2023-03-20 10:47:48
በይ ጥሪኝ ሰርግሽን
ልታደም ግብዣሽን ልመርቅ ባልሽን
ልቅመስ ድግስሽን ላሙቀው ዳስሽን
በሞቀው አጀባ ባሰርሽው ቀለበት
ሳቅሽን እያየው ካዳፈንኩት
ቁስሌ ጨው ልነስንስበት
የበጋ ዘመኔን ጭጋግ እያረሰው ሳሚው ሳሚው
ሲሉሽ እጄን አንከርፍፌ ላጨብጭብ እንደሰው
ከበሮሽ ሲደቃ የክህደትሽ በትር እያነቀኝ ሴቃ
እልል በሉ ልበል ተድረሻል በቃ
እያነቡ እስክስታ ልጨፍር የኔ አለም
በይ ጥሪኝ ግድ የለም
ያሰርንው እምነት የገባንው ኪዳን
ቀን ጎድሎ ከከዳን ሲቀር ታሪካችን
እንባሽና እንባዬ ይፍጅ ሆዳችን
ልብሽና ልቤን አስሮ የገመደው ባይቆረጥ ውሉ
ለራስ አልተፃፈም ያፈቀሩት ሁሉ…
https://t.me/BrocknHearts
359 viewslast seen, edited 07:47