2022-07-03 19:54:11
ቤርሙዳ
አለማችን እጂግ ያልተረዳናቸውን እጂግ አስደናቂ ሚስጥሮችን ይዛለች ለበረካታ መቶ አመታት ሚስጥሩ ሳይፈታ እንዲሁ በጊዜ ይፈታው ተቆልፎ የቀር በርካታ ሚስጥራዊ ሁነቶች አሉ።
እንኳንስ በመላው አለም በኢትዮጵያ ምድር ላይ ለሰወች የተከለከሉ ከፍተኛ የስበት ሃይል ያለባቸው የአቅጣጫ መጠቆሚያ ኮምፖሶችን የሚስዋዠቁ የአይር መንገድ በርራን ያገዱ ቦታወች ከራስ ደጀን ጀምሮ እስከ የረር ሚስጥራዊ ቦታወች ከ ከፋር በርሀማ ቦታ እስከ ሱዳን ጠረፍ ጭምር በሚያስደንቅ ሀንታ ይገኛሉ።
በእርግጥ እኒህ ቦታወች በመንፈሳዊ አይን እይታ ሲታዩ መልስ ቢገኝላቸው ለተቀረው አካላት ግን እንቆቅልሽ ሁነው ያልፋሉ።
በኢትዮጵያ ከፈተኛ እና ዝቀተኛ ቦታወች ያሉ በርካታ መግነጢሳዊ ቦታወች በሌላ ፕሮግራም የምንገኛን ይሆናል...
ለዛሬ ግን አንድ እጂግ አደገኛ እና ሚስጥራዊ ቦታን ላስግብኛችሁ ... የሰይጣኑ ማዕዘን ይባላል
በጻህፍት ደራስያን በከረሰ ምድር አጥኝወች በስነ ፈለካት ተመራማሪወች ብዙ አወዛጋቢ ነገሮች ተብሎለታል።
በምዕራቡ ሰሜን አትላንቲክ ወቅያኖስ አካባቢ የሜክሲኮ የባህር ሰላጤ ታክኮ ከካርቢያን ሃይቅ ስር እኛዎ ምድር የሚገኝ 3,900,000 km 2 የሚሰፋ መግነ ጢሳዊ ሃይል ባለቤት ቤር ሙዳ....
ወደ ዚህ የ ሶስት ማእዘን ክልል ውስጥ የገባ ማንኛውንም ነገር ካሉበት አካባቢ በነፋስ ፍጥነት ጎትቶ የት እንደደረሱ ድራሻቸው የሚያጠፋው ቤርሙዳ ትሪያንግል ጀርባ ያለው ሚስጥራዊ ነገር ምን ይሆን...?
ከቤርሙዳ ትሪያንግል ጀርባ ያለው ሚስጥራዊ ነገር?
ቤርሙዳ ትሪያንግል በአትላንቲክ ውቅያኖሶች ውስጥ የሚገኝ ከፍተኛ ሀይል እና ስበት ያለው ሚስጥሩ ያልተፈታ ድንቅ ቦታ ነው::
ከአሜሪካ ፍሎሪዳ ግዛት ዝቅ ብሎ የሚገኝ ሲሆን በስተ-ደቡብ
በኩል ካሪቢያን ደሴት ያዋስነዋል::
ቤርሙዳ ትርያንግልን ለመጀመሪያ ጊዜ ያየው ክርስቶፍር ኮሎምቦስ ነው ዘመኑም 1449 ነበር:: አለምን በሚያስስበት ወቅት ቤርሙዳን ሲያይ በመገረም እንዲህ አለ''በአድማስ ላይ የሚደንስ እንግዳ የሆነ የ ብርሐን ጮራ'' .
''በሠማይ ላይ የነገሰ የእሳት ነበልባል'' ''የአቅጣጫ
መጦቀሚያ ኮምፓስን የሚያመሠቃቅል ሀይል'' ብሎታል::
ታድያ ከዚህ ቦታ ጀረባ ምን ቢኖር ነው እንዲህ ብርቱና ምታታዊ የሚመስል ክስተትን የሚያሳይ?
