Get Mystery Box with random crypto!

ዛሬ ደግሞ ስለ ኦሾ ጥቂት እንበል። የኦሾ ትምህርቶች ለአመዳደብ አይመቹም። ከግላዊ የፍቺ ፍለጋ ጀ | Eyosi book's ✍🏿

ዛሬ ደግሞ ስለ ኦሾ ጥቂት እንበል።
የኦሾ ትምህርቶች ለአመዳደብ አይመቹም። ከግላዊ የፍቺ ፍለጋ ጀምሮ እጅግ
አንገብጋቢ እስከሆኑ የዘመኑ ማህረሰብ የተጋፈጣቸውን ጉዳዮች ይሸፍናሉ።
መፅሀፎቹ ለመፅህፍ አንባቢ ተብለው የተፃፉ ሳይሆኑ በሰላሳ አምስት አመታት
ጊዜ ውስጥ ለአለም አቀፍ ታዳሚዎች ካቀረባቸው ያልተዘጋጀባቸው የድምፅና
የቪዲየ ንግግሮች በፅሁፍ የተገለበጡ ናቸው።
ኦሾ በለንደኑ ሰንዴይ ታይምስ "ከ1000ዎቹ የ20ኛው ክ/ዘመን ተጽእኖ
ፈጣሪዎች አንዱ› እንዲሁም በአሜሪካዊው ዴራሲ በቶም ሮቢንስ "ከክርስቶስ
በኋላ የተፈጠረ በጣም አደገኛ ሰው ተብሎ ተነግሮለታል።
ኦሾ ስለ ገዛ ራሱ ሲናገር ለአዲስ የሰው ልጅ መወለድ አመቺ
ሁኔታዎችን እየፈጠረ መሆኑን ይናገራል። አብዛኛውን ጊዜ ይህንን አዲስ የሰው
ልጅ "ዞብራ ዘ ቡድሃ" ብሎ ይገልፀዋል።
ትርጉሙም የግሪኩን የዞብራን ዓለማዊ ደስታና የጉተማ ቡድሃን ፀጥ ያለ
የመንፈስ እርጋታ አጣምሮ የሚደሰት ማለት ነው። በኦሾ ስራዎች አጠቃላይ ገፅታ
ላይ ጊዜ የማይሽረውን የምስራቁን ዓለም ጥበብ እና በምዕራቡ አለም ሳይንስና
ቴክኖሎጂ እምቅ ሀይል ያቀፈ ራዕይ እንደክር ተጠምጥሞ ይታያል።
ኦሾ በተጨማሪም ለውስጣዊ ለውጥ ባበረከታቸው አብዮታዊ አስተዋፅዎችም
ይታወቃል። በዚህ አስተዋፅኦው በተመስጦ ማስላሰልን በፈጣን ለውጥ ላይ
የሚገኘው ተዛማጅ ህይወት ላይ ጠቀሜታ እንዲኖረው አስችሎታል።
በአይነት ልዩ የሆኑት የ'አክቲቭ ሜዲቴሽንስ'(ብርቱ የሆኑ በተመስጦ የማሰላሰል)
እሳቤዎቹ በመጀመሪያ ደረጃ የተከማቹትን የአካልና የአእምሮን ውጥረቶች
በማስወጣት ላይ ያነጣጠሩ ናቸው።
በዚህም የተነሳ ከሀሳብ ነፃ የሆነ እና ዘና ያለ በተመስጦ የማሰላሰል ተግባርን
ለመለማመድ ቀላል ይሆናል።

#ኦሾ


Join&share
@EyosC1
ማንበብ ባህላችን ይሁን