Get Mystery Box with random crypto!

ድርሻዬ @mawekletesanew @endemeselen አሀዱ ተብሎ ስገዱ ሲጀመር ጆሮን የ | እንደመሠለን🥴😂❤️

ድርሻዬ

@mawekletesanew

@endemeselen

አሀዱ ተብሎ ስገዱ ሲጀመር
ጆሮን የሚረብሽ ድምፅ ይሰማ ነበር
በሴቶች መግቢያ በር
ስርአቱን ትቼ
ቀና ስል ጓጉቼ
መለየት ይከብዳል ሰው ወይም መንፈስ
ክንድ እሚያህል ታኮ በአጭር ቀሚስ
ጡቷ እንደ ፀጉር እጅግ የወረደ
እርምጃዋ ግራ የተወላገደ
ፊቷ እንደ ለሊት ፅልመት የሞላበት
ፍርሀት ወረረኝ ውሻ እንዳየ ድመት
እናቶች ከበሩ አታልፊም ሲሏት
ሞነጫጭራ ገፍታ ሁሉንም በፍጥነት
አልፋኝ እንደ ሄደች የኋላው ሲጀመር
የጭኗን ሁኔታ መግለፅ ከባድ ነበር
በቃ ኩፍታ ነው እንደው ይወፍራል
ስገዱ ባይባል ያየ ሁሉ ይፈርዳል
ሁኔታዋ ቀፎኝ ወደ ጎን ሳማትር
የዘበኛው ነገር ቀጥ ብሎ ነበር
ከቅዱሱ ስፍራ ቶሎ እንደማባረር
መልዐክ እንዳየ ሰው ቆሞ ያያት ነበር
.
እናቶችን ገፍታ ዘበኛ አደንዝዛ
በከበረው ቤቱ ስቴድ እንደዋዛ
ተበሳጨሁኝ ልቤ ጨከን አለ
ላሶጣት ወሰንኩኝ ህዝቡ ሰግዶ እንዳለ
ከዛም ፈጠንኩና ልብሷን ሳብ አረኩኝ
ስሟን እንዳልጠራ ስሟን አላወኩኝ
ወዲያው እንደሳብኩት ዞራ ስታየኝ
ብርድ ብርድ ብሎ ላብ አስቸገረኝ
የህንዶች ሆረር ፊልም በጣም ናፈቀኝ
እረ አምላኬ ምነው
ሲኦል የከተትከኝ ምድር ላይ እያለው
-.
እቺን ለማባረር
ያስፈልጋልና አምላካዊ ተዐምር
ልመለስ ወሰንኩኝ ችግር ሳይፈጠር
ግን ደንዳናው ልቤ ድርሻህን ተወጣው
በማለት ደጋግሞ ውስጤን ሲያስጨንቀው
በንዴት ሳብኩና የራሴን ነጠላ
አልብሻት ተወጣው ድርሻዬን በመላ

@mawekletesanew

@endemeselen
@endemeselen