Get Mystery Box with random crypto!

#ከዓሪፎቹ_መንደር ‹‹ አንድ ሰው ወደ አላህ እውነትኛ የሆነን ሱጁድ ቢያደርግ ከስጁድ በኋላ በፍ | ቢስሚከ ነሕያ✿⁠ ⁠♡

#ከዓሪፎቹ_መንደር

‹‹ አንድ ሰው ወደ አላህ እውነትኛ የሆነን ሱጁድ ቢያደርግ ከስጁድ በኋላ በፍጹም ካጎነበሰበት መነሳት አይችልም፡፡›› ሱልጣን አልዓሪፊን ኢብኑ ዐረቢ (ቀደሰላሁ ሲረሁ)

እንግዲህ የዓሪፎቹ ንግግር ከባድና ጥልቅ ነው፡፡ የእነርሱን ንግግሮች ለመረዳት ጥረት ብናደርግና ብንኖርበት ለጊዜያችን ብዙ ምላሾች አሉት፡፡ ንግግሮቻቸው ከቁርአናዊና ሐዲሳዊ ግንዛቤና ከአላህ የተሰጣቸው ድንቅ ችሮታ ነው፡፡ እውነት ነው አንዴ ለአላህ የሰገደች ነፍስ እንዴት ሌላ ይታያታል፡፡ የስጁድ ትርጉሙ ባርነትን ለአላህ ማድረግ መቻል ነው፡፡ ባሪያ ደግሞ ነጻነቱ ጌቶቹን ማስደሰቱ ነው፡፡ እኛ አላህን ማስደስት መቻል ነበር ነጻነታችን እንጂ የነፍሲያን ፍላጎት ማግነን አልነበረም፡፡ አላህን በማምለክ ባርነት ውስጥ ማግኘት የነበረብንን ብዙ ጥቅሞችና የዱንያ ገረዶች ፍጡሩን በማምለክ የፈለግነው ጊዜ ተዋረድን፡፡ ሰዎች የገንዘብ፣ የአስተሳሰብ፣ የፖለቲካና የነፍሳቸው ባሪያ ሲኾኑ ሰው ስለኾኑ ብቻ የተሰጣቸው ታላቅነት ይገፈፋሉ፡፡ ሰዎች ለአላህ በሚያሳዩት ባርነት ልክ ደስታቸውን መሥራት ሲጀምሩ ከመላእክት ሁላ ይበልጣሉ፡፡ ዛሬ ግን ሰዎች ሕይወታቸው ከሚያሳድጉት ውሻ ራሱ አልሻል አለ፡፡ ለውሻቸው ስም የሚያወጡ ሰዎች ረስተውት ራሳቸው እንደውሻ ፍርፋሪ መልቀም ብቻ ሆነ ሥራቸው፡፡ ሰዎች ከፍታቸው በባርነታቸው ሲሆን ይህ ባርነት ለፍጡር ሲሆን ደግሞ በምንም ነገር ቢከብሩ በእምነት እንኳ የላቁ ቢመስላቸው የተዋረዱ ሆነው ይኖራሉ፡፡

#መደድከ_ያ_አላህ!

@ቤስት ከሪም