የሚሽነሪዉ አካል ሙሀመድ ሱሩር ማን ነዉ ? (ክፍል 2 ) ቢስሚላህ ! በቁጥር አንድ እንደ ጀመርኩላችሁ የሚሽነሪዉ አካል ሙሀመድ ሱሩር ቤተሰቦቹ የጁ ዉስጥ እንደ ሆኑ ያወራል ( በርግጥ አንዳቸዉም ቤተሰቡ ነኝ ብሎ የመጣ አላዉቅም ) ሰዉየዉ በአንድ ወቅት መርሳ ከተማ ላይ ለትልቅ እስላማዊ ዝግጅት ስንጓዝ ከፊት ወንበር ጋቢና ላይ ተቀምጧል ታላላቅ ዓሊሞችና ጎደኞቼ ከሓላ ተቀምጠን ከካራቲስትነት ከፍ ብሎ በሆነ ጦርነት ( ስሙን ረሳሁት ሀገር ዉስጥ በተደረገ ) ላይ ከሄሊኮብተር ሲወርድ እንደተጎዳ አገግሞ እንደ ዳነ ያወራል ። ይህ ሰዉ በማበረሰብ ዘንድ ተቀባይነት አገኘ የቁርአን ሂፍዝ ማእከሉ አድራጊ ፈጣሪ ሆነ ሚስትም አገባ ትንሽ ቆይቶ ሀኪም ነኝ የህክምና ት/ት መማር አለባችሁ ብሎ ከመርከዝ ልጆች አምስት ሰዉ መርጦ በጊዜዉ እኔ አብዱራህማን ሱልጧን ዶ/ር አህመድ ኑርየ ኢንጂነር ሙሀመድ ጀዉሀር ( አሏህ ይማረዉ ሁላችሁም ዱዓ አድርጉለት ) ሌሎች ሁለት ወንድሞቼ ረሳሃቸዉ ሁነን ለአንድ ሳምንት መርፌ እንዴት እንሚሰጥ አስተማረን እኔም በሳምንት የመርከዙ ሀኪም ሆኜ እርፍ !። በጊዜዉ ለህክምና ብዙ ትልልቅ ሰዎች ይመጡ ነበር ቪ B2 ወግቶ በጊዜዉ የማይታመን ብር ነበር የሚጠይቀዉ ለምን የሚለዉም አልነበረም ። ሚስት የሓላ ሓላ ስቃዪ በዛ ከአንድ የዲን መምህር ነኝ ከሚል ሰዉ የማይጠበቁ ነገሮችን ስታይ ለማን ትናገር ማንስ ያምናታል ። የመርከዝ ልጆችም ለሁለት መከፈል ጀመሩ የተለያዩ ወንጀሎችን ሲፈፅም ያዮትንና የጠረጠሩትን ልጆች የኢማን ድክመት አለባቸዉ ፡ ጅሀድ ይጠላሉ የተለያዮ ስም እየለጠፈ የመርከዙ ልጆችን ከፋፈላቸዉ በመሀባ እንባ ይራጩ የነበሩ ወንድማማቾች ተኮራረፉ ። ባጭሩ የወልዲያ ሰዉ ዳዒ አለመሆኑን እየተረዳ ይመስላል ስለዚህ ክትትል ጀምሯል ። የሚገርሙ ታሪኮች ይቀጥላሉ ወልዲያ የጀመዓዉና የሚስቱ ታሪክ ከቆቦ እስከ ኮምቦልቻ …..። Abdurahman Sultan 6.9K viewsedited 16:02