Get Mystery Box with random crypto!

📖 የ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ 📖 ©ሶፊ

የቴሌግራም ቻናል አርማ bestletters — 📖 የ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ 📖 ©ሶፊ
የቴሌግራም ቻናል አርማ bestletters — 📖 የ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ 📖 ©ሶፊ
የሰርጥ አድራሻ: @bestletters
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.94K
የሰርጥ መግለጫ

ሶፊ 👉 @umsofi27 enjoy ✌
"I don't write words; i write sentiments."
-®Sofi
Do what it worth to live..."
.
.
.
በካፊያ አልደነግጥም የተዘጋጀውት ለዶፍ ነው።
.
.
#💚💛❤
@sofimemo

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

3

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-31 21:56:19
Best wish ever
328 views፲፪ 12, 18:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 21:41:27 ነገ ልደቴ ነው።

የኔ ቀን።
ሶፊ
347 views፲፪ 12, 18:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 21:21:21
ለአቅመ ደራሲነት አልበቃኹም ገና...

ግን

እንደ አቅሚቲ
ይኼ ችግር እኔንም ሳይገጥመኝ አልቀረም "writers block" ።ምንም አዲስ ነገር ማሰብም ኾነ መጻፍ አልቻልኩም።


አዲስ ነገር እስክጽፍ መልካም ጊዜ
ሶፊ
158 views፲፪ 12, 18:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 21:06:45
159 views፲፪ 12, 18:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 20:59:44 ከሶላ እና ሶፊ


.....ዘመን ሲመሽ #2
ጊዜ ሲሸሽ.......



በአባቶቻችን ፍክት ብሎ የነበረው ብርሀን መሽቶ ይታየኛል።ንጋት ይናፍቃል... ንጋት እንኳን ቢኖር እንዳናይ የአይናችን ጉድፍ ሰውሮታል...መልካም ሆነን ተፈጥረን ሳለ መልካሙን መንገድ አልመረጥንም...መልካምነት እምቢኝ፤ክፋት ይግዛን አልን። ሳይሰሩ ውጤት ብቻ ናፋቂ፤ክፋት ዘርቶ መልካም ጠባቂ።የድሎት እና የሆዳችን ተገዢ ከህሊናችን አጉድለን ኪሳችንን የምንሞላ፤ባደረግነው የማንፀፀት ሀፍረት የሌለን ልበ ደንዳና ድፍኖች ሆነናል። የዘራነው ዘር የወፍ ሲሳይ ሆኗል... ትርፋችን ብኩንነት ነው....
...ግብይይቱ ግን ተፋፍሟል.... የማይሸጥም የለም! የተሰረቀ ህንፃ ይሸጣል፤ታሪክ፤ቅርስ እና ማንነት በረከሰ ዋጋ ይሸጣል ። (በዚህም ይሄ ትውልድ ታሪክን አዛብቶ እውነትን ይራባል!)፤ሰው በቁሙ ይሸጣል። የሚገርመው ገዢው! የሚገዛው ወንድሙን፣ሻጩም የሚሸጠው የገዛ ወንድሙን ነው።
#2_ዘመን_ሲመሽ_ጊዜ_ሲሸሽ
የምንፈጥረው ችግር ተበራክቷል...ሰማዩ የምድሩን። ግፍ ያንፀባርቃል...ሀሩር ፀሀይ(እጅግ የሚለበልብ)፣ጭጋግ፣ቁጣ አዘል መብረቅ፣ውርጭ ከክፉ ስራችን የተጠመቀ መራር ፅዋችን ነው።ሁለት አይነት ሰው ሆነናል! ግራ የገባን እና ምንም ያልገባን... ወዴት እንደምንሄድ ያልተገነዘብን፤ ወደፊት እየረገጥን ወደኋላ የሚንራመድ፤ መድረሻውን ስንል መነሻው ጠፍቶን መሀል ቤት የቀረን ሆነናል። ልክ እንደኛ መንገድ የጠፋበትን እንከተላለን....
መብታችን ይከበር ለሚለው ሰልፍ ወተን ነዳጅ ተወደደ! ይቀነስልን!!! የሚለው ሰልፍ ላይ ተሰልፈን እንመለሳለን።...ሰፊ ቤተ-መቅደስ እያለን በጠባቡ አለም እየተጋፋን ነው...ቀኝ እጃችንን ግራ፣ግራ እጃችንን ቀኝ ልናደርግ እንፈልጋለን።የምንፈታተነውን አናውቀውም...ኑሯችን መልክ ብቻ ነው...ግብረገብነት ከህሊናችን ተፍቆ ጥላቻ በደማቁ ተፅፏል(ፍቅራችን ከጥቅም አይዘልም።) ለውጣችን ቁልቁል ነው።በክፋት ጎዳና ላይ ስለሆንን በእኛና በእኛ መካከል ፈጣን ዝግመተ ነውጥ ይታይብናል። ከራሳችን ጋር እንኳን ሰላም የለንም።
#2_ዘመን_ሲመሽ_ጊዜ_ሲሸሽ
ከአፅናፍ እስከ አፅናፍ በጥላቻ ደለል ተደፍነናል...ለተደረገ መልካም ነገር እንጂ ለተደረገው መጥፎ ነገር ሀላፊነቱን የሚወስድ ጠፍቷል...መልካሙን የኔ መጥፎውን የእናንተ ይላሉ።ማንን ማመን እንዳለብን ጨንቆናል ሁሉም በመረጃ አስደግፎ ይዋሻል...
የሚሉንና የምናየው ነገር ለየቅል ነው...በዳዩን ልኮ ሊያፅናን ይመጣል...(የማፅናናት ወይስ የመበደል ፍቅር ያለው???)
ከአካላችሁ አንዱ የናንተ አይደለም...ስለራሳችሁ ከእናንተ በላይ እኛ እናውቃለንም ይሉናል...(ጆሮዬ ነው ወይስ አፍንጫዬ የእኔ ያልሆነው...? )
ከአካላችሁ አንዱ ሲጎል ለውስጣችሁ ሰላም የምታደርጉት መስዋትነት ነው...ወንድማችንን እንዳንወድ ዘረኝነት ጠምዶ ይዞናል...ትስስራችን የመልካም ባህል ትውፊቶቻችን አፈር በልቷቸዋል ጤና ይስጥልኝ ትተን ጤና ይንሳልኝ፤ምነው በደፋልኝ ማለት ከጀመርን ሰነባብተናል... ልባችንም፤ዘመናችንም የክፋት እና የኅጥያት ማደርያ ሆኗል።


