Get Mystery Box with random crypto!

📖 የ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ 📖 ©ሶፊ

የቴሌግራም ቻናል አርማ bestletters — 📖 የ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ 📖 ©ሶፊ
የቴሌግራም ቻናል አርማ bestletters — 📖 የ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ 📖 ©ሶፊ
የሰርጥ አድራሻ: @bestletters
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.94K
የሰርጥ መግለጫ

ሶፊ 👉 @umsofi27 enjoy ✌
"I don't write words; i write sentiments."
-®Sofi
Do what it worth to live..."
.
.
.
በካፊያ አልደነግጥም የተዘጋጀውት ለዶፍ ነው።
.
.
#💚💛❤
@sofimemo

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

3

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-29 14:51:51
ጠይም ልጅ ነች ፤ ፍልቅልቅ የምትባል አይነት  ።

እወዳታለሁ ፦

ቆንጆ ስለሆነች የምወዳት መስሎኝ ነበር ፤ ባለፈው አሟት አይኗ ግብት እስኪል ከሳች ፤ ጥምልምል አለች ወዟ ጠፋ

አዘንኩላት ፣ አመድማ ስትመስል ፍቅሬ በማዘን በኩል ብቅ አለ ።

ታታሪነቷ ማርኮኝ የምወዳት መስሎኝ ከረመ ፤ ባለፈው በተደጋጋሚ ዝንጉነ'ቷ ምክንያት አለቃዋ ስትከሳት ለእሷ ተቆረቆርኩላት ፤ ሰንፋ ራሱ ለማበርታት አቀድኩ እንጂ ፍቅሬ አልቀነሰም

በእርግጥ ብዙ ጊዜ የዋህ ስለሆነች የምወዳት መስሎኝ ብዙ ዘልቄ ነበር በቀደም ስለ'ኔ ስናወራ ስር ያለው የበቃ አሰላሳይ እንኳ የማይሰነዝረው ጥልቀት ያለው ነገር አብራራች

ስለነጋችን ስናወራ ፣ ስለ ልብ ጓደኛዬ ስነግራት የሰጠችው አሰተያየት ብስል ያለ ነበር ፤ የዋህነቷ ተኗል ወይ የዋህ አልነበረችም ብዬ ብስለቷን መወድድ ጀመርኩ

ፍቅር ማለት የምንወደው ሰው ያለውን ነገር መውደድ ይሆን ?!  ።


                Adhanom Mitiku
433 views፲፪ 12, 11:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 22:36:16 የመጨረሻ ደብዳቤዋ ኃይለ ቃል ይኸ ነበር...

"እንደደከመህ አውቃለሁ ፤ ግን ና፤ መንገዱ በዚህ ነው..."

እንዲህ ብላኝ ቀረኹ።

እናንተም እንደሷ ጨካኝ! ትሉኝ ይኾናል።
ግድ የለም ፍረዱብኝ!
እንኳን የማታውቁኝ እናንተ እሷም ፈርዳብኛለች።

እውነታው...
እንደ ንስር ገለል ብዬ፤በወጣትነቴ ያረጀብኝን ማንነት አፈራርሼ፥አድሼ እመጣለኹ ብዬ ነው... ፈርሼ የቀረኹት።
ይበልጥ ከንቱ ኾኜ ነው የቀረኹት !


ከተቀደደው ማስታወሻ
ሶፊ
560 views፲፪ 12, edited  19:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 21:46:34 ያኔ ነው……የእናቴን ቀሚስ ጨምድጄ እንደያዝኩ፤ ድጋሜ ነፍስን ስንጥቅ የሚያደረግ መብረቅ አንባረቀ የበለጠ ጭምድድ……
"እማዬ ምንድነው የጮኸው?"
"መብረቅ"
"ምን ሆኖ ነው?"
"ወድቆ ነው"
"ማን ጣለው?"
"ማን ይጥለዋል ራሱ ነው የወደቀው"
"አዳልጦት ነው?"
"ምን ይላል ልጁ!……"
ራሱ ወድቆ እንዲህ የጮኸ ሰው ቢጥለው እንዴት ሊጮኽ እንደሚችል አሰብኩት……

