Get Mystery Box with random crypto!

ᎷUᏚᎯᏰ™ Islamic Page

የቴሌግራም ቻናል አርማ eslamic_page_musab99 — ᎷUᏚᎯᏰ™ Islamic Page
የቴሌግራም ቻናል አርማ eslamic_page_musab99 — ᎷUᏚᎯᏰ™ Islamic Page
የሰርጥ አድራሻ: @eslamic_page_musab99
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.46K
የሰርጥ መግለጫ

👌ሁሌም ቢሆን ለዲንህ ትልቁን ቦታህን ስጥ!
አንብብ ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል።
👌ያን ደግሞ በተግባር አሳይ።
«አላህ መልካም ነገርን የፈለገለት ሰው በዲን ላይ ጥልቅ ግንዛቤ እንዲኖረው ያደርገዋል።» ነቢዩﷺ
Please don't leave, tell us the mistake
#4_any comment & promo:- @Al_Musab99

Ratings & Reviews

5.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-11-24 07:54:04
ማለዳ

#አጭር_ፅሁፍ
         
#ግዙፍ_መልዕክት__!!
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
#ስታለቅስ_በደስታ_ስቀዋል
#በፈገግታ_እጂግ_ደምቀዋል
#ሲያለቅሱ_እንድትስቅ_ስራ
#በስራህ_ውጤት_እንድትኮራ
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ከእናትህ ሆድ ስትወጣ እያለቀስክ ነው የወጣኸው።ሰዎቹ ግን ዙሪያህን ከበው በደስታ እየሳቁ ነበር።

   ሞተህ በመሬት ሆድ ስትቀበር ደግሞ ዙሪያህን ከበው በሀዘን ያለቅሳሉ። አንተ ግን የዛች ቀን በደስታ ለመሳቅ የሚያስችልህን መልካም ስራ ሰርተህ ሙት።

فاجهادي يا نفسي أن تكوني إذا بكوا في يوم موتك ضاحكاً مسرورا

@Islamic_direction
242 views ⓃⓔⓑⓊ , 04:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-24 07:54:04
የኔ الله

የኔ አላህ ሰሚዕ ነው፤ ያልተናገርነውን፤ ለመናገር ያሰብነውን የሚሰማ፤ ሰፍፍፍ ብሎ የሚያዳምጠን፤ ባሪያዬ ምን ጠየቀኝ ብሎ የሚጓጓ፤ እህ የሚለን! እገሌ ጉዳዩን አውጉቶኝ ነበር እጥፍ ድርብ አድርጌ ላንበሽብሸው የሚለን! አይ የኔ አላህ! የሱ ባህሪ እኮ የሚገርም ነው።

አንዳንዴ እራሴን እወቅሳለሁ፤ ሀዘን ሲገባኝ ተቀዳሚ ስሞታዬን የማቀርበው ለጌታዬ ሳይሆን ይቀራል፤ ቅርብ ጓደኞቼን አስቀድማለሁ፤ ቀድሞ መስማት ያለበትን ረስቼ ለቀጣዬቹ አሰሙታለሁ።

ጌታዬ ሰልቺ አይደለም፤ ቀኑን ሙሉ ብናለቅስበት ሳይሰለች ይሰማናል። ሁሉንም ነገር እንጠይቀው ይሰጠናል። 'እቺን ትንሽ ነገርማ አላህን መጠየቅ አፍራለሁ' አትበል! እሱ በየትኛውም ጉዳይ እንድታወጋው በጉጉት እየጠበቀህ ነውና! ለእሱ ምንም ብትነግረው አያሳፍርህምና!

አላህዬ ሀዲሰል ቁድሲይ ላይ ልብ በሚሰረስር ሁኔታ እንዲህ ይላል:
"የአደም ልጅ ሆይ! ከምንም ነገር ፈጠርኩህና አስገኘሁህ፤ መስሚያ፣ ማያ፣ልቦናና ህሊና ሰጠሁህ። እኔ አስታውስሃለሁ አንተ ትረሳኛለህ። እኔ ካንተ አፍራለሁ አንተ ከኔ አታፍርም። በሬን አንኳኩቶ ያልከፈትኩለት ማን አለ? ለምኖኝ ያልሰጠሁትስ ማን አለ? ስስታም ሆኜ ነው እንዴ ባሪያዬ በኔ የሚሰስተው?" ይለናል

ቃላቶቹ አይከብዱም? ሚዛናቸው ከባድ ነው፤ ላስተነተናቸው ጠጣር ምንነት አላቸው፤ ለተረዳቸው ወደ አላህ ለመሮጥ ሰከንዶችን የማይጠይቁ ናቸው!

