Get Mystery Box with random crypto!

እንደመሠለን🥴😂❤️

የቴሌግራም ቻናል አርማ endemeselen — እንደመሠለን🥴😂❤️
የቴሌግራም ቻናል አርማ endemeselen — እንደመሠለን🥴😂❤️
የሰርጥ አድራሻ: @endemeselen
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 119
የሰርጥ መግለጫ

ለምን ጭንቀት

Ratings & Reviews

1.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

3


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-04-29 06:57:38 ❝❝❝❝❝አይንሽ ይጥፋ❞❞❞❞
እኔን ባየሽበት ያየሽ እንደው ሌላ
ተዋደን ተፋቅረን ከምንጠላላ
ግድ የለም አለሜ...
አሜን በይ ተቀበይ እርግማኔ ይስራ
አይኖችሽ ይጥፉና እኔ አንቺን ልምራ።
192 views𝖘𝖊𝖑𝖎𝖐 𝖇𝖎𝖓, 03:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-29 22:24:55 በምንም ይጀመር

@endemeselen

@mawekletesanew


ላገኛት ነው በቃ በጣም ደስ ብሎኛል
ፍቅሯ ብዙ ዘመን በብዙ ጎድቶኛል
ጎድቶኛል ያንሰዋል እንደውም ገሎኛል
ገሎኛልም ያንሳል
ግን የለም ሌላ ቃል

እኔኮ ....

ምክንያት ሳፈላልግ ካየዃት ጀምሮ
በድሀው ልጀምር ወይስ በሀብታም ኑሮ
አይ እንደውም እሱን ትቼው
የሀብት ምኞቴን
የደሀ ህይወቴን
ሁሉን እረስቼው
ድንገት እንደ ሚወድቅ እንደ ህመምተኛ
ሳገኛት ሳገኛት ከስሯ ልተኛ
ወይስ አማኝ ልሁን
ካህን ወይ ዲያቆን
ይሄኛውም አይሆን
ይከብዳል ለመሆን
እያልኩኝ ሳወጣ ሳወርድ
ሀሳቤን በሀሳቤ ስንድ
ለሷ ብዙ አረኩኝ
ብዙም ተጎዳሁኝ
ይሄን ብቻ አደለም ሌላም አድርጊያለው
አብይ ፆም ፆሜ ጁማም ሰግጃለው

እኔኮ ስለሷ

እየሩስ አሌም ሄድኩ
አረብ አገር ደረስኩ

እኔ ለሷ ሲባል

ጨርቄን ጥዬ አበድኩ
ከዛም ጤነኛ ሆንኩ
ጨርቄንም ሰበሰብኩ

እኔ እሷን እያሰብኩ

በምዕራብ ወጥቼ በምስራቅ ተመለስኩ

እኔማ ስለሷ

መንዙማ ከፍቼ ከበሮ ደበደብኩ
አሀዱ ሳይባል ወደ መስጂድ ዘለኩ
ሱባኤ ገብቼ አምላኬን አማረርኩ
እኔ በሷ ምክንያት ብዙ ብዙ ፈፀምኩ
አሁን ጊዜው ደርሶ ይህ ሁሉ ተቆጥሮ
ደስታ መጣ እኔጋ ሀዘኑ ተባሮ
አቤት የኔ ኑሮ
በግጭት ጅማሮ
አወይ ግጭት
አትገርምም ግን ግጭት
ጎሳን ከጎሳ ጋር
ሀገርን ከሀገር
ባጃጅ ከትራከር
አንድን ግለሰብ ከአንድ ግለሰብ
እንዳላጋደለች በሚገራርም ፀብ
ግጭትም አንሳ ይኸው
እጇን በጄ ገጨው
መነሻም አገኘው

@mawekletesanew

@endemeselen
235 viewsЄямι Иєgи, 19:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-28 08:17:10 የቀብርሽ ዕለት
ከአገር ዳር እስከ ዳር፣
ቆሞ ከሚያለቅሰው ዘመድ አዝማድ ጎራ፤
ፎቶ የታቀፉ፣
ደካማ አዛውንት ከቆሙበት ስፍራ፤
ለአንቺ እንደሆነ ሳስብ፣
የተከማመረው ድንጋይና አፈሩ፤
ቄሱም በቃላቸው በንግርቱ መሐል፣
"አዳም የተበጀው ከዚህ አፈር ነው" ሲሉ፤
ቀፈፈኝ ገላዬ ቢቀፈኝ አካሌ፣
ተመኘሁ በልቤ በሞትሽ ወላፈን ገላዬ እንዲቀጣ፤
አዳም ቀድሟልና ትካት በምፅአቱ፣
ቀድሞ እርሱ ይቀበር ቀድሞ ስለመጣ።
❴ከጎኔ ቅበሯት❵
190 views𝖘𝖊𝖑𝖎𝖐 𝖇𝖎𝖓, 05:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-07 19:04:07 ​​​​​ ​​ ┈┈••◉❖◉●••┈
እውነት ሄድሽ በቃ?
:¨·....................:¨·.



