2022-06-28 04:12:26
ጌትዬ የመጨረሻችንን ነገር አደራ ዛሬ ስንታይ ጀነት ላይ vip ፊርደውስን የገባን ያህል ፈታ ብለናል አንተው በዲንህ ላይ አፅናን ።
ኢብነል ጀውዚ እንዳወሰቱ ኢብኑከሲር አልቢዳያ ወኒሃያ ላይ እንዳሰፈሩት አንድ ዐብደቱ ኢብኑ ዐብዱረሂም የተባለ ቃሪእና ሙጃሂድ ከሚባሉት ውስጥ የነበረ ሰው ነበር ከእለታት አንድ ቀን ከሙስሊሞች ጋር ወደ ሩም በዘመተበት ግዜ ላይ ይህ ሙጃሂድ ከአንድ ምሽግ ውስጥ ተቀምጦ ይጠባበቃል በአጋጣሚ ግን አይኑ ወደ አንዲት ቆንጆ የሩም ክርስቲያን ሴት ላይ አረፈ ወድያውኑ ልቡም ሸፈተ ወደዚች ሴት ለመድረስም ደብዳቤ ላከላት እንዲህም አላት " ወደ አንቺ መድረሻው መንገድ ምንድነው?
እርሷም " እኔን የምታገኝበት መንገድ አንድና አንድ ነው እሱም እኔ ያለሁበትን ክርስትና መቀበል ያኔ እኔ ያንተ መሆን እችላለሁ " አለች
እርሱም ለጥያቄዋ አወንታዊ ምላሽን ሰጠ! ለርሷ ተንበረከከ ከፈረ! አላህ ይጠብቀን ።
ከርሱም ጋር የነበሩ ሙስሊሞች ያልጠቁት ክስተት ነበረና እጅጉን አዘኑ በርሱ ሰበብም የሙስሊሞች ጦር ክፍተት ተፈጠረበት። ይህ ክስተት ካለፈ ከረዥ አመታት ቡሃላ ሙስሊሞቹ በሩሞቹ ቀዬ በኩል ሲያልፉ ይህን ቃሪእ ምጃሂድ የነበረ ወንድማቸውን አስታወሱት ፈልገውም አገኙት ።
ሲያገኙት ከዛችው ከሩም የሆነችዋ ከሚስቱ ጋር ነበር ቀጥለውም እንዲህ አሉት " አንተ ዐብደት ሆይ! እንደው እስቲ ንገረን ያ ሁሉ የሸመድድካቸው የአላህ ቃል ቁርአን ምን ላይ አደረሰክ? ያ ዒልምህስ? ያ ሶላትህስ ያ ፆምህስ ? ያ ጂሀድህስ? ...
የእርሱ መልስ ግን እንዲህ ነበር
" እወቁ እኔ አሁን ላይ ሁሉንም የቁርአን አንቀፆች ረስቻቸዋለሁ አይህ አንቀፅ ሲቀር እርሱም ...
رُّبَمَا يَوَدُّ الَّذِينَ كَفَرُوا لَوْ كَانُوا مُسْلِمِينَ
እነዚያ የካዱት (በትንሣኤ ቀን) ሙስሊሞች በኾኑ ኖሩ ብለው በብዛት ይመኛሉ፡፡
ذَرْهُمْ يَأْكُلُوا وَيَتَمَتَّعُوا وَيُلْهِهِمُ الْأَمَلُ ۖ فَسَوْفَ يَعْلَمُونَ
ተዋቸው ይብሉ፤ ይጠቀሙም፡፡ ተስፋም ያዘናጋቸው፡፡ በእርግጥም ወደፊት (መጥፎ ፍጻሜያቸውን) ያውቃሉ፡ ( አል ሂጅር 23)
ረሱሉ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ይህን ዱዐእ ያበዙ ነበር
" አንተ ልብን ምታገለባብጥ ጌታ ሆይ በዲንህ ላይ ልቤን አፅና "
አላህ ልቦናችንን ያፅናልን
አንዋር ኺያር
99 views01:12