ሶፊ ያለው እውነቱን ነው "የደከመ ላይ የሚበረታ እንጂ የደከመን የሚያበረታ ጠፍቷል..."

መመደብ ትወዳላችሁ...

እኔንስ ማን ትሉኛላችሁ ?


"ኤሎሄ...! "
218 views፲፪ 12, 17:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 20:53:15
When pictures talk...

አይ Africa መቼ ይሆን ሰከን ብለን ተረጋግተን ስለ ልማት የምናስበው?
161 views፲፪ 12, 17:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 23:04:11
I love positive energy
334 views፲፪ 12, 20:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 20:42:36 ተወርዋሪ ኮከቤ ነሽ


የሶፊ ደብዳቤ


ቁጥሩ አይታወቅም
389 views፲፪ 12, edited  17:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 20:39:30
ምነው ተለየሺኝ መስከረም ሳይጠበ
እንቁጣጣሽ እያልን ሳናዜም በአበባ

ልቤ እንደ ክረምቱ ለአፍታ አልተረጋጋም የናፍቆትን ካፊያ የፍቅርን ዶፍ ለአጀብ ያዘንባል.......ትዝታን አምርሬ ተፀየፍኩኝ ትዝታሽ እንዳልሆን ፈራሁ......ነበርን ጠላሁት.....አንቺነትሽን በትላንት የትዝታ ግምጃ ቤት መቆለፍ ተሳነኝ በምንስ አቅሜ?........

ፍርሀቴ የአንችስ ፍርሀት ይሆን? እንጃ........

ልቤ እንደ ክረፍቱ ለአፍታ አልተረጋጋም........ፍቅርን ለአጀብ ያዘንባል.....አፀፋሽን ፈራሁት....... ባለቅኔው እንዳሉት ፍቅርን ሳይሆን መለየትን ፈራሁ.....ከራስጌዬ ያሉትን መፅሀፎች መለየትን የሚሰኩኝ መፅሀፎችን ፈራሁ.......አይኖቼን ጨፍዬ በጀርባዬ ተንጋልዬ ያጣጣምኳቸውን የዜማ ስንኞች ዛሬ ለጆሮዎቼ ጎረበጡኝ.........

የማታ ማታ እውነታው በላዬ አፈጠጠ.....መለየት በቦታው ያለ ተቀናቃኝ ሊነግስ ገባ.......ዕድሉን ሊጠቀም ትዝታ የብሶት ቃታውን ሊስብብኝ ተንደረደረ.......ታድያ እኔ ምን ገዶኝ ምናቤን የሙጥኝ ብያለሁ......ምናብ ደጉ.........

ግን.......ሰርክ አንድ ነገር ደጋግሜ አስባለሁ........መልስሽን ባላገኝም ጥያቄዬን ዛሬም ቀጥላለሁ........

"ምነው ተለየሺኝ መስከረም ሳይጠባ
እንቁጣጣሽ እያልንሳናዜም በአበባ"

Nahom እንደከተበዉ
388 views፲፪ 12, 17:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 20:16:30
የሰዉ ልጅ ፥ በዛፍ ላይ ያለን ፍሬ ነዉ ።
ደግሞ ይጣፍጣል ፥
ደግሞ ይመርራል ፥
ደግሞ ያብባል ፥
ደግሞ ይረግፋል ፥
ደግሞ ይዋባል ፥ ደግሞ ይጨነግፋል ፥ የሰዉ ልጅ ፥ በራሱ ላይ እየተነሳ ፥ የሚወድቅ ማዕበል ነዉ ።



------ Photo- Dr Mustefa mahmoud.
361 views፲፪ 12, 17:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