Get Mystery Box with random crypto!

Daily News 🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ dailynews_et — Daily News 🇪🇹 D
የቴሌግራም ቻናል አርማ dailynews_et — Daily News 🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @dailynews_et
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 7.84K

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-09-23 19:36:22
በራያ ግንባር!

ህዋሃት ለወራት እዋጋባቸዋለሁ ብሎ በሰው ቁመት ልክ ያዘጋጃቸው ሹሉበር እና ምንደና ተራራ ስር የሚገኙ ምሽጎች በወገን ጦር ቁጥጥር ስር ውለዋል። በዚህ ግንባር አብዛኛው የትግራይ ወራሪ ኃይል ምሽግ ውስጥ እንዳለ አልቋል።

@dailyNews_et @dailyNews_et
1.7K views16:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-23 17:34:10
የ6 ዓመት ሕፃን በማገት 200 ሺህ ብር የጠየቀው ግለሰብ በቁጥጥር ሥር ዋለ!

የ6 ዓመት ሕፃን በማገት 200 ሺህ ብር የጠየቀው ግለሰብ በቁጥጥር ሰር መዋሉን ፖሊስ አስታወቀ፡፡

የሸኔ አባል እንደሆነ የተጠረጠረው ግለሰቡ የ6 ዓመት ሕፃን በማገት 200 ሺ ብር ከሕጻኑ ወላጆች በመቀበል ልጁን ሆለታ ከተማ ጫካ ውስጥ ጥሎ መሄዱ ተገልጿል፡፡ ከዚያም ዘነበ ወርቅ መናኸሪያ በመሳፈር ወደ ጅማ ከተማ ሊያመልጥ ሲል በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ጅማ በር ፖሊስ አባላት በቁጥጥር ሥር መዋሉን የክፍለ ከተማው ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል።

የክፍለ ከተማው ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ገብሬ መሰል ወንጀሎችን ከቦታ ቦታ እየተዘዋወሩ የሚፈፅሙ ፀጉረ ልውጦች በመኖራቸው ማህበረሰቡ አካባቢውን ነቅቶ እንዲጠብቅ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
    
@dailyNews_et @dailyNews_et
1.6K views14:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-05 08:59:53 አቧሬ

በራያ ቆቦ  07 ቀበሌ ልዩ ቦታው አቧሬ በሚባል አካባቢ የሚገኙ አርሶ አደሮች የታጠቁትን የግል ጦር መሳሪያ በህውሃት ታጣቂዎች ለነገ ማክሰኞ አስረክቡ መባላቸው ታውቋል።

ለምን እንሰጣለን በሚል ጥያቄ ላቀረቡ ግለሰቦች አሁን ዝም ካልናችሁ ስንመለስ ህይወት ታጠፉብናላችሁ የሚል ምላሽ እንደሰጧቸው ለማወቅ ተችሏል።

@dailyNews_et @dailyNews_et
87 views05:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-04 21:23:23
ቀያይ ሴጣኖቹ መድፈኞቹን ረተዋል

በስድስተኛው ሳምንት የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ተጠባቂ መርሐ ግብር ማንችስተር ዩናይትድ 3 ለ 1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የአርሰናልን ያለመሸነፍ ጉዞ ገተዋል።

ማርከስ ራሽፎርድ ( 2X ) እንዲሁም አዲሱ ፈራሚ አንቶኒ የቀያይ ሴጣኖቹን የማሸነፊያ ግቦች ከመረብ አሳርፈዋል። ቡካዮ ሳካ የመድፈኞቹን ብቸኛ እና አቻ ያደረገች ግብ ማስቆጠር ችሎ ነበር።

@dailyNews_et @dailyNews_et
715 views18:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-04 21:19:20
ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ የ10ኛው የበጎ ሰው ሽልማት ልዩ ተሸላሚ ሆነች

10ኛው የዓመቱ በጎ ሰው ዕውቅና እና ሽልማት መርሃ ግብር የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በተገኙበት ዛሬ ተካሂዷል፡፡ በተለያዩ ዘጠኝ ዘርፎች የአመቱ የበጎ ሰው ሽልማት አሸናፊዎች ተለይተዋል።

1. በመምህርነት ዘርፍ ዶክተር ውብሸት ዠቃለ

2. በበጎ አድራጎት ዘርፍ ወይዘሮ ክብራ ከበደ

3. በቅርስና ባህል ሸህ መሐመድ አወል ሃምዛ

4. በኪነጥበብ ፊልም ዳይሬክቲንግ ዓለምፀሐይ በቀለ

5. በዲያስፖራ ዘርፍ ዶክተር ርብቃ ጌታቸው ኃይሌ

6. ንግድና ሥራ ፈጠራ ዘርፍ ሰኢድ መሐመድ

7. በመንግሥታዊ የሥራ ኃላፊነት አቶ ግርማ ዋቄ

8. በሚዲያ ዘርፍ አቶ ሰለሞን ገብረሥላሴ

9. በሳይንስ ዘርፍ ኢሜሪቲስ ፕሮፌሰር ረዳ ተክለሃይማኖት

ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ ደግሞ የ10ኛው የበጎ ሰው ሽልማት ልዩ ተሸላሚ ሆናለች።

@dailyNews_et @dailyNews_et
740 views18:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-04 16:33:06
እኛ ዝም ያልነው ገበሬው እንደዚህ ነው።
አባዋራው ግንባር ሄዶ ከጥምር ጦሩ ጋር ሲዋደቅ እማዋራና ልጆች ስንቅ ያቀብላሉ
ክብር ለእናንተ

@dailyNews_et @dailyNews_et
1.0K views13:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-04 14:50:42
አሳዛኝ ዜና
ተማሪው በዶርሙ ውስጥ እራሱን በመስቀል ህይወቱ አለፈ!!