ምትወጃት ጨረቃ
ከሰማይ ሰሌዳ ሳትጠፋ ጠልቃ
ነብሴም እንቺን ለምዳ፣
ልክ እንደ ህፃን ልጅ ሳይበቃት ፈንድቃ
እውነት ሄድሽ በቃ?
ለቅሶ ይሰማኛል፣
የሚያነቡ ሰዎች ከፊቴ አያለሁ
አፈር ቡንን ይላል፣
መቃብር ሲቆፈር እመለከታለሁ
ምን እያረጉ ነው?
ምን እንደሚያደርጉ እኔ ምን አውቃለሁ
ድንዝዝ ብያለሁ!
መደንዝዝ ታውቂያለሽ፣
ሳይነቃነቁ ዝም ብሎ መገተር
ምንም ስሜት አልባ፣
በጥፊ ቢመታ ወይም ቢገፈተር
ደንዝዝ ብያለሁ አዎ ልክ እንደዛ
እንዲሁ እንደ ወዛ!
ፎቶሽን የያዙ፣
አሮጊት ሴትዮ ደረት ይመታሉ
እንዳንዶች በዕንባ፣
እህህ እያሉ ይንከራተታሉ
የማልቀስ
የማንባት
እነዚህ ስሜቶች እኔ ጋ የታሉ?
ፍርጃ
ፍዝዝ ብያለሁ ያላንዳች እርምጃ
ድንዝዝ ብያለሁ የነካኝን እንጃ!
በቆምኩበት ቦታ፣
እንደተገተርኩኝ ዕንባ ሳላወጣ
የለቅሶ የዋይታ፣
አሰቃቂ ድምፀት እየተጠጋኝ መጣ!
ድንገት ብንን አልኩኝ፣
ይደልቅ ጀመረ ልቤ በሀይል መምታት
ለሁለት ተከፈልኩኝ አነቃኝ ማመንታት!
በዚህ...፣
ዘላለማዊ ናት አትሞትም እሷ
በዚያ...፣
እመን
እመን
እመን
ከንግዲህ አትመጣም አፈር ሆኗል ልብሷ!
በጥርጥር መሀል
በማመንም መሀል ልቤ እየዋለለ
ዕንባዬ ጠብ አለ!
ጉም ዙሪያዬን ሞላው ጨለማ ከለለኝ
መሄድ መሞትሽን አመንኩኝ መሰለኝ!
ለራሴ አዘንኩኝ ባዘን ሆዴ ባባ
አምርሬ አለቀስሁ ታጠብኩኝ በዕንባ!
አይመስለኝም ነበር
በግዜ ምትከፍቺው የማቃብርን በር!
መውደድ ሳይዳብሰኝ ፍቅር ሳይነካካኝ
አልቀርብሽም ነበር፣
መሆንሽን ባውቀው እዚህ ድረስ ጨካኝ::
ላትመጪ ነገር
ላትመለሽ ነገር
ወዴት ሄጄ ልበድ፣
የልቤን ትኩሳት ምን ብዬ ልናገር?
ምትወጃት ጨረቃ
ከሰማይ ሰሌዳ ሳትጠፋ ጠልቃ
ነብሴም እንቺን ለምዳ፣
ልክ እንደ ህፃን ልጅ ሳይበቃት ፈንድቃ
እውነት ሄድሽ በቃ?

@endemeselen
206 viewsЄямι Иєgи, 16:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-08 00:24:51
253 viewsPIHALO , 21:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-02 08:10:13 @endemeselen
@endemeselen

ሰው ማለት እንዲ ነው

@endemeselen

በብዙ ህይወት ውስጥ በአንድ ስሜት ጉዞ
ሲፈልግ ጥላቻ አልያ ፍቅርን ይዞ
መጓዝን በሚሹ በሚጓጉ እግሮች
በአንድ በሀሪ በብዙ ጠባዮች
.
ስትፈልግ ተቀባይ ስትፈልግ ገፊዋ
ብዙ መሳይ አለም ብዙ ተከታዩዋ
.
መነሻ በሌለው መድረሻውን ባጣ
በመንጋ ሂደት ውስጥ አንድ እራሱን ያጣ
እራሱን ሲፈልግ በሪታ በርጋታ
ምንም ማታቀው ነብስ ግራዋን ተጋብታ
የበፊት ስፍራዋን ማረፊያዋን አታ
መሸሽን ከጅላ መድረሻዋ ጠፍቷት
ስሜት በሚነካ ንዴት ባለው ምሬት
ሳትፈልግ ተቀብራ እንዲው በመሀል ቤት
:
ስትመለከተው አካሉ እንዳለ ነው
ስትመረምረው ስሜቱ አንድ ነው
ስጋውን ደርቦ በእግሩ እየተመራ
ቁልቁለቱን ሲወርድ ሲወጣ ተራራ
በአንድ ዛቢያ ላይ ብዙ ሲሽከረከር
አዕምሮውን ስቶ በራሱ ሲሸበር
.
በአንድ ሺ ደስታ አንዴ ተደስቶ
በአንዲቷ ሀዘን አንድ ሺ ተጎድቶ
በድንገት ይገኛል ህይወቱን አጥፍቶ
በራሱ መንጋ ውስጥ አንድ እራሱን አቶ