አያችሁ አስ-ሰሚዕ የኛን ስሞታ ለመስማትና ለመቀበል ምን ያክል ጉጉ እንደሆነ? ባሪያው እጁን ዘርግቶ ሲለምነው በባዶ መመለስን የሚያፍር አምላክ! ሱብሃነላህ ልዕልናህ!

وَاللَّهُ يَسْمَعُ تَحَاوُرَكُمَا ۚ إِنَّ اللَّهَ سَمِيعٌ بَصِيرٌ

አላህም (በንግግር) መመላለሳችሁን ይሰማል፡፡ አላህ ሰሚ ተመልካች ነውና፡፡"
237 views ⓃⓔⓑⓊ , 04:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-20 16:37:28
ሁሌም ምኞትህን የአላህ ውዴታ ተመኝ
ወደርሱም ቅረብ ‥

እሱ ከወደደህ ሁሉም ነገር ይወድሃል...
ነገርህ ሁሉ ያምርልሃል ኪሳራ የለለው ጉዞ የአላህን ውዴታን ፈልጎ

እዚህ ምድር ላይ የአላህን ውዴታ ከማግኘት ውጪ የእውነት በሀሴት የሚሞላ
ምን አለ!? ምንም ቢላህ

ነብዩ ሙሳም ለጌታቸው እንዲህ ይላሉ...
وَعَجِلْتُ إِلَيْكَ رَبِّ لِتَرْضَىٰ
"ጌታዬ ሆይ! ትወድልንም ዘንድ ወደ አንተ ቸኮልኩ» አለ፡፡"
[ሱረቱ ጧሃ:84]

@Islamic_direction
331 views ⓃⓔⓑⓊ , 13:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-20 16:37:28 ላስታውስሽ እህቴ (ፈዘኪር)

ቢስሚላሂ ብዬ ልጀምር በስሙ
ተወዳጅ ነውና በኸይር ነገር ላይ ስሙን ማስቀደሙ

ላስታውስሽ እህቴ !
ላስታውስሽ እህቴ በትንሹም ቢሆን በቻልኩት ቀለሜ
መተዋወሱማ ብዙው ይጎድለናል አልጨርሰው ባቅሜ
ፈዘኪርም ብሏል ጀባሩ ጌታችን በቅዱስ ቁርአኑ
መተመተዋወሳችን ለኛ ለሙስሊሞች ጠቃሚ መሆኑ

ላስታውስሽ እህቴ !
ላስታውስሽ እህቴ በትንሹም ቢሆን
ደዋይ የበዛብሽ ስልክሽ ቢዚ እስኪሆን
የኢስላምን ባህር ያልገባሽ እንደሆን
ላ ተቅረቡ ዚና ን ዘንግተሽው ከሆን
ላስታውስሽ እህቴ በትንሹም ቢሆን
ወላሂ አይጠቅምሽም ተይ እንደዚ መሆን

በረራ ማብዛትሽ ሰውን ተደብቀሽ
የአላህን ትእዛዝ በጭራሽ እረስተሽ
ሊመክሩሽ ሲመጡም ምን አገባው ብለሽ
ፈዘኪር ማለቱን ከቶውን ዘንግተሽ
ሸይጧን እና ስሜት ከተቆጣጠሩሽ
ከወንድ ጋር መጃጃል አራዳነት መስሎሽ
የነቢዩን ሱና ፋራነት ነው ብለሽp
ቁርአን አሽቀንጥረሽ ስልክሽን ታቅፈሽ
ለሙስሊሟ እህትሽ ሰላምታ አርቀሽ ፈገግታንም ነፍገሽ
መስጊዱንም ተውሽው መንገዱም እራቀሽ
አዱንያም አታላሽ ተረታ አኼራሽ

