Get Mystery Box with random crypto!

ቤተ_ዜማ

የቴሌግራም ቻናል አርማ bete_zemas — ቤተ_ዜማ
የቴሌግራም ቻናል አርማ bete_zemas — ቤተ_ዜማ
የሰርጥ አድራሻ: @bete_zemas
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 233

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-05-11 00:16:06 ወቅታዊ መልዕክት ለምዕመናን
++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++
መምህር ያረጋል አበጋዝ እንደጻፉት በሚል በማኅበራዊ ሚዲያዎች የተሰራጨውን   ጽሑፍ ተመልክተነዋል።ጽሑፉ ስለ መሪ ዕቅድ፣ስለ ዘላቂ ጥናቶች፣ስለ እጩ ኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ ወዘተ ...የሚዳስስ ሲሆን ያልተጨበጠ፣በመረጃ ላይ ያልተመሰረተና ነባራዊ እውነታዎችን ያላገናዘበ ሆኖ አግኝተነዋል።

     ይሁን እና ቤተ ክርስቲያናችን የገጠሟትን ፈተናዎች በጽናት ከመቋቋም ጋር ተቋማዊ አሰራሯን በማስተካከልና በማዘመን ውጤታማ ሥራ ለመሥራት በከፍተኛ ትጋት ላይ በምትገኝበት በዚህ ወቅት መምህር ያረጋል አበጋዝ   ፍጹም ከእውነት የራቀ መረጃን ለሕዝበ ክርስቲያኑ በማቀበል መደነጋገር እንዲፈጠር ለማድረግ ያደረጉት ሙከራ በእጅጉ አሳዝኖናል።

     ስለሆነም  ጸሐፊው በዝርዝር በገለጿቸው ጉዳዮች ዙሪያ በቅርቡ በብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባሕርዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ዝርዝር ማብራሪያ የሚሰጥበት መሆኑን እየገለጽን ሕዝበ ክርስቲያኑ ይህንን አውቆ በጸሎት፣ትዕግስትና በጽናት እንዲጠባበቅ በታላቅ አክብሮት ለመግለጽ እንወዳለን።

የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
ግንቦት ፪   ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም
27 views21:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-09 17:28:26 ሐናና ኢያቄም ይባረኩ ዘንድ ወደ ቤተመቅደስ ሔዱ። ዘካርያስም መልአኩ ለሐና እንዲነግራት ያዘዘውን ልትባረክ ስትመጣ ይነግራት ጀመረ።"ሐና የምነግርሽን ነገር ስሚ፤ በልቦናሽም ጠብቂው ከዚህ በኋላ ከባልሽ ከኢያቄም ጋር አትተኚ፤ በማኅጸንሽ ያለው ፍሬ ለእግዚአብሔር ንጹሕ መሥዋዕት ነውና። ይኸውም በዚያን ዘመን ሙሴ የተመለከተው ዕጽ ነው። በውስጡም እሳት ይነድ ነበር፤ ፍሬውንም አላቃጠለውም፤ ይኽም በበረሓው ድንኳን ውስጥ ያስቀመጡትን የወርቅ መሶብ፣ ከሰማይ የወረደ፣ ለዓለሙ ሁሉ ሕይወትን የሚሰጥ የተሰወረ መና ያለበት ነው። ዛሬም ለእግዚአብሔር የተቀደሰና ንጹሕ ቁርባንን እስከምትወልጂ ድረስ (ከጉድፍ) ከጉስቁልና ትጠበቂ ዘንድ አዝዝሻለው። ሥራውንም ለዓለሙ ሁሉ ለልጅ ልጅ ይናገራሉ አላት።" ሐናም ይኽን ነገር በልቧ እየጠበቀች በረከትን ተቀብላ ወደቤቷ ሔደች።

ዘመዶቿና ጎረቤቶቿም በሐና መጽነስ ተደስተው ይጎበኟቸው ነበር። ከእነዚህም መካከል ሀና ቤርሳቤህ የተባለች የአጎቷ የአርሳባን ልጅ ተደንቃ ማኅጸኗን ስትዳስሳት አይኗ በርቶላታል።

ሌላም ሐና የምትወደው ሳሚናስ ወልደ ጦሊቅ በሞተ ጊዜ ተግንዞ ወደተኛበት ሄዳ የአልጋውን ሸንኮር ይዞ በምታለቅስበት ወቅት ጥላዋ ቢያርፍበት ከተኛበት ተነስቶ .. ሰማይንና ምድርን ለፈጠረው አምላክ አያቱ የተባልሽ ሐና ሰላም ላንቺ  ይሁን .. አላት፤ አይሁድም ደንግጠው ምን አይተህ እንዲህ አልክ? አሉት።

እርሱም "ከዚህ ከሐና ማኅጸን የምትወለደው ሕጻን ሰማይ ምድርን የፈጠረ አምላክን ትወልዳለች እያሉ መላእክት ሁሉ ሲያመሰግኗት ሰማኋቸው፤ እኔንም ያነሣችኝ እርሷ ናት" አለ በዚህም አይሁድ በማኅጸን ባለች ጽንሷ እንዲህ ካደረገች በእኛ ልትሰለጥን አይደለምን ብለው በምቀኝነት ተነሳሱባት። መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልም ለኢያቄም ተገልጾ ሐናን ሊባኖስ ወደሚባል ተራራ እንዲወስዳት ነገረው።#ጊዜ_ልደት_በደብረ ሊባኖስ

ሐናና ኢያቄምም በደብረ ሊባኖስ እያሉ ግንቦት 1 ቀን ሐና እመቤታችንን ወለደች። ቅዱስ ያሬድም ይህንን በማሰብ ...ኢያቄም ወሀና ወለዱ ሰማየ፤ ሰማዮሙኒ አስረቀት ፀሐየ። ኢያቄምና ሀና ሰማይን ወለዱ፤ ሰማይቱም ፀሐየ ጽድቅ ክርስቶስን አወጣችልን  ... አለ።

ስለ ጊዜ ልደቷም ሲናገር "በእንተ ልደታ ለማርያም አድባር ኮኑ ኅብስተ ሕይወት ወእምዕጸወ ገዳምኒ ፈረዩ አስካለ በረከት" .. ድንግል ማርያም ስትወለድ ድንጋዮቹ ተራሮቹ ሁሉ የሕይወት እንጀራ (ምግብ) ሆኑ እጽዋትም ሁሉ የሕይወት ፍሬ አፈሩ በማለት ይገልጽልናል።

ሐናና ኢያቄምስ ወላጅነታችሁ ድንቅ ነው። በእውነት በመጽሐፍስ መካን የነበሩ ብዙ ደጋግ ቅዱሳን የተባረከ ልጅን ወልደዋል። እናንተ ግን ለፍጥረተ ዓለም በጸጋ፤ ለፈጣሪ ደግሞ በግብር እናት የምትሆንን ልጅ ወልዳቹሃልና። ለእናንተ ልጅ ናት ለኢየሱስ ክርስቶስ ግን አንድያ እናቱ ናት።