ተማሪ ፋዓድ ወንድወሰን ዳንኤል በወሎ ዩኒቨርሲቲ በጤና ኮሌጅ የ2ኛ ዓመት የፋርማሲ/ Pharmacy /ተማሪ የነበረ ሲሆን በ26/12/2014 ዓ.ም ምክኒያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ከማደሪያ ቤቱ/ዶርሙ/ውስጥ እራሱን በመስቀል ህይወቱ እንዳለፈ ዩኒቨርሲቲው ገልፇል።

ዩኒቨርሲቲው በተማሪው ህይወት ማለፍ ከፍተኛ ሃዘን የተሰማው መሆኑን የገለፀ ሲሆን ለቤተሰቦቹ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹና ለክፍል ጓደኞቹ መጽናናትንም ተመኝቷል።

ነብስ ይማር
  
@dailyNews_et @dailyNews_et
1.2K views11:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-04 12:44:12 አሸባሪው ህወሀት በቆቦ ህፃናትና አዛውንቶች ላይ በከባድ መሳሪያ ጥቃት ፈፅሟል

አሸባሪው የህወሀት ቡድን የሽብር ቡድኑ ነሐሴ 19 ቀን 2014 በቆቦ ወረዳ ህፃናትና አዛውንቶች ላይ በከባድ መሳሪያ ጥቃት መፈፀሙን የጥቃቱ ተጎጂዎችና ቤተሰቦቻቸው ገለጹ።
ንፁሃንን በመጉዳት የተካነው የሽብር ቡድኑ በቆቦ ወረዳ የአርሶ አደሮችን ቤት እና ከብቶችን በመጠበቅ ላይ የነበሩ ታዳጊዎችን በመድፍ በመደብደብ በህፃናትና አዛውንቶች ላይ ጉዳት አድርሷል።

"እኛ አርሶ አደሮች ነን፤ የሽብር ቡድኑ በማዕበል ወረራ ፈፅሞ ዘረፋ መፈጸሙ ሳያንስ በከባድ መሳሪያ ደብድቦናል" ይላሉ።
የሽብር ቡድኑ ያደረሰባቸው ጉዳት መቼም የማይሽር ጠባሳ መሆኑን የገለጹት ተጎጂዎቹ፤ በአሁኑ ወቅት ተገቢ ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑን ጠቅሰዋል።

ሆኖም በሽብር ቡድኑ ወረራ ውስጥ ያሉ ቤተሰቦቻቸውን በህይወት የመኖርና አለመኖር ሁኔታ አለማወቃቸው በእጅጉ እንዳሳሰባቸውም ነው የተናገሩት።
የሽብር ቡድኑ ለሰላም የተሰጠውን እድል ትቶ ጦርነት በከፈተባቸው የአማራ ክልልና አፋር ክልል ወረዳዎች በንፁሃን ዜጎች ላይ ጥቃት በማድረስ የሽብር ተግባር መፈጸሙን አሁንም መቀጠሉን የኢዜአ ዘገባ ያመለክታል።

@dailyNews_et @dailyNews_et
1.2K views09:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-04 11:47:58

ይህ መረጃ ትክክል አለመሆኑን አሁን በተደወለልኝ ስልክ አረጋግጫለሁ።ሮቢትና አካባቢው ፋኖ የሰለጠኑትን ዝርዝር ይዘው ቤት ለቤት በመዞር ወጣቶችን እየደበደቡ ነው ብለውኛል።መረጃዎቹ በብዙ ውጣ ውረድ ነው የሚገኙት።ያጋጥማል ቤተሰብ ይቅርታ

@dailyNews_et @dailyNews_et
1.2K viewsedited  08:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-03 21:36:49
በወርቄ አካባቢ ከ3 ቀበሌ ከ20 ሺህ በላይ ህዝብ ተፈናቅሎ እንደሚገኝ ተሰምቷል።6 እናቶች ገና አዲስ ወልደው ዛፍ ስር ተጠልለው ይገኛሉ።ወንዶች ትግል ላይ ናቸው።በቀል እንዳይፈፀምባቸው ሸሽተው የሄዱት ሴቶች እና ህፃናት ሲሆኑ ልዩ ድጋፍ ስለሚፈልጉ ትብብር እናድርግላቸው።


@dailyNews_et @dailyNews_et
745 views18:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