እናም እህት አለም ላስታውስሽ ውዲቷ በትንሹም ቢሆን
ለዚያ ለውብ ሀገር ለ አኼራ ቤትሽ ምን ሰንቀሽ ይሆን ?
ካዲያ እስከመቼ ነው እንዲ የመሆንሽ
ተመሳሳይ ቦታ ሁል ጊዜ መውደቅሽ
ይቅርብሽ እህቴ አድምጪኝ ልምከርሽ
GC እንኳን ብትሆኚ ሲንየር ወይም ፍረሽ
ደዋዩ ቢበዛም እውነት እንዳይመስልሽ
ለትዳር ለኒካህ አንዱም አያስብሽ
መሀላ ቢያበዛ ቃልም ቢገባልሽ
አትዘንጊው እህቴ ጊቢ ውስጥ እንዳለሽ

ከእናት ከአባትሽ ከወንድም እርቀሽ
ክብርሽን ጠባቂ አንቺው ለራስሽ ነሽ
በሀላሉ መንገድ እሱ እስኪመጣ
ለምን ትሰሪያለሽ ቀብር የሚያስቀጣ ?

ተውሂድን ልበሽው መብረርን አቁመሽ
ለሰው ሰበብ ሁኚ ለራስሽ ቶብተሽ
በነቢዩ ሱና ጉዞሽን አድርገሽ
በዲንሽ ጠንካራ ጎበዝ ልጅም ከሆንሽ
ጅላጅል ባለጌ ፈፅሞ አይደርስብሽ


ኢስቲቃማን ይስጥሽ በኸይር ስራሽ ላይ እንዲያጠነክርሽ ጌታሽን ጠይቂው ይሰማሻል ከላይ
ጌታሽ አል_ከሪም ነው ለለመኑት ባሮች አይደለም ከልካይ
ውዴታህን በይው መገን በስሞችህ ከደጅህ አልጥፋ
በጧትም በማታ አመሰግንህ ዘንድ በሱጁድ ልደፋ
እፊትህ የምቆም በስራዬ ሳይሆን ነው በእዝነትህ ተስፋ

እናማ ኡኽታዬ !
እናማ ኡኽታዬ ተምረሻል ብዙ ካለፈው ስህተትሽ
ትናንትና ሄደ እርሺውና እሱን ወደ አላህ ተመለሽ
ያለፈው ተይው ጌታሽ መሀሪ ነው ሁል ጊዜ አስታውሺ
ይቅር በለኝ ብለሽ መንገድሽ እንዲያምር ወደፊት ገስግሺ
ቂርአትና ደርሱን ሁሉንም ሞክሪው ብዙን ይጠቅምሻል
ዛሬሽን አርክቶ ለነገ አኼራሽ ዝግጁ ያደርግሻል
ቀራሁትም አትበይ ኢልም አይጠገብም
ብትደግሚው ትርፉ እንጂ ጉዳቱ አይታየኝም
ዲንሽን ለማወቅ ጉጉቱ ይኑርሽ ከሁሉ አስቀድሚው
ባወቅሽ ቁጥር ነው ትልቁ ጌታሽን ምታመሰግኚው
ጌታሽን ካወቅሽው እርሱ ከወደደሽ ትርፍሽ ጣራ ነካ
እንዲህ አይነት ስኬት ይህን መሳይ ደስታ ከምን ጋር ሊለካ

ለሙስሊሟም እህት ሰላምታ አቅርቢላት
ፈገግታን የሚሰጥ ከቶ ካንቺ ሌላ ወዴት እህት አላት
የረሱላችንም አስተምህሮታቸው ትእዘዝ አለበት
አፍሹ ሰላም አሉን በመሀከላችን ሰላምታን ለማብዛት

እናም እህት አለም አንቂያት እህትሽን አውጫት ከጨለማ
በአንድ ላይ ደስ ይላል እየተጋገዙ የተውሂዱ ማማ
እህትሽ አትድከም አንቺም አትስነፊ
ገና በለጋ እድሜሽ ለአኼራሽ ልፊ

ተነሽ! እህት አለም የሱናዋ ወጣት
ነፍስሽን ከመጥፎ አሁኑኑ አርቂያት
ወጥተሽ ከጨለማ በተውሂድ አድምቂያት !
ወጥተሽ ከጨለማ በተውሂድ አድምቂያት !