አብርሃምና ሣራ ብሩክ ዘር የሚሆን ይስሐቅን ወለዱ፤ ሐናና ኢያቄም ግን የምድርን አሕዛብ ይባርክ ዘንድ አምላክ የሚወለድባትን ዘር ለዓለም ሰጡ።

ሐና አልቅሳ ለእሥራኤል መስፍን ለቤተ መቅደስም አገልጋይ የሚሆን ሳሙኤልን ወለደች፤ ሐናና ኢያቄም ግን ለአማናዊው ድኅነት መፈጸሚያ የሆነች ቤተመቅደስን ወለዱ።

ራሔል አልቅሳ ያዕቆብንና ዘሩን ከምድራዊ ረኃብ ከጊዜያዊ ሞት ለጊዜው የሚቤዣቸውን ዮሴፍን ወለደች፤ ሐናና ኢያቄም ግን አዳምን ከነልጆቹ ከዘለዓለማዊው ሞት አንስቶ ለዘለዓለማዊ ድኅነት በማብቃት የሚቤዣቸውን ክርስቶስን  የምታስገኘውን፤ እርሷም በፍቅሯ እየጠራች ስለኃጢአታቸውም ምሕረትን እየለመነች የምታድናቸውን መድኃኒት ወለዱ።

ሐናና ኢያቄምስ ከዚህ በፊት ከነበሩት ወላጆች ሁሉ ከበሩ፤ በክብር በሞገስም ከፍ ከፍ አሉ ለአምላክ አያቱ ሆነዋልና፤ ዘርን በማስቀረት ረድኤቱን በማድረግ ለአዳምና ለልጆቹ ሲሰጥ ለነበረ አምላክ እናቱን ስጦታ/መባዕ አድርጋችሁ ሰጥታቹሃልና። ይኸውም መባዕ ቅድሚያ ብቸኛ እናት ልትሆነው የምትችለውን (እስከ እርጅና ያለልጅ የቀራችሁበትን ጊዜ በእምነት ታግሳችሁ ከሌላ ሳትሄዱ) በመውለዳችሁ፤ ሁለተኛም ለእርሱ አገልጋይ ሆና ነየ አመቱ ለእግዚእነ ... እኔ ለጌታ ባሪያው ነኝ .. የምትል ለታላቂቱ አገልግሎት (ለድኅነተ አዳም) የተመረጠች ልጅን ስለሰጣችሁ ነው።

"ሙሽራዬ ሆይ ከሊባኖስ ነዪ፤ ከሊባኖስ ከእኔ ጋር ነዪ ከአማና (ሃይማኖት) ራስ ከሳኔርና ከኤርሞን ራስ ከአንበሶች መኖሪያ ከነብሮችም ተራራ ተመልከች።"

              መኃ 4፥8

ጠቢቡ ሰሎሞን በትንቢት መነጽር ልደቷን ተመልክቶ በሊባኖስ እንደምትወለድ በሳኔር በተመሰለ ከኢያቄም በኤርሞንም በተመሰለች ከሐናም እንደምትወለድ፤ የአንበሶች የነብሮች ተራራ በማለት ከሁለቱ ኃያላን ከቤተ መንግሥት እና ከቤተ ክህነት ወገን እንደምትወለድ ተናግሯል።

የእመቤታችን ልደት የተከናወነው በደጅ፤ ከፍ ባለ ተራራ ላይ ነው። በዚህ መወለዷም የእርሷ ልደት ለዓለም ሁሉ ጥንተ መድኃኒት መሆኑና ለሁሉ የተሰጠች ስጦታ መሆኑን ለማመልከት ነው።

በስደት ላይ ያለ ሰው የላመ የተዘጋጀ ምግብ የለውምና ሐናና ኢያቄም ንፍሮ እየበሉ እመቤታችንን በደብረ ሊባኖስ መውለዳቸውን በማሰብ በዓሉን ከደጅ ወጥተን ንፍሮ በመብላት እናከብረዋለን። በበዓሉም ምዕመናን ለከርሞ ብንደርስ በማለት ብጽዓት/ ስእለት ይሳላሉ። ዕለቱን ከኪዳን ከማኅሌት ከቅዳሴው በመሳተፍ፣ ቅዱስ ቁርባኑን በመቀበል፣ ጸበል በመጠጣት በመጠመቅ፣ የእመቤታችንን የምስጋና መጻሕፍትን በተለይም መልክአ ልደቷን በማድረስ፣ በመመጽወት የታመሙትን የታሰሩትን በመጠየቅ ማክበር ይገባናል።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን።                                 
                              ዋቢ መጻሕፍት
1.መጽሐፍ ቅዱስ የ፳፻ ዕትም
2.ድርሳነ ማርያም
3. መኃልይ መኃልይ ዘሰሎሞን ማብራሪያ በመጋቤ ሐዲስ ስቡሐ አዳምጤ
4. መዝሙረ ዳዊት ትርጓሜ ትንሳኤ ዘጉባኤ እትም
5.የእመቤታችን በዓላት በመ/ር ተስፋሁን ነጋሽና መ/ር ኤርምያስ ወ/ኪሮስ
32 views14:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-09 17:28:25 ያሬዳውያን:
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሕዱ አምላክ አሜን።

ክርስቶስ ተንሥአ እምሙታን በዐቢይ ኃይል ወስልጣን አሰሮ ለሰይጣን አግዓዞ ለአዳም ሰላም እምይእዜሰ ኮነ ፍስሐ ወሠላም።

             ልደታ ለማርያም

{ መሠረታቲሃ ውስተ አድባር ቅዱሳን }
                መዝ 86÷1

እመቤታችን ልደቷ እንደእንግዳ ደራሽ እንደውኃ ፈሳሽ ሆኖ ሳይነገር ሳይታወቅ ሳይጠበቅ የመጣ አይደለም፤ እንደልጇ ሁሉ አበው ሲሿት በምሳሌ ጥላነት ሲያዩዋት፣ ነቢያቱ ሲተነበዩላት ዳዊት ልጄ ሆይ ስሚኝ በማለት ሰሎሞንሞ እቴ ሙሽራዬ እያለ በትንቢት መነጽርነት ሲያናገራት የነበረች ናት እንጂ ።

አስቀድሞ ለአዳም በገባለት ቃልኪዳን ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንኃለው በማለት እርሱ ይወለድባት ዘንድ ያላት የመረጣት የአዳም የልጅ ልጅ እንደምትወለድና ከእርሷም እንደሚወለድ ነግሮታል።

ከዚህ በጎላ እና በተረዳ ግን ነቢዩ ኢሳይያስ "ትወጽእ በትር እምሥርወ እሴይ ወየዓዐርግ ጽጌ እምኔሃ" ... ከእሴይ ሥር በትር ትወጣለች፤ አበባም ከግንዱ ይወጣል ... በማለት በትር ብሎ በትረ አሮን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከእሴይ ሥር ከዳዊት እንደምትወለድና ከእርሷም ጽጌ የተባለ ክርስቶስ እንደሚወለድ ተናግሯል።

