Get Mystery Box with random crypto!

ከ ሐጅ ቪዛ ውጪ ሐጅ ማድረግ እንደማይፈ ቀድ የሳውዲ የሐጅ ሚኒቴር አስጠነቀቀ። የሳውዲ አ | "ኡማ ቲቪ " Tv

ከ ሐጅ ቪዛ ውጪ ሐጅ ማድረግ እንደማይፈ ቀድ የሳውዲ የሐጅ ሚኒቴር አስጠነቀቀ።

የሳውዲ አረቢያ የሐጅና ዑምራ ሚኒስቴር ፣ ከሐጅ ቪዛ ዉጪ በማንኛውም የቪዛ አይነቶች ሐጅ ማድረግ እንደ ማይፈቀድ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ገለፀ።

የጉብኝት ፣ የቱሪስት ፣ የትራንዚት : የስራና መሰል በሳውዲ አረቢያ የሚሰጡ ቪዛዎችን በመጠቀም ሐጅ ለማድረግ የሚሞክሩ ከዚህ ተግባራቸው እንዲቆጠቡ ከወዲሁ የሚኒስተር መስሪያ ቤቱ አስጠንቅቋል።

ሐጅ ለማድረግ ሳዑዲ አረቢያ ከመገባቱ በፊት የሐጅ ቪዛ ማግኘት የግድ አስፈላጊ መኾኑን የጠቀሰው ሚኒስቴሩ፣ በጉብኝት ቪዛ፣ በሥራ ቪዛ፣ በቱሪስት ቪዛ፣ በትራንዚት እና በመሳሰሉት ቪዛዎች ሳዑዲ አረቢያ በመግባት ሐጅ ማድረግ እንደማይቻል አሳስቧል።

ሚኒስቴሩ አክሎም፣ ሐጅ ማድረግ የሚቻለው ጉዳዩ የሚመለከተው የሳዑዲ አረቢያ ሚኒስቴር በየሀገራቱ የሐጅና ዑምራ ጉዳይ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በመተባበር በሚሰጠው የሐጅ ቪዛ እና፣ እነዚህ ተቋማት በሌሉባቸው ሀገራት ደግሞ "ኑሱክ ሐጅ" በሚሰኘው ፕላትፎርም አማካይነት ብቻ መኾኑን መረዳት ያስፈልጋል ብሏል።

ሐጅ ለማድረግ፣ ሳዑዲ አረቢያ ከመገባቱ በፊት ራሱን የቻለ የሐጅ ቪዛ ማግኘት የግድ አስፈላጊ እንደኾነ የጠቀሰው የሚኒስቴሩ መግለጫ፣ ከሳዑዲ የሐጅና ዑምራ ሚኒስቴር ጋር ግንኙነት ካላቸው የየሀገራቱ የሐጅና ዑምራ ተቋማት ውጪ የሐጅ ቪዛን ማግኘት እንደማይቻል በመግለጽ ምዕመናን ከመታለል እንዲጠነቀቁ አሳስቧል።

"ሐጅ እናስደርጋለን" በሚሉ አጭበርባሪ ኩባንያዎች መታለል ከሚያስከትለው የገንዘብ ኪሳራ በተጨማሪ፣ የጓጉለትን ሐጅ ለማድረግ አለመቻልን በማስከተል ከባድ ሐዘን ላይ ሊጥል እንደሚችል ሚኒስቴሩ አሳስቧል።

የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት።