Get Mystery Box with random crypto!

'ጠላታችን ሥም ነው!' ሥም ከወላጅ የሚሰጠን ቅርስ ነው። በውስጡ ፍላጎት፣ እምነት፣ ፍቅር፣ ተስ | Eyosi book's ✍🏿

"ጠላታችን ሥም ነው!"

ሥም ከወላጅ የሚሰጠን
ቅርስ ነው። በውስጡ ፍላጎት፣ እምነት፣ ፍቅር፣ ተስፋ…ያጨቁ እንድምታዎች
ሊኖሩት ይችላሉ። በግብር የምንወርሳቸው ሥሞችም አሉ። የሆነ ተግባር ፈፅመን
የምንደርባቸው አይነት። የሥም ዋና ጥቅሙ አንዱን ከአንዱን ለመለየት
ይመስለኛል። ይህ ሆኖ ሳለ ግን ሥምን እንደ ማነፃፀሪያ መቁጠሩ እየተለመደ
መጥቷል። የምናከብረው፣ ዋጋ የምንሰጠው፣ የምናስቀድመው የግለሰብ
ማንነት ቀርቶ ሥምን ሆኗል። ሐብታም ለሚባል ስያሜ እናሸረግዳለን፤ የኔ
ቢጤውን እናንቋሽሻለን። ለዶክተሩ ክብር ይኖረናል፤ ተራውን ዜጋ እንንቃለን።
አንዱን ሰው ከሌላው፣ አንዱን ብሄር ተወላጅ ከሌላው፣ አንዱን ሐይማኖት
ተከታይ ከሌላው የምንወደው፣ የምንጠላው…የምናከብረው፣ የምንንቀው…
የምንቀርበው፣ የምንርቀው ማንነትን መሰረት አድርገን ሳይሆን ሥምን ተከትለን
ነው። ግን ያልተገለፀልን ከሥም ሰው የመሆን ማንነት እንደሚቀድም ነው።
በእኩል አይን ለመመልከት ሥም አያስፈልጋችሁም፤ ማንነት በቂ መሠረት ነው።

ሥም የለኝም፣ ሥም የለኝም በቤቴ
አንዱ እምዬዋ ሲለኝ፣ አንዱ ሲለኝ አከላቴ
ጎኔ ሽታዬዋ ሲሉኝ
በፍቅራቸው ሲጠሩኝ…(ጂጂ)
ሥም ከሌለህ ሁሉም ሥሞችህ ይሆናሉ። ይሄ ደግሞ ሰውነት ይባላል። አየህ
ጠቢቧ ቀድማ ተናግራ ነበር።

በGame of Thrones ተከታታይ ፊልም ላይ ከብዙዎቹ ውስጥ አንድ የምወዳት
ወሳኝ ጭብጥ አለች። Jaqen H'gar የሚባለው ገፀ-ባህሪ አንዲት የመሳፍንት
ዘር ያለባትን እንስት ፊት የለሽ (face less) እንድትሆን ሲያሰለጥናት ይታያል።
ይሄም ፊትን በቀላሉ እየቀያየሩ ሰዎችን ለመግደል እንዲያመች ነው። አዚች ጋር
ፋንጣዚ (fantacy) ነገር አለበት። እናም ፊት የለሽ ለመሆን በቅድሚ ከበፊት
ሥሞችህ ጋር መፋታት ይኖርብሃል። ማንም፣ ሥም የለሽ (No one) መሆን
አለብህ።
በስልጠናው ሒደት የምትሰለጥነው ጉብል Arya Stark ከበፊት ሥሟ በቀላሉ
መለያየት የሚሆንላት አልሆነም። ተልኮ ቢሰጣትም የበፊት ሥሟ ተፅኖ
እያደረገባት ሳትፈፅም ቀርታ አሰልጣኟ አይነ-ስውር ያደርጋታል። በዚህም በብዙ
ትፈተናለች። ትራባለች፣ ትታረዛለች…። መምህሯ በመጨረሻ ይመጣና "ልጅቷ
ሥሟን ከነገረችኝ ምግብ፣ መጠለያ እሰጣታለሁ፤ ብሎም የአይን ብርሃኗን
እመልስላታለሁ?" እያለ ይፈትናታል። ልጅቷም "ማንም (No one) ነኝ" እያለች
ትፀናለች። እንዲያ ከሆነ ይልና ጤና የሚሰጠውን (ዓይንን የሚያበራውን) ውሃ
መሳይ ፈሳሽ እንድትጠጣ ይሰጣታል። በእርግጥ ፈሳሹ ሞትም አምጪ መሆኑ
መታወቅ አለበት። በዚህ ወቅት ማቅማማት (እንዳትሞት ፈርታ) ሲታይባት ወሳኝ
ነጥቧን ያነሳል "ልጅቷ የእውነት ማንም ከሆነች ምንም የሚያስፈራት ነገር
የለም" (If a girl is truly 'no one', she has nothing to fear.)
ብዙሃኑ ሰው በልቡ ፍርሃት እንዲነግስበት የሚያደርገው እንደካባ ደርቦ ደራርቦ
የሚዞረው ሥሙ ነው። በአብዛኛው ሰው የሚፈራው ለማንነቱ ሳይሆን ለሥሙ
ነው። የሚጠነቀቀውም ለሥሙ ነው። የሚታመነውም እንደዛው። እንዳልሰደብ፣
እንዳልበለጥ፣ እንዳልወድቅ፣ መጠቋቆሚያ እንዳልሆን። መሞት የምትፈሩትም
ለሥማችሁ ነው። ወልጄ ከብጄ የምትሉትም ነገር አለ። የምትወልዱትም
ለሥማችሁ ነው። ተሽቀዳድማችሁ ዶክተር፣ ኢንጂነር፣ ዳኛ መሆን
የምትፈልጉትም ለሥማችሁ ነው። ከሰው በላይ እንዲጠራ፤ በለጥኩኝ ለማለት
ነው። አያችሁ ማንም (No one) ከሆናቹ ግን ሁሉም ሥሞች መጠሪያዎቻችሁ
ይሆናሉ። ያኔ ሥሞቻቹ ማንነታችሁ አይሆንም፤ ማንነታችሁ ሥሞቻችሁ ይሆናሉ
እንጂ።

ከዚህ ሐሳብ ጋር ቀጥተኛ ተዛምዶ ባይኖራትም ኤሚኒዬም የሚላትን አንድ
አባባል ማንሳት ተገቢ ይመስለኛል። "የምታጣው ምንም ነገር ከሌለ ፣
ምታገኘው ሁሉንም ነው" (When you have nothing to lose, you have
everything to gain)። የኔ ሐበሻ ጠቢቡ "የበሰበሰ ዝናብ አይፈራም"
እንዳለው ማለት ነው።

ዳዊት ወንድማገኝ (ዶ/ር)

የተዝናና የፈካ ምሽት ይሁንልን

ግሩፑን ለማግኘት

@Mtshaf_bicha
ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
አሰተያየት ካላችሁ
@Eyos18 አድርሱን

Join&share
@EyosC1
ማንበብ ባህላችን ይሁን