Get Mystery Box with random crypto!

#የምርጫህ_ውጤት_እንደሆንክ_ተረድተሀል “በፊታችሁ ሕይወትንና ሞትን በረከትንና መርገምን እንዳስቀ | Ethiopian Catholic Charismatic

#የምርጫህ_ውጤት_እንደሆንክ_ተረድተሀል

“በፊታችሁ ሕይወትንና ሞትን በረከትንና መርገምን እንዳስቀመጥሁ እኔ ዛሬ ሰማይንና ምድርን በአንተ ላይ አስመሰክራለሁ፤ እንግዲህ አንተና ዘርህ በሕይወት ትኖሩ ዘንድ ሕይወትን ምረጥ፤”
— ዘዳግም 30፥19

መልካም ሕይወትም ክፉ ሕይወትም በምርጫህ ውስጥ ያለ መሆኑን ተረዳና ዛሬ መልካሙን ሕይወት ለማግኘትና ለመኖር ወስን። የምርጫህ ውጤት ነህ ያልመረጥከውን መኖር አትችልም። አሁን ወይም ባለፉት ግዜያት ምን በማድረግ እያሳለፍክ ነው? የምትውልበትና ትኩረት የሰጠኸው ግዜህን የሰጠኸው ነገር ምንድን ነው? የዚያ ውጤት እንደሆንክ ተረዳ። እግዚአብሔርም ባልመረጥከው ነገር ምንም ሊያደርግልህ አይችልም። ስለዚህ ነቅተን ሕይወት የሚገኝበትን ነገር ላይ ትኩረት እናድርግ። ቃሉን እናጥና እንፀልይ መልካምን ለማድረግ እንትጋ ሕይወታችን በደስታ የተሞላ ጣፍጭ ይሆናል።


https://t.me/eccrm
https://t.me/eccrm
https://t.me/eccrm