Get Mystery Box with random crypto!

@endemeselen @endemeselen ሰው ማለት እንዲ ነው @en | እንደመሠለን🥴😂❤️

@endemeselen
@endemeselen

ሰው ማለት እንዲ ነው

@endemeselen

በብዙ ህይወት ውስጥ በአንድ ስሜት ጉዞ
ሲፈልግ ጥላቻ አልያ ፍቅርን ይዞ
መጓዝን በሚሹ በሚጓጉ እግሮች
በአንድ በሀሪ በብዙ ጠባዮች
.
ስትፈልግ ተቀባይ ስትፈልግ ገፊዋ
ብዙ መሳይ አለም ብዙ ተከታዩዋ
.
መነሻ በሌለው መድረሻውን ባጣ
በመንጋ ሂደት ውስጥ አንድ እራሱን ያጣ
እራሱን ሲፈልግ በሪታ በርጋታ
ምንም ማታቀው ነብስ ግራዋን ተጋብታ
የበፊት ስፍራዋን ማረፊያዋን አታ
መሸሽን ከጅላ መድረሻዋ ጠፍቷት
ስሜት በሚነካ ንዴት ባለው ምሬት
ሳትፈልግ ተቀብራ እንዲው በመሀል ቤት
:
ስትመለከተው አካሉ እንዳለ ነው
ስትመረምረው ስሜቱ አንድ ነው
ስጋውን ደርቦ በእግሩ እየተመራ
ቁልቁለቱን ሲወርድ ሲወጣ ተራራ
በአንድ ዛቢያ ላይ ብዙ ሲሽከረከር
አዕምሮውን ስቶ በራሱ ሲሸበር
.
በአንድ ሺ ደስታ አንዴ ተደስቶ
በአንዲቷ ሀዘን አንድ ሺ ተጎድቶ
በድንገት ይገኛል ህይወቱን አጥፍቶ
በራሱ መንጋ ውስጥ አንድ እራሱን አቶ

ሰው ማለት ይህ ነው!!!

@mawekletesanew
@mawekletesanew