የእመቤታችን ልደት ሊቁ "መኑ ይእቲ እንተ ትሔውጽ ከመጎኅ ያላት" ... ይህች እንደማለዳ ፀሐይ ያለች ማናት ... በማለት የገለጣት ለአማናዊው ፀሐይ ጎኅ፤ ለአማናዊው ወንጌል ንዑስ ወንጌል የሆነች የእመቤታችን ልደቷ ለልደተ ክርስቶስ ጎኅ ሆኖልን፤ በእርሷ መወለድ የእርሱን ሰው ሆኖ መወለድ እውን ሆኖልን ያረጋገጥንበት ነው።

ደራሲም ድንግል በልደቷ ለአዳምና ለልጆቹ ከመርገሙ መዳኛ ስለመሆኗ እንዲህ ብሎ ይጠቅሳል :-

ማርያም ድንግል በልደትኪ መጠነ አቅሙ፤
አዳም ይዌድስኪ ምስለ ደቂቀ ኩሎሙ፤
እስመ ለአዳም ብኪ ተስእረ መርገሙ።
        መልክአ ልደታ

የእመቤታችን ልደት ከአምስቱ ልደታት አንዱ የሆነው እንደ ልደተ አቤል ያለ ይኸውም ከእናትና ከአባት የሚወለዱት ልደት ነው። ልደቷም መሠረታቲሃ ውስተ አድባር ቅዱሳን... መሠረቶቿ በተቀደሱ ተራሮች ናቸው..  በማለት ቅዱስ ደዊት "አድባር ቅዱሳን" ብሎ ከገለጣቸው በምድር  ከተነሱት ሁሉ በግብራቸው በጽድቃቸው በትሩፋት በክብር  እንደ ተራራ ከፍ ብለው ከሚታዩት ከተነሱት ከታላላቅ ቅዱሳን ወገን ነው። ታሪክ በእንተ ልደተ ማርያም

ጰጥሪቃና ቴክታ የሚባሉ ደጋግ ቅዱሳን ባለጸጋ ለእንሶቻቸው የወርቅ ጉትቻ እስኪያረጉ ድረስ ሁሉ የተትረፈረፋቸው ሰዎች ነበሩ። እነርሱም መካን በመሆናቸው ያዝኑ ነበር። አብዝተውም እግዚአብሔርን ለመኑት ጠየቁትም  በኋላም ሕልምን አዩ።

ሕልሙንም ሕልም ፈቺ ዘንድ ሔደው ፍቺውን ጠየቁት። እርሱም ነጭ ጥጃ መልኳ ደምግባቷ ያማረ ምግባሯ የተወደደ ሴት ልጅ ናት። እንዲህ አይነቷ እሷን የምትመስል እየወለደች ትሔዳለች፤ የመጨረሻዋ ጥጃ ጨረቃ መውለዷም ከሰማይ ዝቅ ከምድር እና ከፍጥረታት ወገን ግን ከፍ ያለች ልጅ ናት የፀሐዩ ነገር ግን አልተገለጠልኝም አላቸው። እነርሱም ይህንኑ ሰምተው ሄዱ። ሄኤማንን ወለዱ። ሄኤሜን ዴርዴንን፣ ዴርዴን ቶናን፣ ቶና ሲካርን፣ ሲካር ሔርሜላን ወለደች። ሔርሜላና ማጣትም የጌታ አያቱ የምትሆን ሐናን ወለዱ።

ኢያቄም እና ሐና

ከነገሥታቱ ከይሁዳ ወገን የሚሆን ኢያቄም ቀለዮጳ የሚባል አንድ ባለጸጋ ሰው ነበር። እርሱም ከካህናቱ ከነገደ ሌዊ የምትወለደውን ሐናን አገባ። እነርሱም የተቀደሱ ደጋግ ነበሩ። በደቂቀ እሥራኤል ዘንድም አብዝተው መስዋዕትን ያቀርቡ ነበር።

ከእለታት አንድ ቀንም ከደቂቀ እሥራኤል ወገን የሆነ ሮቤል የተባለ ሰው መጣና " በእኛ ፊት መሥዋዕትን ታቀርብ ዘንድ አይገባም፤ በእሥራኤል መካከል ዘር የለህምና" አለው። አይሁድ እና ካህናቱም ልጅ ስለሌላቸው ይንቋቸው ይጠሏቸው፤ መሥዋዕታቸውንም ለመቀበል እምቢ ይሉ ነበር።

ኢያቄምም ፈጽሞ አዘነና ስእለቴን እስኪሰጠኝ ወደእኔና ወደሚስቴም እስኪያይ ድረስ አልመገብም አልጠጣምም ብሎ ሱባኤ ለመያዝ ወደ ገዳም /በረሓ ወጣ። ሰባቱ ሰማያት እንደመጋረጃ ተገልጠው ነጭ ወፍ ወርዶ በራሱ ላይ ሲቀመጥ በራእይ አየ።

ታላቁ የፋሲካ በዓል በደረሰ ጊዜ አንዲት የመንደሩ ሴት ወደሐና መጥታ ለምን ታዝኛለሽ? ራስሽንስ ለምን ትጎጃለሽ? በዓል ስለደረሰ መምህሬ የሰጠኝን ይህንን ልብስ ልበሺ ልብሱ የነገሥታት ልብስ ነውና አንቺ ትለብሽው ዘንድ ይገባሻል አለቻት።

ሐና ግን አዝና ነበርና ብቸኛ በመሆኔ፣ ልጅም ስለሌለኝ ኀዘንተኛ ነኝና ያማረ ልብስን አለብስም፤ ደግሞም ማን እንደሰጠሽ በምን አውቃለሁ? እኔንም ከኃጢአትሽ ልትጨምሪኝ ነውን? አለቻት። ሴቲቱም በምላሹ ተናዳ እግዚአብሔር ማኅጸንሽን በመዝጋቱ ደግ አድርጓል አለቻት።

ሐናም ከቀድሞው አብልጣ አዘነች። ፈጥና ተነስታም ወደቤተ መቅደስ ሔደች። አእዋፋትንም ከልጆቻቸው ጋር ባየች ጊዜ አንስሳት አራዊት ልጆች አላቸው፤ ምድር እንኳን ፍሬ አላት ለእኔ ግን ልጅ የለኝም፤ ለሁሉ ልጅ አለውና ለእነርሱ ልጅን የሰጠህ ወደእኔ ተመልከት ልጅንም ስጠኝ ብላ እያለቀሰች ትጠይቅ ነበር።

ቅድስት ሐና ሆይ እግዚአብሔርስ አንቺን ሳይመለከት ቀርቶ አይደለም። ከተናገረው ቀን ሳያጓድል ይመጣ ይወርድ ይወለድ ዘንድ ያለበትን ጊዜ እየጠበቀ ነበር እንጂ። እነሆም ቀኑ ደረሰ እግዚአብሔርም ወደአንቺ አየ ስእለትሽን ሰማ ልመናሽንም ተቀበለ ልጅንም ሰጠሽ፤ በአንቺም ዘንድ ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬም "ነጸረ አብ እምሰማይ ወኢረክበ ዘከማኪ" ያላትን ከፍጡራን መካከል አምሳያ የሚተካከል የሌላትን አንድያ እናቱን አገኘ።