ጧት እናቴ የላከችኝን ከሰል ልገዛ ስወጣ ጋሽ መብረቁን ከርቀት አየኋቸው ጤነኛ ናቸው፤ አልቆረጣቸው አልፈለጣቸው፤ እንዳወዳደቃቸውና እንደጩኸታቸው የሚተርፉ አልመሰለኝም ነበር። ያ ሁሉ ድምፅ ከዝች አጭር ሰውነት ነው የወጣው? እግዚኦ… ደግሞስ ራሳቸውን እንደአርበኛ እያዩ እንደ አልቃሻ ልጅ መጮህ አልነበረባቸውም…… ሰመለስ ጋሽ መብረቁን መጥፎ ቦታ ላይ ቆመው አየኋቸው ተንደርድሬ የቤታችንን በር ከኋላዬ ጥርቅም……
"ፈረሰኛው ጊዮርጊስ ምንሆነሀል አንተ?"
"መስኰቱን ዝጊው እማዬ"
ምን መአት መጣ ብላ በድንጋጤ መስኰቱን ድርግም "ምንድነው አንተ?" ለወሬ ጎጉታለች……
"ጋሽ መብረቁ መሰላል ላይ ናቸው እኝህ ተንኰለኛ ሽማግሌ ራሳቸውን ሊጥሉ ነው"

~Tewodros
587 views፲፪ 12, 18:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 15:17:31
የምሽት ጨረቃ ባር ባር በሚል ጣቷ
ገርፋ ስትሞዝቀኝ
እኔም የማላውቀው እርሱም የማያውቀኝ
የሆነ ሩቅ አገር አለ ሚናፍቀኝ


(ኑረዲን ኢሳ)
708 views፲፪ 12, 12:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 21:30:06 ልረሳሽ እየጣርኩ ነው...



ከአዱኛው


በሶፊ


እንዳነብላችኹ የምትፈልጉት አሪፍ ግጥም ካለ በዚህ አድርሱኝ @umsofi27
716 views፲፪ 12, edited  18:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 21:08:30
ነገ "ከተቀደደው ማስታወሻ" ላይ የማጋራችኹ ጽሁፍ አለ... መልካም ጊዜ ሶፊ
692 views፲፪ 12, edited  18:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 20:32:49
"እንዳገባዉ አደለም ያፈቀረኝ የሚያገባዉ አለዉ"

አይኔን እያየ አፈቅርሻለሁ ባለበት አንደበቱ እሷን አቅፎ ቀና እንኳን ሳያደርጋት እወድሻለሁ ማለቱ ለምን እኔጋ ያሶቅሰዋል ? እርቃን ተዋዉቆ ፣ ተዋህዶ ፣ ነፍስ ለነፍስ መናበብ ከቻሉ ወዲያ መጋባት መጨረሻዉ ያደረገዉ ማነዉ ? ነፍሱን (እኔን) አፍቅሮ ህይወቱን (እሷን) ማግባቱ ልክ ከነበር ... አይበቃኝም?

ጀርባ መሰጣጣትም አንዳንዴ ጥሩ እኮ ነዉ ከዐይን አልፎ በነፍስ ትስስር መግባባት ...

ነፍሴ ሸሽታ ማረፊያ ስትፈልግ ካገኘችዉ ጥላ ስር ለማረፍ ያልመረጠችዉኮ ማረፉን ጠልታ አልነበረም አልመች ቢላት እንጂ ... እሱስ ማረፊያዉ ካልተመቸዉስ ...

እና እነሱን ተዋቸዉ የራሳቸዉ ጉዳይ

~MARTA
731 views፲፪ 12, edited  17:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 21:56:16
እንደውም ከእንግዲህ ጠዋት ጠዋት በምስራቅ እየመጣሽ አዲስ ቀን ባታበስሪን ደስ ይለኛል ።

ደህና ነገር የማይሰማበት ቀን!
144 views፲፪ 12, 18:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 21:44:03
168 views፲፪ 12, 18:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 21:30:54
ነገ የማጋራችኹ ጽሁፍ አለ ከተቀደደው ማስታወሻዬ ላይ...እና ጥያቄ አለኝ በአጭሩ ሲሆን ነው ወይስ በረጅሙ ሲፃፍ የሚሻለሁ...(በዛው ምን ያህል ሰው እንደሚያነብ ለማወቅ ነው።)
Anonymous Poll
19%
በአጭሩ
78%
በረጅሙ
3%
እንደው ባይፃፍ
37 voters171 views፲፪ 12, 18:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