውስጥ ያለውን እምቅ እይታ፣ እውቀት፣ ፍልስፍናውን ሁሉ ሳይቸገሩ
በቀላሉ እንደ ቅኔ ሊዘርፉ ይችላሉ። በጥቅሉ እንደኔ እይታ መሲሆች ለማንና
ለየትኛው ክፍል ታስቦ ተጻፈ ? ቢባል! ሁሉም ለኔ የሚል ይመስለኛል። በተለይ
በተለይ አሁን ላይ በማህበራዊ ጉዳይ ዙሪያ ይበልጥ ግንዛቤ ለሚያስፈለገን
ማህበረሰብ የሰላምን ጉዳይ በፍልስፍና መነጥር ለመመልከት የቻልክበት
መንገድ "Extremely Thank You" የሚያስብል ነው።...ብዙ አሳቦች በአንድ
ጥራዝ ሰብሰብ ተደርገው ተቃኝተዋል። ቀርበዋል። ይህ በራሱ እንደው ምስጉን
መሆን መቻል ብቻም ሳይሆን ትልቅ ትልቅነት ነው።
...ነጣጥሎ ማንበብ የሚሻም አንባቢ ቢፈልግ የሳበውን ነጠላ ርዕስ ብቻ
ከመካከል መዘዝ እያደረገ ሊያነብ የሚችለው አይነት መጽሐፍ ነው! የመሲሆች
እድር።
በተለይ ደግሞ በመሲሆች እድር ውስጥ ተካተው ያሉት ነጠላ (ንዑስ) አሳቦች
የጋራ ውይይትን ለመፍጠር ምቹ ሁኔታን ያመቻቹ ናቸው። መጽሐፉ ውስጥ
በተነሱት አሳቦች ምክንያት አንባቢው በራሱ መንገድም ብዙ እንዲመረምርም
እድል የሰጠ ነው።
በአጠቃላይ የመሲሆች እድር ውስጣዊ ይዘቱ፤ ሁለንተናዊነትን ያገናዘበ ነው።
አሳቦችን በተለየ መንገድ ይመለከታል። ጠጣር መልዕክቶችን አስተላልፏል።
ፍንጭ ይሰጣል።
መጽሐፉን ገዝቶ ያነበበ ወይም ገና ገዝቶ ለሚያነብ አንባቢ የምለው ነገር ቢኖር
ምንም ጥያቄ የለውም ያተርፍበታል።
ሁሉም ብቻውን በሁለት እግሩ መቆም ቢሻ የራሱ መሲህ መሆን አለበት። ሁሉም
የራሱን መሲህነት አረጋገጠ ማለት ሰላምና ስልጣኔ በአንድነት ወደ ላይ ከፍ ከፍ
ይላሉ። ያኔ ምዕራባዊያን ጥቁሮች ላይ የሚያሴሩትን ረቂቅ በደል ሁሉ መረዳት
እንድንችል ያግዘናል። ይህ ሲሆን ሁዋላ ቀርነት ና ችግር የተቆጣጠሩትን ቦታ
ለአሳብ ልዕልና (ስልጣኔ) ይለቃሉ።
በዚህ ረገድ ማህበራዊ ጉዳዮችን በፍልስፍና መንገድ የምታይበት መነጽር
በእውነቱ የሚያስመሰገን ነው። ባህልና እምነትን ባከበረ መንገድ እየተቸህ፣
እያስተማርክ፣ ትውልድን እያነጽክ ነውና።
መሲሆችን ያላነበበ ሁሉ እንደ እድለኛ ሊቆጠር ይችላል። ክረምት እንደመሆኑ
መጠን ክረምትና መጽሐፍ፣ንባብ ሲገናኙ.........

ውብ ቀን

ግሩፑን ለማግኘት

@Mtshaf_bicha
ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
አሰተያየት ካላችሁ
@Eyos18 አድርሱን

Join&share
@EyosC1
ማንበብ ባህላችን ይሁን
10.3K viewsEyosi, 11:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-25 14:13:01 የልብ_ማህተም

