Get Mystery Box with random crypto!

ተስፋ ማር ነበረ @endemeselen @endemeselen የታለመ ምኞት ያሰሩት በመላ ለዛሬ | እንደመሠለን🥴😂❤️

ተስፋ ማር ነበረ

@endemeselen

@endemeselen

የታለመ ምኞት ያሰሩት በመላ
ለዛሬ መኖሪያ የሚሆን ከለላ
ለነገ መድረሻ
የሚሆን ወጌሻ
ተስፋ የህይወት ማር ከማርም ወለላ
ወድቆ ባይሰበር ባይደርቅ እንደ ሸክላ
ተስፋ ማር ነበረ
ባአቶ ካልመረረ
ተስፋ ተስፋን አቶ እሬትን ባልጋተ
የመኖር ድባብን ባላንኮታኮተ
ፅልመትን አንግሶ ሞትን ባልጎተተ
ስሜትን ባልጎዳ
በእውን በተነዳ
ተስፋ ማር ነበረ
ከሁሉ የከበረ
ባይቀር በነበረ


@endemeselen
@endemeselen
@endemeselen