2022-01-05 11:41:03
"የትግራይ ወራሪ ሀይል የህልውናችን ስጋት በመሆኑ ሁልግዜም በተጠንቀቅ ተዘጋጅተን መጠበቅ አለብን።" ዶክተር ይልቃል ከፋለ
ዶክተር ይልቃል ከፋለ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ተከታዩን መልዕክት አስተላልፈዋል
የትግራይ ወራሪ ሀይል የህልውናችን ስጋት በመሆኑ ሁልግዜም በተጠንቀቅ ተዘጋጅተን መጠበቅ አለብን።
ህልውናችን ለማስከበር መላ ህዝባችን ያለምንም ልዩነት በአንድነት የከፈለው መስዋትነት የጠላትን ወረራ መቀልበስ እንዳስቻለ ሁሉ በቀጣይም ለህልውናችን ስጋት የሆነውን ወራሪ ሀይል ለመዋጋት ብቻ ሳይሆን ለውስጣችን ሰላምና ልማትም ወሳኝ በመሆኑ አንድነታችን አጠናክረን ማስቀጠል ይገባናል።
በሌላ በኩል የከተሞቻችን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ መጀመሪያ በኮረና በመቀጠል በጦርነቱ ምክንያት በከፍተኛ ሁኔታ እየተዳከሙ ይገኛሉ። ይህን የቁልቁለት ጉዞ ለመግታት የተገኙ አማራጮችን ሁሉ በመጠቀም ኢኮኖሚውን ማነቃቃት አማራጭ ሳይሆን ግዴታ ነው።
ከዚህ አንጻር በመጭው ግዚያት በተለይ የቱሪስት ከተማወች የበለጠ እንዲነቃቁ የሚከበሩ በአላትን እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም የመሻሻል ተስፋን መፈንጠቅ አለብን።
ከመደበኛ አከባበሩ በተጨማሪ ዲያስፖራው ከሀገር ፍቅር ስሜት በመነጨ እያደረገ ላለው ጉብኝትና ድጋፍ ከበአሉ ጋር ተዳምሮ የተለየ ቀለምና ድምቀት እንዳለው ማስተጋባቱም ለውስጥም ለውጭም ዘርፈ ብዙ መልእክት እንዳለው መረዳት ይገባል።
ከዚህም በላይ በአላትን በደመቀ ሁኔታ ማክበሩ በህዝባችን ላይ የደረሰውን የስነ ልቦና ጉዳት ለመጠገን የራሱ አስተዋጽኦ አለው። እነዚህ ሁነቶች በጦርነት የተጎዳው ህዝባችን ወደነበረበት መደበኛ ህይወት መመለስ እንደሚችል ተስፋ ይሰጣል። በመሆኑም በአሉ በአግባቡ እንዲከበር በመንግስት ትኩረት መሰጠቱ ተገቢ መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል።
በአንድ በኩል ህልውናችን ለማስከበር በሌላ በኩል የውስጥ ሰላማችንና ልማታችን ለማፋጠን ሁላችንም እኩል ትኩረት ሰጠን መንቀሳቀስ ቀጣዩ የትግላችን አቅጣጫ ነው።
ትግል በአንድ ወቅት የሚጠናቀቅ ሳይሆን በየምዕራፋ በቅብብሎሽ የሚቀጥል ጅረት ነው።
መጭው ግዜ በተስፋ የሚጠበቅ የድል፤ የሠላምና የልማት ግዜ ለማድረግ ሁላችንም በአንድነት እንረባረብ!
@dailyNews_et @dailyNews_et
2.3K views08:41