ቅድስት ሐናም ነጭ ርግብ መጥታ በራሷ ላይ ተቀምጣ ከራሷ ላይም ወርዳ በጆሮዋ ገብታ በማሕፀኗ ስትተኛ በራእይ ተመለከተች። እነሆም በሐምሌ 30 ቀን የጌታ መልአክ (ቅዱስ ገብርኤል) ከሰማይ ወርዶ በፊቷ ቆመ፤ ጸሎትሽ ተሰምቷል ልምናሽንም ተቀብሏል ትፀንሻለሽ አላት። እርሷም ልጅን ከሰጠኝስ እስከ ዘመኑ ፍጻሜው ድረስ እንዲያገለግል ለእግዚአብሔር እሰጣለሁ አለች። መልአኩም ወደ ኢያቄምም ሔዶ ይህንን ብሥራቱን አበሠረው።ኢያቄምም ተደስቶ ሁለት በጎችንና 12 ላሞችን መሥዋዕት አድርጎ አቀረበ።

አንድ ሱባዔ ይዘው ከቆዩ በኋላ እመቤታችን ቅድስት ንጽሕት ብጽእት ድንግል ማርያምም ነሐሴ 7 ቀን በብሥራተ መልአከ በንጹሕ መኝታ ተጸነሰች። ስለ ጽንሰቷም የብሕንሳው ሊቀጳጳስ አባ ኅርያቆስ በቅዳሴ ማርያም ላይ "ኦ ድንግል አኮ በፍትወተ ደነስ ዘተጸነስኪ አላ በሩካቤ ዘበሕግ እምሐና ወኢያቄም ተወለድኪ .... ድንግል ሆይ ኃጢአት ባለበት ሥጋዊ ፍትወት የተጸነሽ አይደለሽም በሕግ በንጹሕ መኝታ ከኢያቄምና ከሐና ተወለድሽ እንጂ... በማለት ንጹሕ ከሆነ አልጋ ንጹሕ ከሆነ መኝታ መገኘቷን ይናገራል። ጠቢቡ ሰሎሞንም.. ወዳጄ ሆይ ሁለንተናሽ ውብ ነው፥ ምንም ነውር የለብሽም።.. (መኃ 4፥7) ብሎ ከማኅጸን ጀምሮ ጥንተ አብሶ እንደሌለባት ያስረዳናል።#ተአምረ_ማርያም_እምማኅፀነ_ሐና
28 views14:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-09 15:29:19 #ግንቦት_1

#ልደታ_ለማርያም

በግንቦት አንድ በዚህችም ቀን አምላክን የወለደች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተወለደች እርሷም ለሰው ሁሉ ወገን ድኀነት የሆነባት ናት። ከወንዶች ወገን የከበረ አባቷም ስሙ ኢያቄም ከሴቶች ወገን የከበረች ሚስቱ ሐና ይባላሉ። ሁለቱም ልጅ በማጣት ሲያዝኑ ኖሩ በዚያ ወራት የመካኖችን መብዓ ካህናቱ አይቅበሉም ነበርና።

እነርሱም ከሰው የሚደርስባቸውን ሽሙጥና ኅዘናቸውን ያርቅላቸው ዘንድ በቀንና በሌሊት ወደ እግዚአብሔር ፈጽሞ ይማልዱ ነበር። ሰውን የሚወድ እግዚአብሔርም ከዘራቸው ለዓለሙ ሁሉ መድኃኒት ይሆን ዘንድ መልካም የሆነ ኀሳባቸውን ተመለከተ።

ክቡር እያቄምም አርባ ቀን እስኪፈጸም በተራራ ውስጥ ቁሞ ሲጸልይ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ ተገለጸለትና ለዓለሙ ሁሉ ድኀነት የሚደረግባት ዘር እንደሚሰጠው አበሠረው።

በፍጹም ልብ አምኖ ከተራራው ወረደ ለተመሰገነች ሚስቱ ለሐናም ከእግዚአብሔር መልአክ የሰማውን ያንን ራእይ ነገራት ቃሉ እውነት እንደሆነ እርሷም አመነች ልዑል እግዚአብሔርንም አመሰገኑት።

የተመሰገነች ቅድስት ሐናም ከእርሷ የሚወለደውን በዘመኑ ሁሉ ለቤተ እግዚአብሔር አገልጋይ ታደርገው ዘንድ ለእግዚአብሔር ስለትን ተሳለች። ከዚህም በኋላ ይቺን የከበረች ሕፃን ፀንሳ ወለደች ስሟንም ማርያም ብላ ሰየመቻት ትርጓሜውም እመቤት ነው ደግሞም ሀብትና ስጦታ ማለት ነው።

በእውነት የዓለሙ ሁሉ እመቤት ናት ሁላችን በእርሷ ሰማያዊ ሀብት ልጅነትን ያገኘንባት። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን የሥጋና የነፍስ መድኃኒት የሆነች እርሷን እናቱን ለሰጠን በረከቷም ከሁላችን የክርስቲያን ወገኖች ጋራ ለዘላለሙ ይኑር አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ግንቦት)
28 views12:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-08 22:25:45 ምስባክ ዘግንቦት ልደታ

ዘነግህ፡-፵፬:፲፪
ምስባክ:-

ወለገጽኪ ይትመሐለሉ ኵሎሙ አሕዛብ ብዑላነ ምድር ፤
ኩሉ ክብራ ለወለተ ንጉሠ ሐሴቦን፤
በዘአጽፋረ ወርቅ ዑፅፍት ወኁብርት።

ወንጌል ፡-ማቴ ፩:፩-፲፰

ዘቅዳሴ
መልእክታት -ገላ. ፬:፩-፲፫
                 -፩ጴጥ. ፩:፰-፲፫
                 -ግብ ሐዋ.፯:፵፬-፶፩

ምስባክ፡-፹፮:፩-፪

መሠረታቲሃ ውስተ አድባር ቅዱሳን፤ ያበድሮን እግዚአብሔር ለአናጽቀ ጽዮን፤
እምኵሉ ተዐየኒሁ ለያዕቆብ

ወንጌል፡-ሉቃ ፩:፴፱-፶፯
ቅዳሴ፡-ዘእግዝእትነ(ጎሥዐ)
https://t.me/bete_zemas
https://t.me/bete_zemas
https://t.me/bete_zemas
36 views19:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-08 07:12:38 ​​❖ ሚያዝያ ፴ ❖
❖ እንኳን አደረሳችሁ ❖

እንዲህ ኃጢአታችን ጽዋዑን ሞልቶ በተረፈበት በዚህ ዘመን አንዲት ሰዓትም ውድ የሆነች የንስሃ ዕድሜ ናት:: እግዚአብሔር ግን ደግ ነውና ይሔው ሚያዝያን አስፈጸመን::

