Get Mystery Box with random crypto!

የአንተም ጊዜ ይመጣል! 'ዝሆንና ዉሻ በአንድ ቀን አረገዙ፡፡ ከሶስት ወር በኋላ እርጉዟ ዉሻ 6 | ኢትዮ መፅሀፍት 🇪🇹 📚

የአንተም ጊዜ ይመጣል!

"ዝሆንና ዉሻ በአንድ ቀን አረገዙ፡፡ ከሶስት ወር በኋላ እርጉዟ ዉሻ 6 ቡችሎችን ወለደች፡፡ ከስድስት ወር በኋላ ዉሻዋ እንደገና አርገዘች...ከዘጠኝ ወር በኋላ ሌሎች 6 ቡችሎችን ወለደች፡፡

እንደዚህ እያለች ብዙ ልጆችን ወለደች፡፡ በአስራ ስምንተኛዉ ወር ዉሻዋ ዝሆኗን እንዲህ አለቻት “እርጉዝ መሆንሽን ግን እርግጠኛ ነሽ? እኔም አንቺም እርጉዝናችን የጀመረዉ አንድ ቀን ላይ እንደነበር አስታዉሳለሁ፡፡

ይኸዉ እኔ ሶስት ጊዜ ወልጄ ከደርዘን በላይ ልጆች አሳድጌ ትላልቅ ሆነዉ ልጅ በልጅ ሆኛለሁ፡፡ አንቺ ግን አሁንም እርጉዝ ነሽ...ችግር አለ??”

ዝሆኗም መልሳ እንዲህ አለቻት “አንድ እንድታዉቂልኝ የምፈልገዉ እኔ የተሸከምኩት ቡችላ ሳይሆን ዝሆን ነዉ፡፡

ልወልድ የምችለዉ በሁለት አመት አንዴ ብቻ ነዉ፤ ግን ልጄ ገና ተወልዶ መሬቱን ሲረግጥ ሰዎች ተደንቀዉ ይጎበኙታል...የሁሉንም ቀልብ ይስባል ስለዚህ የተሸከምኩት ሃይለኛና ትልቅ ቀልብ የሚስብ ነዉ”

የዚህ አጭር ተረት መሰል ታሪክ ጭብጡ፡

ሰዎች ለጥያቄዎቻቸዉና ለጸሎቶቻቸዉ መልስ ሲያገኙ አንተ ግን ሳታገኝ ስትቀር ተስፋ አትቁረጥ፡፡ በሌሎች ምስክርነት አትቅና፡፡

የራስህን የጸሎት መልስ ካላገኘህ ዉስጥህ አይሰበር ይልቅ ለራስህ እንዲህ በለዉ "ጊዜዬ እየደረሰ ነዉ ተወልዶ መሬት የረገጠ እለት ሰዎች በአድናቆት የተወለደዉን ይመለከቱታል"

ሰናይ ምሽት ይሁንልን

@bookethio