Get Mystery Box with random crypto!

ሐዘን አይቀጥልም፣አዲስ ነገርም አይደለም፦ (ነብዩ (ﷺ) አዝነው ነበሩ )ቡኻሪ ―6982 ማንባት | ቢስሚከ ነሕያ✿⁠ ⁠♡

ሐዘን አይቀጥልም፣አዲስ ነገርም አይደለም፦
(ነብዩ (ﷺ) አዝነው ነበሩ )ቡኻሪ ―6982

ማንባት ሁልግዜም አይቀጥልም፣ዱንያም ናትና ኣለማልቀስም አይታሰብም፦
(ነብዩ ﷺ አለቀሱ)ቡኻሪ ―1304

ዝምታ ጥሩ ነገር ነው፣በተለይ ስለ ጉዳዩ ምንም ተጨባጭ ግንዛቤ በሌለንበት ጉዳዮች ላይ፦
(ነቢያችን ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰላም ለተወሰነ ጊዜ ዝም ይሉ ነበር) ቡኻሪ 3695

የፈገግታ ግዜ እሩቅ ባይሆንም በትዕግስትና በስሌት ግዜውን እንጠብቅ፣ነገራቶች እያማሩ ሲመጡ የብስራት ብርሃን ፍንጣቂ መምጣቱ አይቀርም፣ፈገግታም ሱና ነው ተብለዋል
(ከዚያም ነቢዩ ﷺ ፈገግ አሉ።)ቡኻሪ- 1021

ከዚያም ዉዱ ነቢያችን በሚያምረው ገፅታቸው ስቀው ነበሩ፣ማለትም ሁልግዜ አንድ አይነት ጨለማ ፊትን ለሁሉም ማሳየት ተወዳጅ አይደለም፦
"ነብዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ሳቁ) ቡካሪ 1936

ፈገግታው፣ ሳቁ፣ ዝምታው፣ ሀዘኑ እና ለቅሶው ለእኛ ለተከታዮቹ መንገድ በሆነው ነቢይ ላይ ሰላት እና ሰላም በእርሱ ላይ ይሁን።

@ጃዕፈር