Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮ መፅሀፍት 🇪🇹 📚

የቴሌግራም ቻናል አርማ bookethio — ኢትዮ መፅሀፍት 🇪🇹 📚
የቴሌግራም ቻናል አርማ bookethio — ኢትዮ መፅሀፍት 🇪🇹 📚
የሰርጥ አድራሻ: @bookethio
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 276
የሰርጥ መግለጫ

ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል::
📚📖📚📖📚📖📚📖
የንባብ በህላችንን እናዳብር ።
📖📚📖📚📖📚📖📚
ሀሳብ አስተያየት ካለ
👇👇👇👇👇👇
@Bookethio_bot
ወይም
@Ibiruk

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-06-21 19:00:58 ሁሌም ትታሰባለህ!

ያለምክንያት አልተፈጠርክም ፤ ያለምክንያት ክቡሩ የሰው ልጅ አልሆንክ ፤ በመፈጠርህ ፣ ሰው በመሆንህ ፣ በልዩ ማንነትህ ሁሌም ተስፋ አለህ ። የተፈጠርክለትን ምክንያት የምታሳካበት ተስፋ ፣ የታሰበልህን ህይወት የምትኖርበት ተስፋ ፣ ያታቀደልህን ፣ የተመረጠልህን ሰው የምታገኝበት ተስፋ ።

አዎ! ጀግናዬ..! ሁሌም ትታሰባለህ ፤ ሁሌም ትታወሳለህ ፤ ሁሌም ትጠበቃለህ ፤ ትጎበኛለህ ፤ ትባረካለህ ፤ ትወደዳለህ በደጉ አምላክህ ፣ በቸሩ ፈጣሪህ በማያልቅ ፣ ማብቂያ በሌለው ፍቅርህ ትፈቀራለህ ፤ ትከበራለህ ። ማብቂያውን በማታውቀው ሰውኛ ተስፋ ፈጣሪን አትኮንን ።

ሰው ቢከዳህ ፣ ሰው ቢገፋህ ፣ ሰው ቢተውህ እንኳ በእምነትህ ልክ ፣ በተስፋህ መጠን መቼም የማይከዳህ ፣ መቼም የማይገፋህ ፣ የማይተውህ የዘላለም ወዳጅ ፣ የዘላለም አምላክ አለህና በቶሎ ፊትህን ወደእርሱ መልስ ።

አዎ! ለማንም የማታዋየው ፣ እርሱ ግን ከመሰረቱ የሚያውቀው ፣
ማንም የማይረዳህ ፣ እርሱ ግን ሳታወራው የሚረዳህ የልብ ወግ ፣ የህይወት ሚስጥር አለህ ፤ የትም አትሒድ ፤ ብዙ አትድከም ፤ መሰረቱን ለሚያውቀው ፣ አመጣጡን ላየው ለእራሱ ደግመህ አስረዳህ ፤ ካልጠየክ መፍትሔ የለህምና በሩን አንኳኳ ፤ ተማፀነው ፤ ለምነው ፤ ጠይቀው የሚበጅህን ምላሽ ከእርሱ እንጁ በፍፁም ከሰው አትጠብቅ ። ሰው ሲታወቅ ለዛሬው ቃሉ ነገ ስለመታመኑ ምንም ማረጋገጫ የለውም ። ሰውን አብዝተው ያመኑ ፣ ሰውን የተደገፉ የት እንዳሉ አይተሃል ፤ በአምላክ የተማመኑ ፣ ፈጣሪን ያመኑ የት እንደደረሱም ተመልክተሃል ።

አዎ! የህይወት ትርጉም በውልደትና በሞት መሃከል ነው ፤ ተስፋ የሚፈተነው ተስፋ በሚያሳጡ ሁነቶች መሃል ነው ፤ የፅናት መኖር የሚታየው በፈተና ወቅት ነው ፤ አምላክም ፍላጎትህን የሚሞላው ፣ ካሰብክበት የሚያደርስህ ፣ ድጋፍ ምርኩዝ የሚሆንህ ተስፋ ባደረከውና በአመንክበት ልክ ነውና ሁሌም ተሰፋ አደርግ ፤ እመን ነገሮች ይቀየራሉ ። በቻልከው መጠን ጥረትህን ቀጥል ፤ "አበርታኝ ፤ አግዘኝ ፤ ደግፈኝ ፤ አፅናኝ" በለው ። የውስጥ ህመምህን የሚያይ ፣ ትግልህን የሚረዳ እርሱ ብቻ ነውና የልብ ወዳጅ ፣ የቅርብ ደጋፊ አድርገው ፤ በእርሱ እገዛና ድጋፍ የማታልፈው ፣ የማትቀይረው ነገር እንደሌለ እመን ። መተማመኛህን ያዛ ፣ የሚያዋጣህን ተደገፍ ፤ በመንገድህ ሁሉ እራስህን ደግፍ ፤ በአምላክህ ተማመን ።

@bookethio
165 views16:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-16 07:23:35 •የተጠየቀ