+ ባይገባን ነው እንጂ በዚሕች ወር ውስጥ:-
- ሚሊየኖች በደዌ የአልጋ ቁራኛ ሁነዋል::
- ሚሊየኖችም ለንስሃ ሳይበቁ እንዲሁ አንቀላፍተዋል (ሙተዋል)::

+ እስኪ እርሱ አምላካችን ቀሪዋን ዘመን ደግሞ ለንስሃና ለመልካም ሥራ ባርኮ ይስጠን::

" ቅዱስ ማርቆስ ወንጌላዊ "

በዚሕች ዕለት ከ72ቱ አርድእት አንዱ የሆነ: ወንጌላዊ: ሐዋርያ: ሰማዕት: ዘአንበሳና ርዕሰ ሊቃነ ዻዻሳት የተባለ ቅዱስ ማርቆስ በሰማዕትነት ግብፅ ውስጥ ዐርፏል::

+ ቅዱስ ማርቆስ እናቱ ማርያም: አባቱ አርስጥቦሎስ ይባላሉ:: በልጅነቱ ኦሪትንና የዘመኑን ጥበብ ሥጋዊ በሚገባ ተምሮ ክርስቶስን ከቤተሰቦቹ ጋር ተከትሏል::

+ የመጀመሪያ ስሙ ዮሐንስ ሲሆን ከ120ው ቤተሰብ በእድሜ በጣም ትንሹ (20 ዓመት) እርሱ ነበር:: ለ3 ዓመታት ከጌታ እግር ሥር ተምሮ: በበዓለ ሃምሳ ጸጋ መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ ለሐዋርያዊ አገልግሎት ብዙ ደክሟል::

በተለይ የግብፅና የኢትዮዽያ ቤተ ክርስቲያን አባት ነው:: ክህነትን ያገኘን ከርሱ ነውና:: ቅዱስ ማርቆስ 16 ምዕራፍ ያለውን ወንጌሉን ሲጽፍ ኪሩብ ገጸ አንበሳ በቀኙ: ሊቀ ሐዋርያት በግራው ሆነው ይራዱት ነበር::

ቅዱሱ ክቅዱስ ዻውሎስ: ከበርናባስና ዼጥሮስ ጋር ተጉዟል:: ከብዙ ስቃይና መከራ በኋላ ሰሜን አፍሪካ አካባቢ በዚህ ቀን በ60 ዓ/ም አካባቢ አረማውያን ገድለውታል::

ዳግመኛ በዚህ ቀን የቅዱስ ማርቆስን ወላጆችን እናስባቸው ዘንድ ይገባል::

❖ ቅዱስ አርስጥቦሎስ (አባቱ) የጌታ ቅን አገልጋይ የነበረ፡፡

❖ ቅድስት ማርያም (እናቱ)
- ከ36ቱ ቅዱሳት አንስት አንዷ:
- ጌታችንን ያገለገለች:
-  ቤቷን ለሐዋርያትና ለጌታ በስጦታ ያበረከተች ቅድስት ናት::

+ ቤቷም (ጽርሐ ጽዮን) የመጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያን ስትሆን ይህች ቤት መንፈስ ቅዱስ ወርዶባታል:: የእመቤታችን ግንዘትም ተከናውኖባታል::

❖ እግዚአብሔር ከሐዋርያዊው ቅዱስ ቤተሰብ በረከትን ያድለን::

ሚያዝያ 30 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ማርቆስ ሐዋርያ
2.ቅዱስ አርስጥቦሎስ (አባቱ)
3.ቅድስት ማርያም (እናቱ)

ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት
2.አባ ሣሉሲ ክቡር
3.ቅዱስ ጐርጐርዮስ ነባቤ መለኮት
4.ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት

"+ . . . እጅግ ሰዎች ተከማችተው ይጸልዩበት ወደ ነበረው ማርቆስ ወደ ተባለው ወደ ዮሐንስ እናት ወደ ማርያም ቤት መጣ:: ዼጥሮስም የደጁን መዝጊያ ባንኩዋኩዋ ጊዜ ሮዴ የሚሏት አንዲት አገልጋይ ትሰማ ዘንድ ቀረበች:: የዼጥሮስ ድምጽ መሆኑንም ባወቀች ጊዜ ከደስታዋ የተነሳ ደጁን አልከፈተችም:: ነገር ግን ወደ ውስጥ ሮጣ ዼጥሮስ በደጅ ፊት ቆሞ እንዳለ አወራች::
+" (ሐዋ. 12:12-15)

ዝክረ ቅዱሳን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
https://t.me/bete_zemas
https://t.me/bete_zemas
https://t.me/bete_zemas
39 views04:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-04 11:33:27 ሥርዓተ ማኅሌት ዘልደታ ለማርያም


"ሥርዓተ ነግሥ"
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፤ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኀቤየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፤ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፤ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፤ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፤ በአሐቲ ቃል።

መልክአ ሥላሴ፦
ሰላም ለኲልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፤ ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወጸ በሣሕል፤ እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል፤ ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል፤ ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል።

ዚቅ
ለማርያም ዘምሩ፤ ለማርያም ዘምሩ፤ መስቀሎ ለወልዳ እንዘ ትጸውሩ።

መልክዐ ሚካኤል፦
ሰላም ለልሳንከ መዝሙረ ቅዳሴ ዘነበልባል፤ ወለድምጸ ቃልከ ሐዋዝ ቀርነ መንግሥቱ ለቃል፤ ሞገሰ ክብሩ ሚካኤል ለተላፊኖስ ባዕል፤ አልቦ ዘይትማሰለከ በልማደ ምሕረት ወሣህል፤ እንበለ ባሕቲታ እኅትከ ማርያም ድንግል።

ዚቅ
ተውህቦ ምሕረት ለሚካኤል፣ ወብሥራት ለገብርኤል፤ ወሀብተ ሰማያት ለማርያም ድንግል።

ዘጣዕሙ፦
ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ፤ ለወልድኪ አምሳለ ደሙ፤ መሠረተ ህይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ፤ ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ፤ እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኮት ስሙ።

ዚቅ፦
ወመሠረቱ ወመሠረቱ ለዓለም አንቲ፤ ዕጓለ አንበሳ ዕጓለ አንበሳ በከርሥኪ ፆርኪ፤ እምአንስት ቡርክት አንቲ፤ ለመሠረትኪ የኃትዎ ዕንቊ ክቡር፤ አንቲ ውእቱ መንፈሳዊት ሀገር ንጽሕት ፀምር፤ ዘኃረያ ጸባኦት አማኑኤል።

ነግሥ፦
፪ቱ አዕሩግ አመ በከዩ ብካየ፤ ረከቡ ወለተ ዘታስተሠሪ ጌጋየ፤ ለወንጌላውያን ኲልነ ዘኮነተነ ምስካየ፤ ኢያቄም ወሐና ወለዱ ሰማየ፤ ሰማዮሙኒ አሥረቀት ፀሐየ።

