2022-09-01 20:56:02
ከሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር የጸጥታ ምክር ቤት በወቅታዊ ጉዳየው የተሰጠ መግለጫ እና የክልከላ እገዳዎች!
ከክልከላዎቹም መካከል፡-
1.ማንኛውም ባጃጅ እና ሞተር ሳይክል ከምሽቱ 2 ስአት በኃለ መንቀሳቀስ አይችልም ፣
2.የሰው እንቅስቃሴ ገደብ ከምሽቱ አምስት ስዓት በኃላ የተገደበ ነው
3.ማንኛውም የአልጋ አገልግሎት የሚሰጡ ሆቴሎች በፎርሙ መሰረት እንዲያከራዩና የተለየ እንቅስቃሴ ሲመለከቱም ለጸጥታ አካላት መጠቆም አለባቸው፣
4. መጠጥ ቤቶች፣ ምግብ ቤቶች፣ ጭፈራ ቤቶች እንዲሁም ማንኛውም አገልግሎት የሚሰጡ የግል ተቋማት ከምሽት 4 ሰዓት በኃላ ምንም አይነት አገልግሎት መስጠት አይችሉም ፣
5. ከየትኛውም አካባቢ ተፈናቅለው በከተማዋ ተጠልለው የሚገኙ ወገኞች ከምሽቱ12 በኃላ መንቀሳቀስ አይችሉም ፣
6. ማንኛውም ትራንስፖርት ታሪፍ መጨመር እንዲሁም ሌሎች ምግብ ነክና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁስሶች ላይ ምንም አይነት የዋጋ ጭማሪ ማድረግ በጥብቅ የተከለከለ ነው
7. ማንኛውም አካል ከመንግስት እውቅና ውጪ ስብሰባ ማድረግ የተከለከለ ነው
8. ከመንግስት የፀጥታ አካላት ውጪ ማንኛውም ግለሰብ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ እንዲሁም ህዝብ በበዛባቸው ቦታዎች ይዞ መገኘት በጥብቅ የተከለከለ ነው ፣
9. የጠላት እንቅስቃሴን በአሉባልታ መደገፍ እንዲሁም በተለያዪ ድህረ ገጾች መለጠፍ በጥብቅ የተከለከለ ነው ፣
10. ማንኛውም የቤት አከራይ የሚያከራየውን ተከራይ ማንነት ከመለየት ባለፈ በአግባቡ መረጃ መያዝ እና የተለየ ነገር ሲያጋጥም ደግሞ ለሚመለከተው የጸጥታ አካል ማሳወቅ
11. ማንኛውንም የአልጋ አገልግሎት የሚሰጥ የግል ተቋም አገልግሎት የሚሰጠውን ግለሰብ በፎርሙ መሰረት አገልግሎት መስጠትና የተለየ እንቅስቃሴ ያለውን ጸጉረ ልውጥ ግለሰብ ሲያጋጥም ደግሞ በፍጥነት ለጸጥታ አካላት ማሳወቅ እና ሌሎች ለከተማዋ ሰላምና ደህንነት አስጊ የሚሆኑ ማንኛውንም ጉዳይ ካለማድረግና ሌሎችም እንዳያደርጉ በማድረግ ኃላፊነቶን ይወጡ ሲል ምክር ቤቱ መግለጫውንና ክልከላውን አስታውቋል ፡፡
@dailyNews_et @dailyNews_et
1.5K views17:56