ይህ ቤርሙዳ ባልታወቀ የስበት ሀይል ሚስጥር በርካታ መርከቦችን አውሮፕላኖችን የሠው ልጅ ህይወትና ሃብት እንደያዙ ድብዛቸውን አጥፍቷል ::
በመርከብ የሚሄደውን በአውሮፕላን የሚበረውን ወደታች ስቦ ይውጠዋል:: የሠመጠው ነገር የት እንደገባ አይታወቅም።
በዚህ ቤርሙዳ ትሪያንግ ክልል ውስጥ አለም ላይ በተለያየ ግዚያት ብዙ ኩነቶችን አስተናግዳለች።
በ1812 ቲዎዶሲያ በር አልስተን የተባለች የወቅቱ የ
AMERICA ም/ፕ የሆኑት የአሮን ባር ልጅ DECEMBER
30 በ1812 ዓመት ፓትሮዎት በተባለች መርከብ ስትጓዝ ጠፍታ
ቀርታለች::
ፍላይት 19 የተባለች አውሮፕላን ከ 14 ተጋዥ ጋር በዚህው አካባቢ ስትበር የት እንደገባች ሳይታወቅ ጠፍታለች::
ፍላይትና ፍለጋ የተላኩ 6 አውሮፕላኖችና 27 ሠዎች በዛው ጠፍተዋል::
1918- ሳይክለሮፕል ዩ.ኤስ.ኤል የተባለች መርከብ 309
ተሳፋሪዎችን ይዛ ተሰውራለች:: ይህ እስካሁን ድረስ በ AMERICA ባህር ሐይል ታሪክ ፍቺ ያልተገኘለት ሚስጥር ሆኖ ቀርታል::
1948- ስታር ታይገር 19 እና ዳግላስ DC 3 የተባሉ
አውሮፕላኖች ባጠቃላይ ከ9 አብራሪዎችና ከ54 ተሳፋሪዎች ጋር ጠፍተዋል::
1949- ስታር ሮያል የተባለች አውሮፕላን ከ7 አብራሪዎችና ከ13 ተሳፋሪዎች ጋር ጠፍታለች:: .
ይህ አካባቢ ብዙ ያልተመዘገቡ እና አለም ላይ ይፋ የማይደረጉ ክስተቶችን በሰወች ልጆች ላይ አድረሷል ወደፊትም ያደርሳል።
ስለዚህ አካባቢ ብዙ ጥናትና ምርምር ቢደረግም ከመላምት የዘለለ ይህ ነው የሚባል አንዳች ነገር አልተረጋገጠም።
ከፍተኛ የማግኔት መጠን ውቅያኖስ ውስጥ ሊኖር ይችላል የሚል መላምትም ሲሰጡት ይስተውላለ ::
በአትላንቲክ ውቂያኖስ በተለምዶ ‹‹ቤርሙዳ ትሪያንግል›› ተብሎ የሚጠራው አካባቢ ሚስጥር በመጨረሻ እንደደረሱበት የዘርፉ ተመራማሪዎች አስታወቁ፡፡
በ500 ሺህ ኪሎ ሜትር ስኩዌር የውቂያኖሱ ክልል ላይ የተንጣለለው ይህ አነጋጋሪ ውሃማ ክልል በተለያዮ ጊዜዎች በርካታ ቁጥር ያላቸውን አውሮፕላኖች፣ መርከቦች፣ የጦር ጀቶችና ሌሎች ቁሶችን ውጦ በማስቀረት ዱካቸውን አጥፍቶ ለአርጂ እንኳን ወሬው ሳይደረስ እስካሁን ሲያነጋግር የቆየ ሚስጥር ነበር፡፡
ይህንንም ተከትሎ ተመራማሪዎች ለበርካታ ጊዜያት የጉዳዩን ምንነት ሚስጥር ለመፍታት ሲታትሩ ቆይተው አሁን ላይ በለስ ቀናን ሲሉ ተናግረዋል፡፡