ዚቅ
ምሥራቀ ምሥራቃት መፃአ ፀሐይ፤ እግዝእትነ ዘመና ሙዳይ፤ ተወልደት ዮም ዳግሚት ሰማይ።

መልክአ ማርያም፦
ሰላም ሰላም ለዝክረ ስምኪ ሐዋዝ፤ እምነ ከልበኔ ወቊስጥ ወእምነ ሰንበልት ምዑዝ፤ ማርያም ድንግል ለባሲተ ዓቢይ ትእዛዝ፤ ይስቅየኒ ለለጽባሑ ወይነ ፍቅርኪ አዚዝ፤ ከመ ይሰቅዮ ውኂዝ ለሠናይ አርዝ።

ዚቅ
በሐኪ ማርያም ዘገነት ኮል፤ ዕፀ ጳጦስ መዝገቡ ለቃል፤ ዕለተ ልደትኪ ዮም በጽድቅ ናብዕል።

ወረብ
በሐኪ ማርያም ዘገነት ኮል/፪/
'ዕፀ ጳጦስ'/፪/ መዝገቡ ለቃል/፪/

መልክአ ማርያም፦
ሰላም ለልሳንኪ ሙኃዘ ኀሊብ ወመዓር፤ ዘተነብዮ ወፍቅር፤ ማርያም ድንግል ወለተ ድኁኃን አድባር፤ ኅብዕኒ እምአይነ ፀር ወአንጽሕኒ እምነውር፤ እስመ ተስፋየ አንቲ በሰማይ ወምድር።

ዚቅ
መሠረታቲሃ ውስተ አድባር ቅዱሳን፤ ወብእሲ ተወልደ በውስቴታ።

ወረብ
'መሠረታቲሃ'/፪/ ውስተ አድባር ቅዱሳን/፪/
ወብእሲ ተወልደ በውስቴታ ወብእሲ ተወልደ/፪/

መልክአ ማርያም፦
ሰላም ለአእዳውኪ እሳተ መለኮት እለ ገሠሣ፣ አውቃፈ ብሩር ወወርቅ ለሥርጋዌሆን ኢኃሠሣ፤ ማርያም ድንግል ለመካን ሕንባበ ከርሳ፤ አንጽሕኒ እግዝእትየ ለፍትወተ ዓለም እምርኲሳ፤ በዲበ ሥጋየ ኢትንብር ነጊሣ።

ዚቅ
ኦ ድንግል አኮ በፍትወተ ደነሰ ዘተፀነስኪ፤ አላ በሩካቤ ዘበሕግ እምሐና ወኢያቄም ተወለድኪ።

ወረብ
'እምሐና ወኢያቄም'/፪/ ተወለድኪ/፪/
አላ 'በሩካቤ'/፪/ ዘበሕግ/፪/

መልክአ ማርያም፦
ሰላም ዕብል ለድንግልናኪ ዕጽው፤ እንተ እምኔሁ ሠረቀ ፀሐየ መለኮት ኅትው፤ ማርያም ድንግል ዘስነ ንጽሕኪ ፍትው፤ ለኀዲር በበፍናው በአሕጉር ወበድው፤ ዕቀብኒ ወለቶሙ ለኄራን አበው።

ዚቅ
ወለቶሙ ለነቢያት ይእቲ ማርያም፤ እሞሙ ለሐዋርያት ይእቲ ማርያም፤ ደብተራ ፍጽምት እንተ ኢገብራ ዕደ ሰብእ፤ ዕጹብ ግብረ መናሥግተ ሥጋ ኢያርኃወ ዕጹብ ግብረ።

ወረብ
ወለቶሙ ለነቢያት እሞሙ ለሐዋርያት ይእቲ ማርያም/፪/
ደብተራ ፍጽምት ደብተራ እንተ ኢገብራ ዕደ ሰብእ/፪/

መልክአ ማርያም፦
በዝንቱ ቃለ ማኅሌት ወበዝንቱ ይባቤ፤ ለዘይስዕለኪ ብእሲ ጊዜ ረከቦ ምንዳቤ፤ ብጽሒ ፍጡነ ትሰጠዊዮ ዘይቤ፤ ማርያም ዕንቊየ ክርስቲሎቤ ወምዕዝተ ምግባር እምከርቤ፤ ዘጸገየ ማኅጸንኪ አፈወ ነባቤ።

ዚቅ
ርግብ ፀዓዳ ዘዕንቊ ጽዳ፤ ወዘጳዝዮን ማኅፈዳ፤ ተወልደት ዮም በምድረ ይሁዳ።

ወረብ
ርግብ ፀዓዳ ዘዕንቊ ጽዳ ወዘጳዝዮን ማኅፈዳ ወዘጳዝዮን/፪/
ዮም ተወልደት በምድረ 'ይሁዳ'/፪/ በምድረ ይሁዳ ተወልደት።

ማስረቂያ፦
ሰላም ለልደትኪ እማኅጸነ ድክምት ሥጋ፤ ድኅረ ኃለፋ ውርዙት ወድኅረ ትክቶ ኃደጋ፤ ማርያም ሥመሪ ወጺሐኪ እንበለ ንትጋ፤ ለማየ ንጽሕኪ ትረስዪኒ ፈለጋ፤ እስመ ንጽሕ ይሁብ ሞገሰ ወጸጋ።

ዚቅ
ሐመልማላዊት ሐመልማላዊት ሐመልማላዊት ዕፅ ሙሴ ዘርእያ በደብረ ሲና፤ እግዝእትየ ሙዳዩ ለመና፤ ተወልደት ዮም እምነኢያቄም ወሐና።

ወረብ
'ሐመልማላዊት'/፪/ ዕፅ ሙሴ ዘርእያ በደብረ ሲና/፪/
ተወልደት ዮም እምነኢያቄም ወሐና/፪/

ምልጣን፦
ዮም ፍሥሃ ኮነ በእንተ ልደታ ለማርያም እምሐና ወኢያቄም፤ ከመ ትቤዙ ነቢያተ ወጻድቃነ፤ አማን ተወልደት እመብርሃን።

አመላለስ
'አማን በአማን'/፪/ ተወልደት 'አማን በአማን'/፪//፩/
ተወልደት እመብርሃን/፬/

ወረብ
ፍሥሐ ኮነ ዮም በእንተ ልደታ ለማርያም/፪/
ከመ ትቤዙ ነቢያተ ወጻድቃነ ነቢያተ ከመ ትቤዙ/፪/

እስመ ለዓለም
ልሳንየ ላዕላዕ ይሴብሐኪ፤ እግዝእትየ እብለኪ፤ አዳም ንባብኪ፤ ወመሠረቱ ወመሠረቱ ለዓለም አንቲ፤ ዕጓለ አንበሳ ዕጓለ አንበሳ በከርሥኪ ፆርኪ፤ እምአንስት ቡርክት አንቲ፤ ለመሠረትኪ የኃትዎ ዕንቊ ክቡር፤ አንቲ ውእቱ መንፈሳዊት ሀገር ንጽሕት ፀምር፤ ዘኃረያ ጸባኦት አማኑኤል።

