Get Mystery Box with random crypto!

ከሶላ እና ሶፊ .....ዘመን ሲመሽ #2 ጊዜ ሲሸሽ....... በአባቶቻችን ፍክት ብሎ የ | 📖 የ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ 📖 ©ሶፊ

ከሶላ እና ሶፊ


.....ዘመን ሲመሽ #2
ጊዜ ሲሸሽ.......



በአባቶቻችን ፍክት ብሎ የነበረው ብርሀን መሽቶ ይታየኛል።ንጋት ይናፍቃል... ንጋት እንኳን ቢኖር እንዳናይ የአይናችን ጉድፍ ሰውሮታል...መልካም ሆነን ተፈጥረን ሳለ መልካሙን መንገድ አልመረጥንም...መልካምነት እምቢኝ፤ክፋት ይግዛን አልን። ሳይሰሩ ውጤት ብቻ ናፋቂ፤ክፋት ዘርቶ መልካም ጠባቂ።የድሎት እና የሆዳችን ተገዢ ከህሊናችን አጉድለን ኪሳችንን የምንሞላ፤ባደረግነው የማንፀፀት ሀፍረት የሌለን ልበ ደንዳና ድፍኖች ሆነናል። የዘራነው ዘር የወፍ ሲሳይ ሆኗል... ትርፋችን ብኩንነት ነው....
...ግብይይቱ ግን ተፋፍሟል.... የማይሸጥም የለም! የተሰረቀ ህንፃ ይሸጣል፤ታሪክ፤ቅርስ እና ማንነት በረከሰ ዋጋ ይሸጣል ። (በዚህም ይሄ ትውልድ ታሪክን አዛብቶ እውነትን ይራባል!)፤ሰው በቁሙ ይሸጣል። የሚገርመው ገዢው! የሚገዛው ወንድሙን፣ሻጩም የሚሸጠው የገዛ ወንድሙን ነው።
#2_ዘመን_ሲመሽ_ጊዜ_ሲሸሽ
የምንፈጥረው ችግር ተበራክቷል...ሰማዩ የምድሩን። ግፍ ያንፀባርቃል...ሀሩር ፀሀይ(እጅግ የሚለበልብ)፣ጭጋግ፣ቁጣ አዘል መብረቅ፣ውርጭ ከክፉ ስራችን የተጠመቀ መራር ፅዋችን ነው።ሁለት አይነት ሰው ሆነናል! ግራ የገባን እና ምንም ያልገባን... ወዴት እንደምንሄድ ያልተገነዘብን፤ ወደፊት እየረገጥን ወደኋላ የሚንራመድ፤ መድረሻውን ስንል መነሻው ጠፍቶን መሀል ቤት የቀረን ሆነናል። ልክ እንደኛ መንገድ የጠፋበትን እንከተላለን....
መብታችን ይከበር ለሚለው ሰልፍ ወተን ነዳጅ ተወደደ! ይቀነስልን!!! የሚለው ሰልፍ ላይ ተሰልፈን እንመለሳለን።...ሰፊ ቤተ-መቅደስ እያለን በጠባቡ አለም እየተጋፋን ነው...ቀኝ እጃችንን ግራ፣ግራ እጃችንን ቀኝ ልናደርግ እንፈልጋለን።የምንፈታተነውን አናውቀውም...ኑሯችን መልክ ብቻ ነው...ግብረገብነት ከህሊናችን ተፍቆ ጥላቻ በደማቁ ተፅፏል(ፍቅራችን ከጥቅም አይዘልም።) ለውጣችን ቁልቁል ነው።በክፋት ጎዳና ላይ ስለሆንን በእኛና በእኛ መካከል ፈጣን ዝግመተ ነውጥ ይታይብናል። ከራሳችን ጋር እንኳን ሰላም የለንም።
#2_ዘመን_ሲመሽ_ጊዜ_ሲሸሽ
ከአፅናፍ እስከ አፅናፍ በጥላቻ ደለል ተደፍነናል...ለተደረገ መልካም ነገር እንጂ ለተደረገው መጥፎ ነገር ሀላፊነቱን የሚወስድ ጠፍቷል...መልካሙን የኔ መጥፎውን የእናንተ ይላሉ።ማንን ማመን እንዳለብን ጨንቆናል ሁሉም በመረጃ አስደግፎ ይዋሻል...
የሚሉንና የምናየው ነገር ለየቅል ነው...በዳዩን ልኮ ሊያፅናን ይመጣል...(የማፅናናት ወይስ የመበደል ፍቅር ያለው???)
ከአካላችሁ አንዱ የናንተ አይደለም...ስለራሳችሁ ከእናንተ በላይ እኛ እናውቃለንም ይሉናል...(ጆሮዬ ነው ወይስ አፍንጫዬ የእኔ ያልሆነው...? )
ከአካላችሁ አንዱ ሲጎል ለውስጣችሁ ሰላም የምታደርጉት መስዋትነት ነው...ወንድማችንን እንዳንወድ ዘረኝነት ጠምዶ ይዞናል...ትስስራችን የመልካም ባህል ትውፊቶቻችን አፈር በልቷቸዋል ጤና ይስጥልኝ ትተን ጤና ይንሳልኝ፤ምነው በደፋልኝ ማለት ከጀመርን ሰነባብተናል... ልባችንም፤ዘመናችንም የክፋት እና የኅጥያት ማደርያ ሆኗል።


ሶፊ ያለው እውነቱን ነው "የደከመ ላይ የሚበረታ እንጂ የደከመን የሚያበረታ ጠፍቷል..."

መመደብ ትወዳላችሁ...

እኔንስ ማን ትሉኛላችሁ ?


"ኤሎሄ...! "