ሰው ነው የናፈቀኝ !
ሕዝብማ ወንዝ ነው…
ቁልቁል የሚደፋ ቀና ብሎ እማያይ
እያመመው ተጓዥ በቀደዱለት ቦይ
ሕዝብማ ወንዝ ነው…
አፈር የሚበላው ከድንጋይ የሚጋጭ
እያዘነ የሚጎርፍ የሚታይ በግላጭ
ሕዝብማ ወንዝ ነው…
‘’ሂድ’’ ሲሉት ይሄዳል
የደፈረሰ ነፍስ በቅሬታ ይዞ
‘’ቁም’’ ሲሉት ይቆማል
በውስጡ እያነባ በእድሉ ተክዞ
ሕዝብማ ወንዝ ነው…
የደረቀን መሬት
በእንባው የሚያለማ ላቡን እያጠጣ
በዘፍጥረት ዘመን
ካገሬ ተራሮች መሀፀን የወጣ
ሕዝብማ ወንዝ ነው…
ሰው ነው የናፈቀኝ
ሰው ነው የእምነቴ ዕዳ
ጭፍን የማይጓዝ ጅምላ እማይነዳ
የወንዙን ስሞታ ሰምቶ የተረዳ
የሰውነትን ልክ ካምላኩ የቀዳ
ሰው ነው…ሰው ነው የናፈቀኝ…
ከወንዙ የወጣ ከምንጩ የሚገኝ
ሰው ነው…ሰው ነው የናፈቀኝ
እንደ በትረ ሙሴ
ባህሩን ባይከፍልም ተዓምር ባይሰራ
ምፅአት ላይ ሆኜ
‘’ምፅአቱ ደርሷል!’’ ብሎ እማያስፈራ
ከፍቅር የሚያስታርቅ ከእምነቱ ስፍራ
ከተስፋ እሚያጋባ ደግሞም ከእውነት ጋራ
ሰው ነው…ሰው ነው የናፈቀኝ !
ሕዝብነት ሰለቸኝ…
ወንዝነት ደከመኝ…
አፈሩ መረረኝ ድንጋይ አቆሰለኝ
ከዚህ ጨፍጋጋ አዚም ዙሪት የሚያስቆመኝ
ቂሜን የሚያስረሳ ፍቅር የሚያስተምረኝ
ሰው ነው…ሰው ነው የናፈቀኝ !!!
* * * *
ገጣሚ_ሰለሞን_ሳህለ

ውብ ቀን

ግሩፑን ለማግኘት

@Mtshaf_bicha
ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
አሰተያየት ካላችሁ
@Eyos18 አድርሱን

Join&share
@EyosC1
ማንበብ ባህላችን ይሁን
12.3K viewsEyosi, 11:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-24 17:39:18 የሕልሜ ቅዠት ውስጥ

ደስ ሲል ዓየሩ፣ከጠዋት ጀምሮ፣
እሳት መሳይ ፀሀይ፣ ሰማይ አሳምሮ፣
ብርማ መሬቱን፣ በወርቅ ቀይሮ፣
ያገሩ በሙሉ፣ፅዳት እንከን የለው፣
መንገድና ቤቱ፣ ሁሉም ቦታ ያለው፣
ሰዎች ጨርቅ ፈንታ፣ ብርሀንን ለብሰው፣
ጉድፍ በማያውቀው፣ሽፋን ተኮፍሰው፣
ያይናቸው ብርሀን፣ አይመስል የተፈጥሮ፣
መላ ሰውነትን፣ በፍቅር ቀይሮ።
ብሩህ ፈገግታቸው፣ ማንንም አይለቅም፣
ረሀብ ጥማትን፣ ችግርን አያውቅም።
የሰው ፊት ብርሀን፣በፍቅር የራሰው፣
ጥላቻን አያውቅም፣ ቢሆንም ማንም ሰው፣
ሀይማኖትና ዘር፣ ክብሩን አይቀንሰው።
የእኩልነት ጣዕም፣ ደማቸው ውስጥ ሰርጎ፣
ሁሉን በጠቅላላ፣ ልዩ ሰው አድርጎ፣
ያጭር ሕይወት ዋጋ፣ አጉል አይቀነስ።
በማያልቅ ትንንቅ፣ደም በከንቱ አይፈስ።
እርግጥ ታሪክ ነበር፣ዘመን የለው አቻ፣
ሰው ሁሉ ሲዘጋጅ፣ ሰው ለማጥፋት ብቻ፣
አስር ሚሊዮን ዓመት፣ ታሪክ እንደሚለው፣
ጦር መሣሪያ ሲቀር፣ ጥፋት ሞት ያዘለው።
እፎይ አለ ዓለሙ፣ ይኸው ረጅም ዓመት፣
ሁሉም ሁሌ ይሰራል ፣ ለሁሉም ሰው እድገት፣
ሁሉም ቤት ደስታ፣ በመልካሙ ሕይወት።
ሰላም ተንሰራፋ፣ ከጧት እስከማታ፣
ብርሃን አሸነፈ፣ ጨለማ ተረታ
።

