Get Mystery Box with random crypto!

Ethiopian Catholic Charismatic

የቴሌግራም ቻናል አርማ eccrm — Ethiopian Catholic Charismatic E
የቴሌግራም ቻናል አርማ eccrm — Ethiopian Catholic Charismatic
የሰርጥ አድራሻ: @eccrm
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 658

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-01-14 08:21:30
190 views05:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-11 20:34:02 #የ_21_ቀን_ፆም_ፀሎት_ልዩ_ፕሮግራም

መንፈሳዊ መነቃቃት ለብዙ ክርስቲያኖች ከሁሉም የላቀ አስፈላጊ ነገር ነው። ዛሬ እንዴት እናገኘዋለን? በራሳችን ሕይወትም ሆነ በሌሎች ሰዎች እነኚህ የመነቃቂያ መንገዶች ምን ምን ናቸው።

መንፈሳዊ መነቃቃት ወይም መታደስ ማለት ያለንን ነገር እንደገና ማስነሳት ማነቃቃት ያለንን ነገር በአዲስ መልኩ ትኩረት በመስጠት እንደገና ማሰራት ማስቀጠል ወይም ደግሞ የሆነ ሕይወታችን ላይ ደክሞ የታየን ነገር በአዲስ መልኩ ማሰራት ማስጀመር ብለን ልንገልጠው እንችላለን።

በፀሎት ደክመን ከሆነ እንደገና ወደ ፀሎት ሕይወት ለመመለስ ወደ እግዚአብሔር ፀጋዎች የምንቀርብበት

በመንፈሳዊ ሕይወት ቀዝቅዘን ከሆነ በመንፈሳዊ ሕብረት ውስጥ ለመሳተፍ ሞራል አጥተን ከሆነ ያንን ኃይል እንደገና የምንቀበልበት።

ከእግዚአብሔር ቃል ጋር ሕብረት አቋርጠን ከሆነ ከቃሉ ጋር ሕብረታችንን የምናስቀጥልበት።

በመንፈሳዊ ድካም የተነሳ በስጋ ስራ እየተፈተንን ከሆነ በኃይሉ ነፃ የምንወጣበት።

“እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ፤ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ፤ ይሮጣሉ፥ አይታክቱም፤ ይሄዳሉ፥ አይደክሙም።”
  — ኢሳይያስ 40:31

ሰኞ ታህሳስ 3 ይጀምራል
ከጠዋቱ 3:30 ሰዓት እስከ ቀኑ 9:00 ሰዓት
ቦታ ዶንቦስኮ ቤተ ፀሎት

የምትችሉ ሁሉ በዚህ ፆም ፀሎት ፕሮግራም ላይ በመሳተፍ የበረከቱ ተካፋዮች እንድትሆኑ ተጋብዛችኋል።

ታህሳስ 3 ርዕስ

“በስሜ የተጠሩት ሕዝቤ ሰውነታቸውን አዋርደው ቢጸልዩ፥ ፊቴንም ቢፈልጉ፥ ከክፉ መንገዳቸውም ቢመለሱ፥ በሰማይ ሆኜ እሰማለሁ፥ ኃጢአታቸውንም ይቅር እላለሁ፥ ምድራቸውንም እፈውሳለሁ።”
— 2 ዜና 7፥14

እንዴት ፆም ፀሎት ማድረግ አለብን?
የፆም ፀሎት ፍሬዎች ምንድን ናቸው?
194 views17:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-08 12:22:34
173 views09:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-02 22:22:22
112 views19:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-02 22:20:46 ሰላም ውድ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች  ቅዳሜና እሁድ (ህዳር 24 እና 25) በድምቀት በሚከበረው  የክርስቶስ ንጉስ በአል ምክንያት ሳምንታዊው የእሁድ ፕሮግራማችን እንደማይኖርና ሁላችንም በልደታ ለማርያም (ካቴድራል ቤተክርስቲያን) በመገኘት የበረከቱ ተካፋይ እንድንሆን እናሳስባለን።
116 views19:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-10 20:39:41
133 views17:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-22 11:08:49 #የምርጫህ_ውጤት_እንደሆንክ_ተረድተሀል

“በፊታችሁ ሕይወትንና ሞትን በረከትንና መርገምን እንዳስቀመጥሁ እኔ ዛሬ ሰማይንና ምድርን በአንተ ላይ አስመሰክራለሁ፤ እንግዲህ አንተና ዘርህ በሕይወት ትኖሩ ዘንድ ሕይወትን ምረጥ፤”
— ዘዳግም 30፥19