#ተንቢህ
የድሬ ደዋ ዩኒቨርሲቲ የሙስሊም ሴት ተማሪዎች ፕሮግራም
#Nebiyat_bint_H/Muhajir
11/3/15 E.C

@Islamic_direction
@Islamic_direction
239 views ⓃⓔⓑⓊ , 13:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-20 16:37:28
አላህ እኛ ወደርሱ ሄደን ተውበትን ከማቅረባችን
በፊት ምህረተ ሰፊው ጌታችን እዝነቱን አቅርቦልና
ያማረ ጥሪ ከ ውዱ ጌታችን ምህረቱን ፈላጊ
ለሆነ ሁሉ...


{۞ قُلْ يَا عِبَادِيَ الَّذِينَ أَسْرَفُوا عَلَىٰ أَنفُسِهِمْ لَا تَقْنَطُوا مِن رَّحْمَةِ اللَّهِ ۚ إِنَّ اللَّهَ يَغْفِرُ الذُّنُوبَ جَمِيعًا ۚ إِنَّهُ هُوَ الْغَفُورُ الرَّحِيمُ}
"በላቸው «እናንተ በነፍሶቻችሁ ላይ ድንበር ያለፋችሁ ባሮቼ ሆይ! ከአላህ እዝነት ተስፋ አትቁረጡ፡፡ አላህ ኃጢኣቶችን በመላ ይምራልና፡፡ እነሆ እርሱ መሓሪው አዛኙ ነውና፡፡"
[ሱረቱ ዙመር:53]
ምንም እንኳን ወደ ጌታችን ወንጀል
ብንልክም እርሱ ወደኛ ምህረትን ያዘንባል
ራህማኔ እወድሃለሁ

@Islamic_direction
220 views ⓃⓔⓑⓊ , 13:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-17 19:29:21
ሰለዋት
317 views ⓃⓔⓑⓊ , 16:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-17 19:29:21 አብረን ወደ ጀነት

#ዛሬ #ከምታይዋቸው #ውድና #ምርጥ #ቴክስት #አንዱ #ነው።

➊ ☞ #ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) አሉ በኔ ላይ በየቀኑ 1000 ሰለዋት የሚያደርግ ሰው
በጀነት ሳይበሸር አይሞትም።

➋ ☞ #ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) አሉ በኔ ላይ በየቀኑ 100 ሰለዋት የሚያደርግ አላህ
100 ሀጃውን ያወጣለታል 70 በጀነት 30 በዱንያ።

➌ ☞#ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) አሉ ሲነጋ 10 ሲመሽ 10 ሰለዋት ያደረገ የኔን ሸፈኣ
የቂያማ ቀን ያገኛል።

➍ ☞#ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) አሉ በኔ ላይ አንድ ሰለዋትን ያወረደ ሰው አላህ በሱ ላይ 10 ሰለዋት
ያወርድበታል 10 ሀጥያት ይሰርዝለታል 10 ደረጃ ከፍ ያረገዋል።

➎ ☞ #ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) አሉ ማንም ሰው ሰላም አይለኝ ም አላህ ሩሄን መልሶልኝ ሰላምታውን ብመልስለት እንጂ።

➏☞#ለኔ የመጀመርያ ሰዎቼ የቂየማ ቀን እነዚያ በኔላይ በብዛት ሰለዋትን ያደረጉብኝ ናቸው።

ታድያ ምን እየጠበቅን ነው እኛም ሰለዋት በማብዛት ይሄንን መልክትም ለረሱት ወዳጅ ዘመዶቻችን በፍጥነት #ሼር በማድረግ ሰደቀተል ጃርያን በማሰብ ብናስተላልፍ የቂያማ ቀን ያላሰብነው ስንት ሀሰናት ይጠብቀናል ኢንሻ አላህ።