የተዝናና የፈካ ምሽት ይሁንልን

ግሩፑን ለማግኘት

@Mtshaf_bicha
ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
አሰተያየት ካላችሁ
@Eyos18 አድርሱን

Join&share
@EyosC1
ማንበብ ባህላችን ይሁን
11.1K viewsEyosi, 14:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-22 18:26:49
አንድ ሰዉ የጠዋት ዜናን ለማንበብ ጋዜጣ ሲያገላብጥ የእራሱን ስምና ፎቶ
ከጋዜጣዉ መግቢያ ላይ ይመለከታል።
ዘጋቢዉም በስህተት የዚህን ሰዉ መሞት
ለአለም አሳወቀ።ሰዉዬዉ ይህን ሲመለከት በጣም ደነገጠ 'እንዴ ሞቻለሁ
አንዴ?' የሚል ነበር ምላሹ።የዚህን ሰዉ ሞት ለመግለፅ በጋዜጣው ላይ
'የተቀጣጣይ ፈንጁ ንጉስ ሞተ(dynamite king dies)እንዲሁም 'የሞት
ነጋዴዉ ሞተ(merchant of death dies)የሚሉ ርዕሶች ተሰጥተዉታል።ይህ
ሰዉ ግዙፍ ግድቦችንና ህንፃወችን ለማዉደም የሚያሰችል ተቀጣጣይ ፈንጂን
(dynamite) የፈለሰፈ እንዲሁም ጦር መሳሪያዎችን በመሸጥ ኪሱን በረብጣ
ዶላሮች መሙላት የቻለ ታዋቂ ባለሀብት ነዉ።ጋዜጣዉ ላይ ስለ እሱ ሞት
ሲዘገብ 'የሞት ነጋዴ' ተብሎ የተገለፀበትን ቃል ሲያነብ ዉስጡ ላይ 'እንደዚህ
ነዉ የምታወሰዉ ማለት ነዉ?'የሚል ጥያቄ ፈጠረበት።
ከእራሱ ጋር ከተሟገተ በኋላ ከዚህ በኋላ በእዚህ አይነት መልኩ መታወስ
አልፈልግም በማለት ስለ ሰላም መስራት ጀመረ።ይህ ሰዉ አልፍሬድ ኖቤል
ይባላል።ዛሬ ይህን ሰዉ እጅግ በተከረዉና ስለ ሰላም ለተጉ ሰዎች በሚሸለመዉ
የኖቤል ሽልማት አለም ያታወሳል።
እኛስ አንዴት መታወስ እንፈልጋለን በሰዉ ወዳድነት፣በአክባሪነት ወይስ በጥላቻና
በዘረኝነት?
በሰዎች ልብ ዉስጥ የምንናፈቅ ነን? ወይስ...?

ለቤተሰባችን፣ለጓደኞቻችን፣ለሀገራችን ባበረከትነዉ መልካም ነገር ነዉ
የምንታወሰዉ ወይስ በክፋታችን?

የተዝናና የፈካ ምሽት ይሁንልን

ግሩፑን ለማግኘት

@Mtshaf_bicha
ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
አሰተያየት ካላችሁ
@Eyos18 አድርሱን

Join&share
@EyosC1
ማንበብ ባህላችን ይሁን
13.1K viewsEyosi, 15:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-21 15:48:46
"እንኳንስ ሚልዮኖች ይቅርና አዳምና ሄዋንም በገነት ውስጥ አልተስማሙም
ነበር።"

.
"...ልባሞች ሁኑ ፤ ከጥላቻ ነጻ ውጡ ፤ ከተራ አመለካከትና ከጎጠኝነት ነጻ ውጡ
፤ የሌላ ችግር ብቻ ሳይሆን መጀመርያ የራሳችሁ ችግር አራግፋችሁ ታጠቡ ፤
የባሰው እንዳይመጣ ጸልዩ ፤ የተሻለውን ስጠን እንጂ እገሌ ይውደም እገሌ
ይሁንልን አይባልም።"


መጋቤ ሐዲስ እሸቱ አለማየሁ

#መልካም ግዜ !!

ግሩፑን ለማግኘት

@Mtshaf_bicha
@Mtshaf_bicha
ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
አሰተያየት ካላችሁ
@Eyos18 አድርሱን

Join&share
@EyosC1
ማንበብ ባህላችን ይሁን
┄┉┉✽‌»‌ ••✿•• »‌✽‌┉┉
12.7K viewsEyosi, 12:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