Get Mystery Box with random crypto!

ጠላትን ፍለጋ ደራሲ ደረጀ በቀለ 'ታንጀሪና ሆቴል' የሚል የአጫጭር ልቦ-ለድ ስብስብ ከመጽሐ | ኢትዮ መፅሀፍት 🇪🇹 📚

ጠላትን ፍለጋ

ደራሲ ደረጀ በቀለ 'ታንጀሪና ሆቴል' የሚል የአጫጭር ልቦ-ለድ ስብስብ ከመጽሐፍት አለው ከልቦለዶቹ አንዱ 'ትንሹ ሰይጣን' ይመዘዛል። ገጸ-ባህሪው ለረጅም አመት ታስሮ ይፈታል። በተፈታበት ዕለት ማታ አንድ ዱርዬ ልጅ ያገኛል። ልጁ ያጨሳል የሴተኛ አዳሪ ልጅ ነው። ገጸ-ባህሪው ከዚህ ልጅ ጋር ወሬ ይጀምራል። ልጁ የሚያወራው ነገር ሰይጣን አስባለው ግን የራሱ ልጅ ነው። ደራሲው እንዲህ ብሎ ልቦለዱን ይደመድማል። "ከትንሹ ሰይጣን ጀርባ የቆመው ትልቅ ሰይጣን ማን እንደሆነ በደንብ ታይቶኛል-ግሩም።"

ለሕይወት የተንሸዋረረ አረዳድ ከሌለን በቀር ከአካባቢያችን የሚታየው ስዕል ከእኛ ንድፍ ይነሳል። ለምሳሌ ካሊጉላ(ከ37 እስከ 41 እ.ኤ.አ) በግማሽ አእምሮው የተናወጠ መሪ ነው። ግን ለሮማውያን ጠላት አልነበረም የሮም ጠላት የነበሩት ካሊጉላን የተቀመሉት ለዚህ እውነት የሕዳግ ማብራሪያ አያስፈልገውም...

ይህ ሁሉ ነገር መፍትሄ የሚያገኘው ጠላትን በማወቅ ነው። እውነት ጠላታችን ማነው? አቤት የጠላታችን ብዛት ደራሲና ኀያሲ ዓለማየሁ ገላጋይ "ጠላታችን ማነው?" በሚለው መጣጥፉ
በፊታውራሪ ተክለሐዋርያት ተክለ ማርያም በተጻፈው አውቶባዮግራፊ(የሕይወቴ ታሪክ)
ን ዋቢ አድርጎ እንዲህ ይላል።

ከሁሉም ዘመን እጅግ የከፋው የዚህ ወቅት ሽኩቻ ነው። ያለማጋነን ህዝቡ እንዳለ ‹‹ቀኛዝማች ወልደአማኑኤሎችንና፣ ቀኛዝማች ፋሪሶችን›› እንዲሆን ተጥሯል። በብሔር፣ በቋንቋ፣ በሃይማኖት፣ በክልል አስተዳደር፣ በፖለቲካ… እየተናነቀ ሙሉ ትኩረቱን አጠገቡ ያለ ወገኑ ላይ እንዲያደርግ እየተሴረ ነው። በገዢዎች የተመደበለትን ተጋጣሚ የመጣል ባዕድ ትልም ግቡ አድርጐ እንዲቀርና ወደላይ እንዳያማትር በዕለት ተዕለት ሽኩቻ እርስ በእርሱ እንዲጠላለፍ ተደርጓል። ከበድ ያሉትን አገር አቀፍ ጉዳዮች ትተን በህግ፣ በፖሊሲና በደንብ እየታከኩ የሚጠሩትን የእርስ-በርስ ጠላትነቶች እንመልከት።" ብሎ አያበቃም መራር ጥያቄ ይጠይቃል እውነት ጠላታችን ማነው? ይላል።

ንጋት ከሚፈጥረው ዕለት ከሚፈጥረው ቁስል ጀርባ ያለው ማነው? ቁስር አለ ካልን ቆሳይና አቁሳይ አለ ከሁሉም ጀርባ እኛ አለን ገጣሚ ሰለሞን ሞገስ "እውነትን ፍለጋ" በሚለው የግጥም ስብስቡ እንዲህ ተቀኝቷል።

ጠላቴን ስፈልግ፥ ከጎረቤቶቼ
ጠላቴን ስፈልግ፥ ከባልደረቦቼ
ጠላቴን ስፈልግ፥ ከሩቅ ከቅርቦቼ
ለካስ ክፉ ጠላት ደመኛዬ ያለው
ከገዛ እኔነቴ ከራሴ ውስጥ ነው።

እጅ መጠቆሚያ አትፈልግ ያንተው ጠላት አንተው ነህ! ሐሳብ ያዝ በሐሳብ ተገዛ የተጫነህን መጅ አንሳ ወይ ለተሻለ ሐሳብ እጅ ስጥ! እስከመቼ ጠላትህን ስትፈልግ ጠላት ስትፈጥር ጠላቴነው ስትል ትኖራለህ?

@bookethio
@bookethio