Get Mystery Box with random crypto!

​​​​​ ​​ ┈┈••◉❖◉●••┈ እውነት ሄድሽ በቃ? : | እንደመሠለን🥴😂❤️

​​​​​ ​​ ┈┈••◉❖◉●••┈
እውነት ሄድሽ በቃ?
:¨·....................:¨·.



ምትወጃት ጨረቃ
ከሰማይ ሰሌዳ ሳትጠፋ ጠልቃ
ነብሴም እንቺን ለምዳ፣
ልክ እንደ ህፃን ልጅ ሳይበቃት ፈንድቃ
እውነት ሄድሽ በቃ?
ለቅሶ ይሰማኛል፣
የሚያነቡ ሰዎች ከፊቴ አያለሁ
አፈር ቡንን ይላል፣
መቃብር ሲቆፈር እመለከታለሁ
ምን እያረጉ ነው?
ምን እንደሚያደርጉ እኔ ምን አውቃለሁ
ድንዝዝ ብያለሁ!
መደንዝዝ ታውቂያለሽ፣
ሳይነቃነቁ ዝም ብሎ መገተር
ምንም ስሜት አልባ፣
በጥፊ ቢመታ ወይም ቢገፈተር
ደንዝዝ ብያለሁ አዎ ልክ እንደዛ
እንዲሁ እንደ ወዛ!
ፎቶሽን የያዙ፣
አሮጊት ሴትዮ ደረት ይመታሉ
እንዳንዶች በዕንባ፣
እህህ እያሉ ይንከራተታሉ
የማልቀስ
የማንባት
እነዚህ ስሜቶች እኔ ጋ የታሉ?
ፍርጃ
ፍዝዝ ብያለሁ ያላንዳች እርምጃ
ድንዝዝ ብያለሁ የነካኝን እንጃ!
በቆምኩበት ቦታ፣
እንደተገተርኩኝ ዕንባ ሳላወጣ
የለቅሶ የዋይታ፣
አሰቃቂ ድምፀት እየተጠጋኝ መጣ!
ድንገት ብንን አልኩኝ፣
ይደልቅ ጀመረ ልቤ በሀይል መምታት
ለሁለት ተከፈልኩኝ አነቃኝ ማመንታት!
በዚህ...፣
ዘላለማዊ ናት አትሞትም እሷ
በዚያ...፣
እመን
እመን
እመን
ከንግዲህ አትመጣም አፈር ሆኗል ልብሷ!
በጥርጥር መሀል
በማመንም መሀል ልቤ እየዋለለ
ዕንባዬ ጠብ አለ!
ጉም ዙሪያዬን ሞላው ጨለማ ከለለኝ
መሄድ መሞትሽን አመንኩኝ መሰለኝ!
ለራሴ አዘንኩኝ ባዘን ሆዴ ባባ
አምርሬ አለቀስሁ ታጠብኩኝ በዕንባ!
አይመስለኝም ነበር
በግዜ ምትከፍቺው የማቃብርን በር!
መውደድ ሳይዳብሰኝ ፍቅር ሳይነካካኝ
አልቀርብሽም ነበር፣
መሆንሽን ባውቀው እዚህ ድረስ ጨካኝ::
ላትመጪ ነገር
ላትመለሽ ነገር
ወዴት ሄጄ ልበድ፣
የልቤን ትኩሳት ምን ብዬ ልናገር?
ምትወጃት ጨረቃ
ከሰማይ ሰሌዳ ሳትጠፋ ጠልቃ
ነብሴም እንቺን ለምዳ፣
ልክ እንደ ህፃን ልጅ ሳይበቃት ፈንድቃ
እውነት ሄድሽ በቃ?

@endemeselen