2024-05-16 14:50:17
ሀገራዊ ምክክሩ ሙስሊሙን ያገለለ የተሳታፊ ልየታ እንደተደረገበት ተገለፀl
በኢትዮጲያ በመጪው ለሚካሄደው ሀገራዊ ምክክር የሙስሊሙ ቁጥር አነሳ በመሆኑ የተሳታፊዎች ልየታ በድጋሚ እንዲካሄድ እና በሙስሊሙ በኩል የቀረቡ አጀንዳዎች በሀገራዊ ምክክሩ እንዲካተቱ የኢትዮጲያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ጥሪ አቀረበ።
…
ጠቅላይ ምክር ቤቱ ባቀረበው ጥያቄ የሙስሊሞች ተሳትፎ በሕዝባችን ቁጥር ልክ መሆን ያለበት በመሆኑ የተሳታፊዎችና የአወያዮች ቁጥር በዚሁ መሠረት በኮሚሽኑ "የአካታችነት መርህ መሠረት ጠ/ም/ቤቱ ያቀረበውን የሕዝበ ሙስሊሙ የምክክር እጀንዳዎች ለጉባኤው ለማሰማት፤ ለማብራራት የሚችሉ ተገቢ ቁጥር ያላቸው ሙስሊም ተወካዮች እንዲካተቱ ይቻል ዘንድ የህዝብ ጥያቄዎች ከፍተኛ እየሆነብን በመምጣቱ ሥብጥሩ በፍትሃዊነት እንደገና እንዲቃኝ ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ የበላይ ጠባቂ ለሆኑት ለፕሮፌሰር መስፍን አርአያ በፃፈው ደብዳቤ ጠይቋል።
…
በኢትዮጵያ የተለያዩ አገራዊ ጉዳዮች ላይ መግባባት ለመፍጠር ይችላል የተባለው የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአዋጅ ተቋቁሞ የተለያዩ ተግባራትን ሲያከናውን መቆየቱ የሚታወስ ሲሆን ኮሚሽኑ ከትግራይ ክልል ውጪ እና ግጭት ባለባቸው የአማራ እና የኦሮሚያ ክልልች አንዳንድ አካባቢዎችን ሳያካትት በ10 ክልሎችን እና የከተማ አስተዳደሮች ለምክክሩ የሚሳተፉ አካላትን ልየታ ቢያካሂድም የሙስሊሙ ቁጥር አነስተኛ መሆኑ ተገልጿል፡፡
…
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ተወካዮች ከሀገራዊ ምክክሩ "3"ኮሚሽነሮች ጋር ውይይት ማድረጋቸው የተገለፀ ሲሆን በባለሙያ በተሰጠ መግለጫ ላይም በተሳታፊና በአወያይ ደረጃ የሙስሊሞችን ተሳትፎ እንዲነገረን ብንጠይቅም ከምክክር ኮሚሽኑ ምላሽ እንዳልተሰጠ በሰጠው መግለጫ ላይ አስታውቋል፡፡
…
ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ውሳኔውን በድጋሚ እንዲያጤነው እና
በኢትዮጲያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አማካኝነት የቀረቡ የመስሊሙ አጃንዳዋች እንዲካተቱ እና ህዝበ ሙስሊሙም በቁጥሩ ልክ ተሳታፊ እንዲሆን ጥሪ ቀርቧል።መረጃወችን ለወዳጄ ዘመድ ሼር ያርጉ!
የቴሌግራም ቻናላችን ከስር በሊንኩ ይቀላቀሉ
https://t.me/+UAKV32q7U2HKzEMf
5.2K viewsedited 11:50