መልካም ሕይወትም ክፉ ሕይወትም በምርጫህ ውስጥ ያለ መሆኑን ተረዳና ዛሬ መልካሙን ሕይወት ለማግኘትና ለመኖር ወስን። የምርጫህ ውጤት ነህ ያልመረጥከውን መኖር አትችልም። አሁን ወይም ባለፉት ግዜያት ምን በማድረግ እያሳለፍክ ነው? የምትውልበትና ትኩረት የሰጠኸው ግዜህን የሰጠኸው ነገር ምንድን ነው? የዚያ ውጤት እንደሆንክ ተረዳ። እግዚአብሔርም ባልመረጥከው ነገር ምንም ሊያደርግልህ አይችልም። ስለዚህ ነቅተን ሕይወት የሚገኝበትን ነገር ላይ ትኩረት እናድርግ። ቃሉን እናጥና እንፀልይ መልካምን ለማድረግ እንትጋ ሕይወታችን በደስታ የተሞላ ጣፍጭ ይሆናል።


https://t.me/eccrm
https://t.me/eccrm
https://t.me/eccrm
432 views08:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-14 12:11:16
311 views09:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-12 07:40:30
#ደስተኛ_ሰዎች_ባላቸው_ነገር_አመስጋኞች_ናቸው

“ሳታቋርጡ ጸልዩ፤ በሁሉ አመስግኑ፤ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ እናንተ ነውና።”
  — 1ኛ ተሰሎንቄ 5፥17-18

የሆነ ነገር ሲሳካልኝ እደሰታለው የሚለውን ሀሳብ ተውና አሁን እጃችሁ ላይ ባለ ነገር እግዚአብሔር በሰጣችሁ ነገር ማመስገንና መደሰት ጀምሩ። ሕይወታችሁ ውስጥ ልዩ የሆነ ደስታ በየዕለቱ ማጣጣም ትችላላችሁ። በጠዋት ስትነሱ ባላችሁ ነገር ላይ ከልብ አመስግኑ ቀናችሁ በጥሩ ስሜት ታሳልፋላችሁ። በተቻላችሁ መጠን የሚረብሽ ዜና አትስሙ። በዚህ ዘመን ቲቪውን ሬዲዎውን ሞባይላችሁን ስትከፍቱ በልታችሁ ከምትጠግቡት ቁርስ በላይ ክፉ ዜናዎች ብፌ ሆነው ይቀርቡላችኋል ማየትም አለማየትም ምርጫው የእናንተ ነው። ልባችሁን ጠብቁ ብሎ መፅሐፍ ቅዱስ መክሮናል። ልናስተውል የሚገባው የምንሰማውና የምናየው ነገር ከስሜታችን ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት አላቸው። የሕይወት ምርጫ በእጃችን ነው።

እነዚህን የሚመስሉ መንፈሳዊ ሕይወትን የሚያሳድጉ ትምህርቶች ተዘጋጅቶላችኋል።

በ 2015 አንዱ እቅዳችሁ በመንፈሳዊ ሕይወት ማደግ ከሆነ ለዩ የሆነ የመፅሐፍ ቅዱስ ትምህርት ተዘጋጅቶላችኋል።

ሕይወት በመንፈስ ቅዱስ መነቃቃት ሰሚናር

በጎተራ ዶንቦስኮ ቤተ ፀሎት

ዘወትር እሁድ ከ 5:30 - 7:00 ሰዓት


https://t.me/eccrm
https://t.me/eccrm
https://t.me/eccrm
652 views04:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-11 07:20:42 #የእግዚአብሔር_ፈቃድ_ለደስታችን_ነው

የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ።


አንድ ሰው የእግዚአብሔርን ማንነት በአግባቡ ተረድቶ መኖር ሲጀምር በእግዚአብሔር ላይ የታመነ ሕይወት ይኖረዋል። በእግዚአብሔር ላይ መታመን ማለት በዕረፍት ውስጥ መኖር ማለት ነው። ይህ እንዲሆንልን በየዕለቱ በእግዚአብሔር ቃል የሚታደስ ሕይወት ሊኖር ግድ ይላል። አእምሮአችንን ስናድስ ከብዙ የሕይወት ስህተቶች እንድናለን። አእምሮአችንን ስናድስ ሰላማችንን እናስጠብቃለን። አእምሮአችንን ስናድስ ከጭንቀት ሕይወት ነፃ እንወጣለን። አእምሮአችንን ስናድስ በዓለም ክፉ ስራ አንያዝም። ጭንቀት ውስጥ ፍርሀት ውስጥ ካላችሁ የእግዚአብሔር ቃል አእምሮአችሁን እንዲያድሰው ፍቀዱለትና ከእግዚአብሔር የሆነ ልዩ በረከት ተቀበሉ።

እግዚአብሔር ሁሉን ነገር ሰጥቶናል የሰጠንን ነገር ሁሉ ግን የምናገኘው በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ነው ስለዚህ የእግዚአብሔርን ቃል ለማወቅ ልንበረታ ያስፈልገናል።

በ 2015 አንዱ እቅዳችሁ በመንፈሳዊ ሕይወት ማደግ ከሆነ ለዩ የሆነ የመፅሐፍ ቅዱስ ትምህርት ተዘጋጅቶላችኋል።

ሕይወት በመንፈስ ቅዱስ መነቃቃት ሰሚናር

በጎተራ ዶንቦስኮ ቤተ ፀሎት

ዘወትር እሁድ ከ 5:30 - 7:00 ሰዓት


https://t.me/eccrm
https://t.me/eccrm
https://t.me/eccrm
https://t.me/eccrm
37 views04:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