Get Mystery Box with random crypto!

ሁሌም ትታሰባለህ! ያለምክንያት አልተፈጠርክም ፤ ያለምክንያት ክቡሩ የሰው ልጅ አልሆንክ ፤ በመፈ | ኢትዮ መፅሀፍት 🇪🇹 📚

ሁሌም ትታሰባለህ!

ያለምክንያት አልተፈጠርክም ፤ ያለምክንያት ክቡሩ የሰው ልጅ አልሆንክ ፤ በመፈጠርህ ፣ ሰው በመሆንህ ፣ በልዩ ማንነትህ ሁሌም ተስፋ አለህ ። የተፈጠርክለትን ምክንያት የምታሳካበት ተስፋ ፣ የታሰበልህን ህይወት የምትኖርበት ተስፋ ፣ ያታቀደልህን ፣ የተመረጠልህን ሰው የምታገኝበት ተስፋ ።

አዎ! ጀግናዬ..! ሁሌም ትታሰባለህ ፤ ሁሌም ትታወሳለህ ፤ ሁሌም ትጠበቃለህ ፤ ትጎበኛለህ ፤ ትባረካለህ ፤ ትወደዳለህ በደጉ አምላክህ ፣ በቸሩ ፈጣሪህ በማያልቅ ፣ ማብቂያ በሌለው ፍቅርህ ትፈቀራለህ ፤ ትከበራለህ ። ማብቂያውን በማታውቀው ሰውኛ ተስፋ ፈጣሪን አትኮንን ።

ሰው ቢከዳህ ፣ ሰው ቢገፋህ ፣ ሰው ቢተውህ እንኳ በእምነትህ ልክ ፣ በተስፋህ መጠን መቼም የማይከዳህ ፣ መቼም የማይገፋህ ፣ የማይተውህ የዘላለም ወዳጅ ፣ የዘላለም አምላክ አለህና በቶሎ ፊትህን ወደእርሱ መልስ ።

አዎ! ለማንም የማታዋየው ፣ እርሱ ግን ከመሰረቱ የሚያውቀው ፣
ማንም የማይረዳህ ፣ እርሱ ግን ሳታወራው የሚረዳህ የልብ ወግ ፣ የህይወት ሚስጥር አለህ ፤ የትም አትሒድ ፤ ብዙ አትድከም ፤ መሰረቱን ለሚያውቀው ፣ አመጣጡን ላየው ለእራሱ ደግመህ አስረዳህ ፤ ካልጠየክ መፍትሔ የለህምና በሩን አንኳኳ ፤ ተማፀነው ፤ ለምነው ፤ ጠይቀው የሚበጅህን ምላሽ ከእርሱ እንጁ በፍፁም ከሰው አትጠብቅ ። ሰው ሲታወቅ ለዛሬው ቃሉ ነገ ስለመታመኑ ምንም ማረጋገጫ የለውም ። ሰውን አብዝተው ያመኑ ፣ ሰውን የተደገፉ የት እንዳሉ አይተሃል ፤ በአምላክ የተማመኑ ፣ ፈጣሪን ያመኑ የት እንደደረሱም ተመልክተሃል ።

አዎ! የህይወት ትርጉም በውልደትና በሞት መሃከል ነው ፤ ተስፋ የሚፈተነው ተስፋ በሚያሳጡ ሁነቶች መሃል ነው ፤ የፅናት መኖር የሚታየው በፈተና ወቅት ነው ፤ አምላክም ፍላጎትህን የሚሞላው ፣ ካሰብክበት የሚያደርስህ ፣ ድጋፍ ምርኩዝ የሚሆንህ ተስፋ ባደረከውና በአመንክበት ልክ ነውና ሁሌም ተሰፋ አደርግ ፤ እመን ነገሮች ይቀየራሉ ። በቻልከው መጠን ጥረትህን ቀጥል ፤ "አበርታኝ ፤ አግዘኝ ፤ ደግፈኝ ፤ አፅናኝ" በለው ። የውስጥ ህመምህን የሚያይ ፣ ትግልህን የሚረዳ እርሱ ብቻ ነውና የልብ ወዳጅ ፣ የቅርብ ደጋፊ አድርገው ፤ በእርሱ እገዛና ድጋፍ የማታልፈው ፣ የማትቀይረው ነገር እንደሌለ እመን ። መተማመኛህን ያዛ ፣ የሚያዋጣህን ተደገፍ ፤ በመንገድህ ሁሉ እራስህን ደግፍ ፤ በአምላክህ ተማመን ።

@bookethio