ምርጥ መጽሐፎችን በ PDF ለማግኘት @bookethio ተቀላቀሉ።

#SHARE

@bookethio
176 viewsedited  04:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-16 07:23:02 እውርን እውር ቢመራው ተያይዞ ገደል የሚል ብሂል አለ መጀመሪያ ራስህን አድን ፣ራስህ ላይ አተኩር ፣ እንዲህ ባደርግ ሰዎች ይደሰቱብኛል ማለቱን ተወዉና ''እኔን ደስተኛ የሚያደርገኝ ምን ባደርግ ነው?'' በል። አንተ ደስተኛ ስትሆን አለም አብራህ ትስቃለች ፤ሰዎች የደስታህን ምንጭ ለማወቅ ሲል አንተን ያደምጡሀል ፣አየህ ራስህ ላይ ስታተኩር ሰዎች ደግሞ አንተ ላይ ማተኮራቸው ግድ ነው። አንተ ደግሞ ለራስህ ደስታ አታንስም።

@bookethio
154 views04:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-18 19:50:56 የኔ........ ስልሽ

የኔ ፍቅር ስልሽ
እንባ ያረገዘዉ ይሄ አይኔ ይደርቃል፣
መኖር የደከመዉ አካሌ ይወናል፡፡

የኔ ውድ ስልሽ
እርካሹ ስሜ ባንቺ ይወደዳል፣
ፅልመት የለበሰዉ ህይወቴ ይበራል፡፡

የኔ ቆንጆ ስልሽ
.............ጨለማዬ ነግቶ፣
በቋጥሮ የቆየው ደስታዬ ፈንድቶ፣
ዘላለም የሚቆይ ብርሀንን ይረጫል፣
መቼም ላይጠወልግ ደሰታዬ ያብባል፡፡

የኔ ፍቅር ስልሽ ስሜት ይፀነሳል፣
የኔ ውድ ስልሽ ፍቅር ይወለዳል፡፡
የግሌ አድርጌሽ
የኔ ብቻ ስልሽ
መሞቴን ረስቼ
ይኼው በነፃነት መኖር ጀመርኩልሽ፡፡

ክበር ተመስገን

መልካም ምሽት

@bookethio
258 views16:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-09 00:16:01 የአንተም ጊዜ ይመጣል!

"ዝሆንና ዉሻ በአንድ ቀን አረገዙ፡፡ ከሶስት ወር በኋላ እርጉዟ ዉሻ 6 ቡችሎችን ወለደች፡፡ ከስድስት ወር በኋላ ዉሻዋ እንደገና አርገዘች...ከዘጠኝ ወር በኋላ ሌሎች 6 ቡችሎችን ወለደች፡፡

እንደዚህ እያለች ብዙ ልጆችን ወለደች፡፡ በአስራ ስምንተኛዉ ወር ዉሻዋ ዝሆኗን እንዲህ አለቻት “እርጉዝ መሆንሽን ግን እርግጠኛ ነሽ? እኔም አንቺም እርጉዝናችን የጀመረዉ አንድ ቀን ላይ እንደነበር አስታዉሳለሁ፡፡

ይኸዉ እኔ ሶስት ጊዜ ወልጄ ከደርዘን በላይ ልጆች አሳድጌ ትላልቅ ሆነዉ ልጅ በልጅ ሆኛለሁ፡፡ አንቺ ግን አሁንም እርጉዝ ነሽ...ችግር አለ??”

ዝሆኗም መልሳ እንዲህ አለቻት “አንድ እንድታዉቂልኝ የምፈልገዉ እኔ የተሸከምኩት ቡችላ ሳይሆን ዝሆን ነዉ፡፡

ልወልድ የምችለዉ በሁለት አመት አንዴ ብቻ ነዉ፤ ግን ልጄ ገና ተወልዶ መሬቱን ሲረግጥ ሰዎች ተደንቀዉ ይጎበኙታል...የሁሉንም ቀልብ ይስባል ስለዚህ የተሸከምኩት ሃይለኛና ትልቅ ቀልብ የሚስብ ነዉ”

የዚህ አጭር ተረት መሰል ታሪክ ጭብጡ፡

ሰዎች ለጥያቄዎቻቸዉና ለጸሎቶቻቸዉ መልስ ሲያገኙ አንተ ግን ሳታገኝ ስትቀር ተስፋ አትቁረጥ፡፡ በሌሎች ምስክርነት አትቅና፡፡

የራስህን የጸሎት መልስ ካላገኘህ ዉስጥህ አይሰበር ይልቅ ለራስህ እንዲህ በለዉ "ጊዜዬ እየደረሰ ነዉ ተወልዶ መሬት የረገጠ እለት ሰዎች በአድናቆት የተወለደዉን ይመለከቱታል"

ሰናይ ምሽት ይሁንልን

@bookethio
261 views21:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-06 04:47:12
#መነበብ ያለበት መፅሀፍ
202 viewsedited  01:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-06 00:34:02 ቁጥር 4
256 viewsedited  21:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-06 00:19:31 ቁጥር 3
284 viewsedited  21:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-06 00:18:30 ቁጥር 2
269 viewsedited  21:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