Get Mystery Box with random crypto!

የልብ_ማህተም ሰው ነው የናፈቀኝ ! ሕዝብማ ወንዝ ነው… ቁልቁል የሚደፋ ቀና ብሎ እማያይ እያመመ | Eyosi book's ✍🏿

የልብ_ማህተም

ሰው ነው የናፈቀኝ !
ሕዝብማ ወንዝ ነው…
ቁልቁል የሚደፋ ቀና ብሎ እማያይ
እያመመው ተጓዥ በቀደዱለት ቦይ
ሕዝብማ ወንዝ ነው…
አፈር የሚበላው ከድንጋይ የሚጋጭ
እያዘነ የሚጎርፍ የሚታይ በግላጭ
ሕዝብማ ወንዝ ነው…
‘’ሂድ’’ ሲሉት ይሄዳል
የደፈረሰ ነፍስ በቅሬታ ይዞ
‘’ቁም’’ ሲሉት ይቆማል
በውስጡ እያነባ በእድሉ ተክዞ
ሕዝብማ ወንዝ ነው…
የደረቀን መሬት
በእንባው የሚያለማ ላቡን እያጠጣ
በዘፍጥረት ዘመን
ካገሬ ተራሮች መሀፀን የወጣ
ሕዝብማ ወንዝ ነው…
ሰው ነው የናፈቀኝ
ሰው ነው የእምነቴ ዕዳ
ጭፍን የማይጓዝ ጅምላ እማይነዳ
የወንዙን ስሞታ ሰምቶ የተረዳ
የሰውነትን ልክ ካምላኩ የቀዳ
ሰው ነው…ሰው ነው የናፈቀኝ…
ከወንዙ የወጣ ከምንጩ የሚገኝ
ሰው ነው…ሰው ነው የናፈቀኝ
እንደ በትረ ሙሴ
ባህሩን ባይከፍልም ተዓምር ባይሰራ
ምፅአት ላይ ሆኜ
‘’ምፅአቱ ደርሷል!’’ ብሎ እማያስፈራ
ከፍቅር የሚያስታርቅ ከእምነቱ ስፍራ
ከተስፋ እሚያጋባ ደግሞም ከእውነት ጋራ
ሰው ነው…ሰው ነው የናፈቀኝ !
ሕዝብነት ሰለቸኝ…
ወንዝነት ደከመኝ…
አፈሩ መረረኝ ድንጋይ አቆሰለኝ
ከዚህ ጨፍጋጋ አዚም ዙሪት የሚያስቆመኝ
ቂሜን የሚያስረሳ ፍቅር የሚያስተምረኝ
ሰው ነው…ሰው ነው የናፈቀኝ !!!
* * * *
ገጣሚ_ሰለሞን_ሳህለ

ውብ ቀን

ግሩፑን ለማግኘት

@Mtshaf_bicha
ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
አሰተያየት ካላችሁ
@Eyos18 አድርሱን

Join&share
@EyosC1
ማንበብ ባህላችን ይሁን