አመላለስ
አንቲ ውእቱ መንፈሳዊት ሀገር ንጽሕት ፀምር/፪/
ዘኃረያ ጸባኦት አማኑኤል/፬/

    # Join & share #
57 views08:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-04 11:33:27 ስርዓተ ዋዜማ ዘግንቦት ልደታ ለማርያም

ሃሌ ሉያ ቆምኪ ርእየትኪ(ርእዮትኪ) ወክሣድኪ ከመ አርማስቆስ፤ እኅትነ ይብልዋ መላእክት በሰማያት፤ ስብሕት በሐዋርያት ኢያቄም ወለዳ ፤ደብተራ ዘትዕይንት፤ ጥዕምት በቃላ ወሠናይት በምግባራ፤ እግዝእትነ ማርያም

ምልጣን፦
ስብሕት በሐዋርያት ኢያቄም ወለዳ ደብተራ ዘትዕይንት፤ ኢያቄም ወለዳ ጥዕምት በቃላ ኢያቄም ወለዳ

አመላለስ
ኢያቄም ወለዳ ኢያቄም ወለዳ/2/
ጥዕምት በቃላ ኢያቄም ወለዳ/4/

ለእግዚአብሔር ምድር በምላዕ፦
ሰአሊ ለነ ማርያም እንተ እግዚእ ኀርያ  ሰአሊ ለነ ማርያም

እግዚአብሔር ነግሠ፦
ኦ ማርያም መንክር ልደትኪ ወዕፁብ ግብርኪ ፤ዓምደ እሳት ፆርኪ ወልድኪ መድኃኔ ዓለም ዲበ ዕፅ ተቀነወ፤ ወዘተዼወወ ሕዝብ በደሙ ቤዘወ

በ፫ት፦
ማርያምሰ እሙኒ ዐመቱኒ በትረ አሮን እንተ ሠረጸት እንበለ ተክል

ይትባረክ፦
እግእዝትየ እብለኪ ለእግዚእየ እብለኪ ቃል ቅዱስ ኃደረ ላዕሌኪ

ሰላም፦
ወኩሉ ነገራ በሰላም ፡ወኩሉ ነገራ በሰላም ሰላማዊት ይብልዋ ለቅድስተ ቅዱሳን ፣ ወኩሉ ነገራ በሰላም ወኩሉ ነገራ በሰላም ጥዕምት በቃላ ወሰናይ ምግባራ ፡ ወኩሉ ነገራ በሰላም ወኩሉ ነገራ በሰላም ንፅህት ይእቲ በድንግልና አልባቲ ሙስና ዕራቁ ደመና፤ ወኩሉ ነገራ በሰላም ወኩሉ ነገራ በሰላም ማርያም ታዕካ በምድር ወታዕካ በሰማይ።

https://t.me/bete_zemas
40 views08:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-03 18:31:19 https://chng.it/6RPdvvmkyB
43 views15:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-30 18:37:12 አመ ዕስራሁ ወሡሉሱ ለሚያዝያ በዓለ ጊዮርጊስ ስርአተ ማህሌት

ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኃቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል።

መልክዐ ሥላሴ
ሰላም ዕብል ለንዋየ ውስጥ ምሕረትክሙ። ትሩፋተ ገድል ኩኑኒ ሥላሴ አምጣነ ትሩፋት አንትሙ። ሶበ ሖርኩሰ ከመ እሳተፍ ገድሎሙ። ጊዮርጊስ ኢወሀበኒ መጠነ ነጥበ ጠል እምደሙ። ወተክለሃይማኖት ከልአኒ ስባረ እምዓጽሙ።

ዚቅ
በደመ ሰማዕት መዋዕያን : ወበገድለ ጻድቃን ቡሩካን : ተሣሃለነ እግዚኦ።

ዘጣዕሙ፦
ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ። ለወልድኪ አምሳለ ደሙ። መሠረተ ሕይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ። ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ። እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኮት ስሙ።

ዚቅ
ጻድቃን ይበውኡ ውስቴታ : የዋሃን የዓውዱ መሠረታ : ሰማዕት ይቀውሙ ዓውዳ : በዕለተ ጊዮርጊስ ስብሐት የዓውዳ ለቅድስት ቤተክርስቲያን።

ነግሥ
ሰላም ለቆምከ ዘአዳም ቆሙ። ወለመልክዕከ በይነ ሰላሙ። ቅዱስ ጊዮርጊስ መክብበ ሰማዕታት ኲሎሙ። ሶበ መተሩ ክሣደከ ምድረ አጥለለት ደሙ። ወጊዜ ሞትከ ብርሃናት ፀልሙ።

ዚቅ
ሶበ መተርዎ ሶበ መተርዎ : ሶበ መተርዎ ለጊዮርጊስ : ፀሃይ ጸልመ : ወወርኅ ደመ ኮነ : ዬ ዬ ዬ : አድለቅለቀት ምድር ወተከሥቱ መቃብራት።

መልክዐ ጊዮርጊስ
ሰላም ለዝክረ ስምከ ዘሰሌዳ ሞገስ መጽሐፉ። ዘያሜኒ ኲሎ ወዘያስተሴፉ። ጥዑመ ዜና ጊዮርጊስ ለሀሊበ ዕጎልት ሱታፉ። ሰላምከ ወረድኤትከ በላዕሌየ ያዕርፉ። አኮ ለምዕር ዳዕሙ ለዝሉፉ።

ዚቅ
ከመ ሀሊብ ዘዕጎልት : ወከመ ወይን ዘገነት : ይጥዕም ስምከ ጊዮርጊስ ሰማዕት።

ወረብ
ከመ ሀሊብ ዘዕጎልት ወከመ ወይን ዘገነት/፪/
ስመከ ይጥዕም "ጊዮርጊስ"/፪/ ሰማዕት/፪/

መልክዐ ጊዮርጊስ
ሰላም ለክሣድከ ዘተመሰለ ምንሐረ። በአንቅዖ ሀሊብ ወማይ አመ በመጥባሕት ተመትረ። ጊዮርጊስ ዘፆርከ ሥቃየ ኲነኔ መጽእረ። በለኒ በቃለ ብሥራት ከመ ነሃሉ ኅቡረ። ጥቃ ቤተ ነፍስየ ለከ ሐነጽኩ ማኅደረ።

ዚቅ
ቅዱስ ጊዮርጊስ ሶበ ተከለለ : ደም ወሀሊብ እምነ ክሣዱ ፈልፈለ።

መልክዐ ጊዮርጊስ
ሰላም ለሕሊናከ ዘመከረ በልባዌ። በሞቱ ወበተንሥኦቱ ለተሳትፎ መርዓዌ። ዓቃቤ ሥራይ ጊዮርጊስ መፈውሰ ደዌ። ለወለት ከመ ቤዘውካ እምአፈ ደራጎን አርዌ። ተረፈ ሕይወትየ ቤዙ እምኲሉ ምንሳዌ።

