Get Mystery Box with random crypto!

ላስታውስሽ እህቴ (ፈዘኪር) ቢስሚላሂ ብዬ ልጀምር በስሙ ተወዳጅ ነውና በኸይር ነገር ላይ ስሙን | ᎷUᏚᎯᏰ™ Islamic Page

ላስታውስሽ እህቴ (ፈዘኪር)

ቢስሚላሂ ብዬ ልጀምር በስሙ
ተወዳጅ ነውና በኸይር ነገር ላይ ስሙን ማስቀደሙ

ላስታውስሽ እህቴ !
ላስታውስሽ እህቴ በትንሹም ቢሆን በቻልኩት ቀለሜ
መተዋወሱማ ብዙው ይጎድለናል አልጨርሰው ባቅሜ
ፈዘኪርም ብሏል ጀባሩ ጌታችን በቅዱስ ቁርአኑ
መተመተዋወሳችን ለኛ ለሙስሊሞች ጠቃሚ መሆኑ

ላስታውስሽ እህቴ !
ላስታውስሽ እህቴ በትንሹም ቢሆን
ደዋይ የበዛብሽ ስልክሽ ቢዚ እስኪሆን
የኢስላምን ባህር ያልገባሽ እንደሆን
ላ ተቅረቡ ዚና ን ዘንግተሽው ከሆን
ላስታውስሽ እህቴ በትንሹም ቢሆን
ወላሂ አይጠቅምሽም ተይ እንደዚ መሆን

በረራ ማብዛትሽ ሰውን ተደብቀሽ
የአላህን ትእዛዝ በጭራሽ እረስተሽ
ሊመክሩሽ ሲመጡም ምን አገባው ብለሽ
ፈዘኪር ማለቱን ከቶውን ዘንግተሽ
ሸይጧን እና ስሜት ከተቆጣጠሩሽ
ከወንድ ጋር መጃጃል አራዳነት መስሎሽ
የነቢዩን ሱና ፋራነት ነው ብለሽp
ቁርአን አሽቀንጥረሽ ስልክሽን ታቅፈሽ
ለሙስሊሟ እህትሽ ሰላምታ አርቀሽ ፈገግታንም ነፍገሽ
መስጊዱንም ተውሽው መንገዱም እራቀሽ
አዱንያም አታላሽ ተረታ አኼራሽ

እናም እህት አለም ላስታውስሽ ውዲቷ በትንሹም ቢሆን
ለዚያ ለውብ ሀገር ለ አኼራ ቤትሽ ምን ሰንቀሽ ይሆን ?
ካዲያ እስከመቼ ነው እንዲ የመሆንሽ
ተመሳሳይ ቦታ ሁል ጊዜ መውደቅሽ
ይቅርብሽ እህቴ አድምጪኝ ልምከርሽ
GC እንኳን ብትሆኚ ሲንየር ወይም ፍረሽ
ደዋዩ ቢበዛም እውነት እንዳይመስልሽ
ለትዳር ለኒካህ አንዱም አያስብሽ
መሀላ ቢያበዛ ቃልም ቢገባልሽ
አትዘንጊው እህቴ ጊቢ ውስጥ እንዳለሽ

ከእናት ከአባትሽ ከወንድም እርቀሽ
ክብርሽን ጠባቂ አንቺው ለራስሽ ነሽ
በሀላሉ መንገድ እሱ እስኪመጣ
ለምን ትሰሪያለሽ ቀብር የሚያስቀጣ ?

ተውሂድን ልበሽው መብረርን አቁመሽ
ለሰው ሰበብ ሁኚ ለራስሽ ቶብተሽ
በነቢዩ ሱና ጉዞሽን አድርገሽ
በዲንሽ ጠንካራ ጎበዝ ልጅም ከሆንሽ
ጅላጅል ባለጌ ፈፅሞ አይደርስብሽ


ኢስቲቃማን ይስጥሽ በኸይር ስራሽ ላይ እንዲያጠነክርሽ ጌታሽን ጠይቂው ይሰማሻል ከላይ
ጌታሽ አል_ከሪም ነው ለለመኑት ባሮች አይደለም ከልካይ
ውዴታህን በይው መገን በስሞችህ ከደጅህ አልጥፋ
በጧትም በማታ አመሰግንህ ዘንድ በሱጁድ ልደፋ
እፊትህ የምቆም በስራዬ ሳይሆን ነው በእዝነትህ ተስፋ

እናማ ኡኽታዬ !
እናማ ኡኽታዬ ተምረሻል ብዙ ካለፈው ስህተትሽ
ትናንትና ሄደ እርሺውና እሱን ወደ አላህ ተመለሽ
ያለፈው ተይው ጌታሽ መሀሪ ነው ሁል ጊዜ አስታውሺ
ይቅር በለኝ ብለሽ መንገድሽ እንዲያምር ወደፊት ገስግሺ
ቂርአትና ደርሱን ሁሉንም ሞክሪው ብዙን ይጠቅምሻል
ዛሬሽን አርክቶ ለነገ አኼራሽ ዝግጁ ያደርግሻል
ቀራሁትም አትበይ ኢልም አይጠገብም
ብትደግሚው ትርፉ እንጂ ጉዳቱ አይታየኝም
ዲንሽን ለማወቅ ጉጉቱ ይኑርሽ ከሁሉ አስቀድሚው
ባወቅሽ ቁጥር ነው ትልቁ ጌታሽን ምታመሰግኚው
ጌታሽን ካወቅሽው እርሱ ከወደደሽ ትርፍሽ ጣራ ነካ
እንዲህ አይነት ስኬት ይህን መሳይ ደስታ ከምን ጋር ሊለካ

ለሙስሊሟም እህት ሰላምታ አቅርቢላት
ፈገግታን የሚሰጥ ከቶ ካንቺ ሌላ ወዴት እህት አላት
የረሱላችንም አስተምህሮታቸው ትእዘዝ አለበት
አፍሹ ሰላም አሉን በመሀከላችን ሰላምታን ለማብዛት

እናም እህት አለም አንቂያት እህትሽን አውጫት ከጨለማ
በአንድ ላይ ደስ ይላል እየተጋገዙ የተውሂዱ ማማ
እህትሽ አትድከም አንቺም አትስነፊ
ገና በለጋ እድሜሽ ለአኼራሽ ልፊ

ተነሽ! እህት አለም የሱናዋ ወጣት
ነፍስሽን ከመጥፎ አሁኑኑ አርቂያት
ወጥተሽ ከጨለማ በተውሂድ አድምቂያት !
ወጥተሽ ከጨለማ በተውሂድ አድምቂያት !

#ተንቢህ
የድሬ ደዋ ዩኒቨርሲቲ የሙስሊም ሴት ተማሪዎች ፕሮግራም
#Nebiyat_bint_H/Muhajir
11/3/15 E.C

@Islamic_direction
@Islamic_direction