ሰው ማለት ይህ ነው!!!

@mawekletesanew
@mawekletesanew
258 viewsЄямι Иєgи, 05:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-29 10:13:42 ድርሻዬ

@mawekletesanew

@endemeselen

አሀዱ ተብሎ ስገዱ ሲጀመር
ጆሮን የሚረብሽ ድምፅ ይሰማ ነበር
በሴቶች መግቢያ በር
ስርአቱን ትቼ
ቀና ስል ጓጉቼ
መለየት ይከብዳል ሰው ወይም መንፈስ
ክንድ እሚያህል ታኮ በአጭር ቀሚስ
ጡቷ እንደ ፀጉር እጅግ የወረደ
እርምጃዋ ግራ የተወላገደ
ፊቷ እንደ ለሊት ፅልመት የሞላበት
ፍርሀት ወረረኝ ውሻ እንዳየ ድመት
እናቶች ከበሩ አታልፊም ሲሏት
ሞነጫጭራ ገፍታ ሁሉንም በፍጥነት
አልፋኝ እንደ ሄደች የኋላው ሲጀመር
የጭኗን ሁኔታ መግለፅ ከባድ ነበር
በቃ ኩፍታ ነው እንደው ይወፍራል
ስገዱ ባይባል ያየ ሁሉ ይፈርዳል
ሁኔታዋ ቀፎኝ ወደ ጎን ሳማትር
የዘበኛው ነገር ቀጥ ብሎ ነበር
ከቅዱሱ ስፍራ ቶሎ እንደማባረር
መልዐክ እንዳየ ሰው ቆሞ ያያት ነበር
.
እናቶችን ገፍታ ዘበኛ አደንዝዛ
በከበረው ቤቱ ስቴድ እንደዋዛ
ተበሳጨሁኝ ልቤ ጨከን አለ
ላሶጣት ወሰንኩኝ ህዝቡ ሰግዶ እንዳለ
ከዛም ፈጠንኩና ልብሷን ሳብ አረኩኝ
ስሟን እንዳልጠራ ስሟን አላወኩኝ
ወዲያው እንደሳብኩት ዞራ ስታየኝ
ብርድ ብርድ ብሎ ላብ አስቸገረኝ
የህንዶች ሆረር ፊልም በጣም ናፈቀኝ
እረ አምላኬ ምነው
ሲኦል የከተትከኝ ምድር ላይ እያለው
-.
እቺን ለማባረር
ያስፈልጋልና አምላካዊ ተዐምር
ልመለስ ወሰንኩኝ ችግር ሳይፈጠር
ግን ደንዳናው ልቤ ድርሻህን ተወጣው
በማለት ደጋግሞ ውስጤን ሲያስጨንቀው
በንዴት ሳብኩና የራሴን ነጠላ
አልብሻት ተወጣው ድርሻዬን በመላ

@mawekletesanew

@endemeselen
@endemeselen
229 viewsЄямι Иєgи, 07:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-28 22:38:09
192 viewsSelik Bin, 19:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-22 19:44:57
226 viewsЄямι Иєgи, 16:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-25 11:04:33 ተስፋ ማር ነበረ

@endemeselen

@endemeselen

የታለመ ምኞት ያሰሩት በመላ
ለዛሬ መኖሪያ የሚሆን ከለላ
ለነገ መድረሻ
የሚሆን ወጌሻ
ተስፋ የህይወት ማር ከማርም ወለላ
ወድቆ ባይሰበር ባይደርቅ እንደ ሸክላ
ተስፋ ማር ነበረ
ባአቶ ካልመረረ
ተስፋ ተስፋን አቶ እሬትን ባልጋተ
የመኖር ድባብን ባላንኮታኮተ
ፅልመትን አንግሶ ሞትን ባልጎተተ
ስሜትን ባልጎዳ
በእውን በተነዳ
ተስፋ ማር ነበረ
ከሁሉ የከበረ
ባይቀር በነበረ


@endemeselen
@endemeselen
@endemeselen
270 viewsЄямι Иєgи, 08:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