ዚቅ
ጸርሐ ጊዮርጊስ በዓቢይ ቃል : ወይቤ እፎ ኢይኄሊ ከመ አምላኪየ ተሰቅለ ዲበ ዕፀ መስቀል።

ዚቅ ዓዲ (ወይም)
ሰኪቦ ለወልድ ትንሣኤ ሞቶ : ጊዮርጊስ ወረሰ ሰማያዊተ መንግሥቶ።

ዓዲ ዚቅ
ቀዊሞ ገሃደ ውስተ ዓውደ ስምዕ : ጊዮርጊስ ሰበከ ትንሣኤ ሞቱ ለበግዕ።

ወረብ
ወይቤ ጊዮርጊስ በዓቢይ ቃል ጸርሐ በዓቢይ ቃል ወይቤ/፪/
እፎ ኢይኄሊ ከመ አምላኪየ ተሰቅለ ዲበ ዕፀ መስቀል/፪/

ዓዲ (ወይም)
ጸርሐ ጊዮርጊስ በዓቢይ ቃል ወይቤ በዓቢይ ቃል/፪/
እፎ ኢይኄሊ ከመ አምላኪየ ተሰቅለ ዲበ ዕፀ መስቀል/፪/

መልክዐ ጊዮርጊስ
ሰላም ለፀዓተ ነፍስከ ጽዋዓ ደመ ስምዕ ሰሪቦ። እማኅፈደ ሥጋ በገድል መከራ ስቃይ ድኅረ ረከቦ። ጊዮርጊስ ስመከ ሶበ እጼውእ በአስተርክቦ። ረድኤትከ ኀበ ሀሎኩ በአርአያ ብእሲ ቀሪቦ። ለትካዘ ልብየ ዘልፈ ያሰስል ዕፅቦ።

ዚቅ
ጊዜ ፮ቱ ሰዓት : አጽነነ ርዕሶ #ጊዮርጊስ ወወጽአት መንፈሱ ሶቤሃ።

ወረብ
ጊዜ ፮ቱ ሰዓት "ጊዜ"/፪/ ፮ቱ ሰዓት/፪/
አጽነነ ርዕሶ ጊዮርጊስ ወወጽአት መንፈሱ ሶቤሃ/፪/

መልክዐ ጊዮርጊስ
ሰላም ለበድነ ሥጋከ እምርጢነ ገለአድ ዘተኃርየ። በላዕለ ድውያን ፈወሰ እስመ ፈድፋደ አርአየ። ጊዮርጊስ ለከ ትብለከ ነፍስየ። በበድነ ሥጋከ ተማኅጸንኩ ኢታስተኀፍር ተስፋየ። ስዕለተ ከናፍርየ ስማዕ ወፈጽም ጻህቅየ።

ዚቅ
ፈወሰ ዱያነ ወከሠተ አዕይንት ዕውራን : ወኲሎ ፈጺሞ አዕረፈ ጊዮርጊስ ሰማዕት።

መልክዐ ጊዮርጊስ
ሰላም ለግንዘተ ሥጋከ በዕደ አግብርቲከ ፪ኤ። ድኅረ ሰለጥከ መዊተ እንዘ ብከ ተስፋ ትንሣኤ። ጊዮርጊስ ዘፆርከ ሥቃየ ዓመታት ሱባኤ። ስመከ በተአምኖ ሶበ አወትር ጽዋዔ። አስራበ ረድኤትከ ያጥልል ዘዚአየ ጒርኤ።

ዚቅ
፯ ዓመተ ዘኮነንዎ : ለቅዱስ ጊዮርጊስ ኢመሰሎ ከመ አሐቲ ዕለት : ብእሲ ጻድቅ ቅዱሱ ለእግዚአብሔር።

መልክዐ ጊዮርጊስ
ሰላም ለመቃብሪከ ምክሐ አድያሚሃ ወዓጸዳ። ለምድረ ሙላድከ ልዳ። ጊዮርጊስ ዘልፈ ሀብተ በረከት ዘእፈቅዳ። ከመ ትጸጊ ሕንባበ ረዳ ለኢያሪኮ በዓውዳ። በዲበ ድማኅየ ትጽጊ እምሰማይ ወሪዳ።

ዚቅ
ወረደ ብርሃን ኀበ መቃብሩ ለብእሴ እግዚአብሔር : ወኮነ መቃብሩ ዘየሐዩ ዱያነ : ጸሎቱ ለጊዮርጊስ ወበረከቱ የሃሉ ምስሌነ።

ምልጣን
ዮም ተጽሕፈ እምነገሥት ከላሌሁ በመጥባሕት ለጊዮርጊስ ሰማዕት : ጸለየ ጊዮርጊስ ወአውዓዮሙ በነበልባል : አማን ኃያል ገባሬ ኃይል።

አመላለስ
አማን በአማን ኃያል 'አማን በአማን'/፪//፪/
ኃያል ገባሬ ኃይል/፬/

ወረብ፦
ዮም ተጽሕፈ እምነገሥት ከላሌሁ በመጥባሕት ለጊዮርጊስ/፪/
ጸለየ ጊዮርጊስ ወአውዓዮሙ በነበልባል አማን ገባሬ ኃይል/፪/

እስመ ለዓለም
ወሰበረ ኆኃተ ብርት ሞዖ ለሞት : ተንሥእ ወልድ በሣልስት ዕለት : ወአግዓዘ ነፍሰ ጻድቃን እምጽልመት ወጽላሎተ ሞት : ካዕበ ይቤሎሙ ለአርዳኢሁ : ገሊላ እቀድመክሙ።

እስመ ለዓለም (ዓዲ)
ንግበር በዓለ በትፍሥሕት :በአስተሐምሞ ቅድስተ ፋሲካ ተዝካረ ትንሣኤሁ ለጊዮርጊስ ነገሮ ኅቡዓተ ኲሎ ሥርዓተ ምሥጢር በደኃሪ ይትገበር ዘሀሎ በንዝኃተ ደሙ ለክርስቶስ ለመፃጉዕ ዘአሕየዎ በቃሉ ወለዕውርኒ ዘከሠተ ዓይኖ  ተንሥአ እሙታን ለአልዓዛር ተንሥእ ዘይቤሎ ወለያዕቆብ ዘአዕተዎ ብሔሮ ተንሥአ እሙታን ምዕረ ሦዓ ርእሶ ወተዓውቀ በመንፈሱ በፈቃዱ ወልድ አቅተለ ርእሶ ተንሥአ እሙታን ሲኦለ ወሪዶ ሰበከ ግዕዛነ በመስቀሉ ወልድ ገብረ መድኃኒተ ተንሥአ እሙታን ጸርሐት ሲኦለ ወትቤ ሰማያዊ ዝስኩ ዘለኪፎቶ ኢይክል።

https://t.me/bete_zemas
    #Join & share
62 views15:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