@Islamic_direction
269 views ⓃⓔⓑⓊ , 16:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-17 00:08:48
አላህ ከአንድ ባሪያው ላይ የከፋውን ችግር ሊያስወግድለትና በጣም ሊያስደስተው ከፊል
ችግሮችንና ጭንቆችን ይቀድርበታል‥

{وَأَصْبَحَ فُؤَادُ أُمِّ مُوسَىٰ فَارِغًا ۖ إِنْ كَادَتْ لَتُبْدِي بِهِ لَوْلَا أَنْ رَبَطْنَا عَلَىٰ قَلْبِهَا لِتَكُونَ مِنَ الْمُؤْمِنِينَ}
" የሙሳም እናት ልብ ባዶ ሆነ ፡፡ ከምእምናን ትሆን ዘንድ በልቧ ላይ ባላጠነከርን ኖሮ ልትገልፀው ቀርባ ነበር ፡፡"
[ሱረቱል ቀሷስ:10]

የነቢዩላህ ሙሳ እናት ልጇን ስታጣ
በጣሙን አዝና ነበር‥ ልጇን ብትይዝ ኖሮ
አሁን ካዘነችው ይበልጥ በጣም ታዝን ነበር
ነገር ግን ሰብር አደረገች ከዚህም ሰብርና ሀዘን በኃላ አላህ አይኗ እንዲረጋ ልጇን መለሰላት...


{فَرَدَدْنَاهُ إِلَىٰ أُمِّهِ كَيْ تَقَرَّ عَيْنُهَا وَلَا تَحْزَنَ وَلِتَعْلَمَ أَنَّ وَعْدَ اللَّهِ حَقٌّ وَلَٰكِنَّ أَكْثَرَهُمْ لَا يَعْلَمُونَ}
"ወደእናቱም ዓይንዋ እንድትረጋ፣ እንዳታዝንም፣ የአላህም የተስፋ ቃል እርግጥ መሆኑን እንድታውቅ መለስነው፡፡ ግን አብዛኞቻቸው አያውቁም፡፡"
[ሱረቱል ቀሷስ:13]
በህይወትህ ላይ ከአቅሜ በላይ
ሆኑብኝ የምትላቸው ችግሮች
ሊመጡብህ ይችላሉ
ከዛ ችግር በኋላ ትልቅ ደስታ
እንደሚጠብቅህ እርግጠኛ ሁን
በአላህ ላይ ጥርጣሬህንም አሳምር
ትእግስት እያደረግክም ተጠባበቅ አብሽር
አላህኮ ለማንም አልሰጠህም ለማንም አልተወህም
ጉዳይህን ሁሉ እሱ ነው ሚፈፅምልህ

@Islamic_direction
256 views ⓃⓔⓑⓊ , 21:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-17 00:08:48 #ትንሽ_ትዕግስት
.
.
.
.
ወተቱ ለረጅም ጊዜ ተቀምጦ "የሚጠጣኝ ጠፋ እኮ!" ብሎ ተስፋ ሊቆርጥ ሲል አንጀት የሚያርስ እርጎ ሆነ። ነገሮች በፈለከው መንገድ አልሄዱልኝም ብለህ የጀመርከውን እንዳታቆም! ወዳጄ ልብህን የሚያሞቅ እርካታ ከፈለክ ትንሽ ታገስ።

ትዕግስተኛ መሆን ማለት አንድን ነገር መተው፣ ማቆም እየቻልክ ወይ ቸኩለህ መወሰን እየቻልክ ትልቁን ነገር አስበህ ራስህን አሳምነህ አሁን ዋጋ ከፍለህ ነገ በብዙ እጥፍ ማትረፍ ነው።

#Be_Patient...

#ሸግዬ_ለይል

@Islamic_direction
197 views ⓃⓔⓑⓊ , 21:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-17 00:08:48
اللهم إجعل القرآن ربيع قلبي ونور صدري وجلاء حزني وذهاب همي.

➲ቁርአን የልብ መድሀኒት የሩህ ምግብ ነው!

►ህይወት ከቁርአን ጋር ጣፍጭ ነች
اللهم يَا مُقَلِّبَ الْقُلُوبِ ثَبِّتْ قَلْبِي عَلَى دِينِكَ


@Quranul_kerim
183 views ⓃⓔⓑⓊ , 21:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