Get Mystery Box with random crypto!

ከአሳሳ እስከ ሮቤ፣ ከኮኮሳ እስከ አዳማ ፣ ከአርሲ እስከ ባሌ፣ እስከ ሸገርና ጎንደር ድረስ ጭምር | "ኡማ ቲቪ " Tv

ከአሳሳ እስከ ሮቤ፣ ከኮኮሳ እስከ አዳማ ፣ ከአርሲ እስከ ባሌ፣ እስከ ሸገርና ጎንደር ድረስ ጭምር ታሪክ አለን ከዚህ ሰው ጋር፡፡
በተለያዩ ከተሞች እየተዘዋወረ በጎዳና ላይ ደዕዋ ሲያደርግ ታውቁታላታችሁ፡፡ ምንም ማንንም የማይፈራ ሙጃሂድ ነው። ስፒከሩ በተዳጋጋሚ ታስሮበት በየፖሊስ ጣቢያው ሲንከራተትም አጋጥሞኛል፡፡

ከልጅነት እስከ ወጣትነትና ጎልማሳነት ምናልባት እስካዛሬዋ እስከመጨረሻዋ የዱንያ ላይ ቀን ድረስ ሐያቱን በሙሉ በደዕዋ አሳልፏል፡፡ አላረፈም። ኢስላምን ለማድረስ ሁሌ እንደተጓዘ ስለማየው ቤት ይገባ ይሆን ብዬ እጠይቃለሁ ብዙ ጊዜ፡፡ ዛሬ ሻሻመኔ ላይ ድንገት ማረፉን ሰማሁ፡፡

ፈቂ ገለቶ አላህ ይዘንልህ፡፡

ሰው በኖረበት ነገር ላይ ይሞታል፤
በሞተበት ነገር ላይም ይቀሰቀሳል፡፡

ደጋግ ባሮችህ ወዳንተ እየመጡ ነው።
አላህ ሆይ!
ዐለይከ ረበና ቢሑስኒልኺታሚ እንላለን ።መረጃወችን ለወዳጄ ዘመድ ሼር ያርጉ!
የቴሌግራም ቻናላችን ከስር በሊንኩ ይቀላቀሉ
https://t.me/+UAKV32q7U2HKzEMf