Get Mystery Box with random crypto!

#የእግዚአብሔር_ፈቃድ_ለደስታችን_ነው የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም | Ethiopian Catholic Charismatic

#የእግዚአብሔር_ፈቃድ_ለደስታችን_ነው

የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ።


አንድ ሰው የእግዚአብሔርን ማንነት በአግባቡ ተረድቶ መኖር ሲጀምር በእግዚአብሔር ላይ የታመነ ሕይወት ይኖረዋል። በእግዚአብሔር ላይ መታመን ማለት በዕረፍት ውስጥ መኖር ማለት ነው። ይህ እንዲሆንልን በየዕለቱ በእግዚአብሔር ቃል የሚታደስ ሕይወት ሊኖር ግድ ይላል። አእምሮአችንን ስናድስ ከብዙ የሕይወት ስህተቶች እንድናለን። አእምሮአችንን ስናድስ ሰላማችንን እናስጠብቃለን። አእምሮአችንን ስናድስ ከጭንቀት ሕይወት ነፃ እንወጣለን። አእምሮአችንን ስናድስ በዓለም ክፉ ስራ አንያዝም። ጭንቀት ውስጥ ፍርሀት ውስጥ ካላችሁ የእግዚአብሔር ቃል አእምሮአችሁን እንዲያድሰው ፍቀዱለትና ከእግዚአብሔር የሆነ ልዩ በረከት ተቀበሉ።

እግዚአብሔር ሁሉን ነገር ሰጥቶናል የሰጠንን ነገር ሁሉ ግን የምናገኘው በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ነው ስለዚህ የእግዚአብሔርን ቃል ለማወቅ ልንበረታ ያስፈልገናል።

በ 2015 አንዱ እቅዳችሁ በመንፈሳዊ ሕይወት ማደግ ከሆነ ለዩ የሆነ የመፅሐፍ ቅዱስ ትምህርት ተዘጋጅቶላችኋል።

ሕይወት በመንፈስ ቅዱስ መነቃቃት ሰሚናር

በጎተራ ዶንቦስኮ ቤተ ፀሎት

ዘወትር እሁድ ከ 5:30 - 7:00 ሰዓት


https://t.me/eccrm
https://t.me/eccrm
https://t.me/eccrm
https://t.me/eccrm