እንደተመራማሪዎቹ ከሀገረ ብሪታኒያ አቅራቢያ በሰሜን ባህር ላይ ስድስት ማዕዘን ቅርጽ ያለው ጉም አልያም ደመና መሳይ አየር ከተመለከቱ በኃላ የቤርሙዳ ትሪያንግልን ሚስጥር መፍታት መቻላቸውን ይፋ አድርገዋል፡፡
ከዚህም ጉም ወይም ደመና ስር ደግሞ በሰዓት 170 ማይል በከፍተኛ ፍጥነት የሚምዘገዘግ ንፋስ እንደሚፈልቅ ከሳተላይት ከተገኘ መረጃ ለማወቅ መቻላቸውን ይናገራሉ ተመራማሪዎቹ ፡፡
ይህም 45 ጫማ ከፍታ ያለው ሰፊ የባህር ሞገድ የሚፈጥር በመሆኑ መርከቦችን የመገልበጥና አውሮፕላኖችን ደግሞ ወደ ውቂያኖሱ የመድፈቅ ከበቂ በላይ አቅም እንዳለው ነው ተመራማሪዎቹ ያረጋገጡት፡፡
በዚህም ምክንያት ታዲያ ተመራማሪዎቹ ይህን ግዙፍ ሀይል የሚያመነጨውን ደመና በግርድፉ ‹‹የአየር ቦንብ›› የሚል ስያሜ አውጥተውለታል፡፡
ለመሆኑ ከዚህ ቦታ በስተጀርባ ያልታወቀዉ ለሳይንስ የከበደ ድብቅ ሚስጥራዊ ሀይል ምንድን ነው?
እንዲህ አይነት የተወሳሰቡና መግቢያ በር ማይገኝባቸው ሚስጥራዊ ሁኔታወች ሲከሰቱ የጥንት የቤተክርስትያን መዛግብት የብራና ድርሳናትን መመልከት ፍቱን መዳሀኒት መሆኑን ግልጽ ነው።
ለመሆኑ መዛግብቶቻችን ስለ ቤርሙዳ ምን ይላሉ?
ይህ ቤርሙዳ በሶስት መአዘን ክልል ውስጥ የሚገኝ የመናፍስቱ እና የሰማዝያ ጭፍሮች መኖሪያ ነው።
እኒህ የስማዝያ ጭፍሮች ራይት ወይም Giant የወደቁ መላእክት ሲሆና ከ ረቂቃን መናፍስት ወይም በሀገረኛው አጠራር ጂን ወይም ቆሌ ከሚባሉ ርቂቃን ጋር የሚኖሩበት ከፍተኛ ስበት ያለው ቦታ ነው። እኒህ ጂን ወይም ቆሌ የኑሮ ዘያቸው እንደሰወች ሲሆን ሩካቤ ይፈጽማሉ ይዋለዳሉ ይራባሉ ነገር ግን ለአይን የማይታዩ ረቂቃን መናፍስት ሲሆን በብዙ የሚኖሩት በባህር እና ወንዝ ዳርቻ ነው። እኒህ ከሰው ዘር የሆኑ በርግማን እንደረከሱ የሚነገርላቸው ቆሌ ወይም ጂን ከስማዝያ ጭፍሮች ጋር በመዋህድ በቤርሙዳ ትርያንግል አካባቢ ሀይላቸውን በመግልጽ ከበርባኖስ ስር በውቅያኖስ ፕራሚድ እንደገነቡ ይነገራል።
በዚህም ምክኒያት የሰው ልጂ ወደ ዚህ ክልል ውስጥ ከገባ ደብዛውን አጥፍተው ይወስዱታል።
በሀገራችንም የተለያዩ ቦታወችም ይህ ቆሌ ወይም ጂን የሚባሉ መናፍስት የሚገለጹበት ቦታወችም አሉ።
144 views16:54