2023-02-12 23:06:56
"የአውዳሚ ፕሮጀክቱ" ሒደቶች...
[አንሙት አ.]
--
⁽⁽የኦሮሞ ብሔር ግንባታ ፕሮጀክት⁾⁾: አያሌ አውዳሚ ግቦችንና ስትራቴጂዎችን የሚከተል እንደሆነ ባለፉት ዓመታት የነካካቸው ነገሮች ሁሉ ምስክር ናቸው።
⁽⁽ በአንዱ ዓመት እንደ አምስት ዓመት መሥራት⁾⁾ በሚል እየተሮጠበት ያለው የብሔር-ግንባታ ፕሮጀክት ፡ የ"ማፍረስ" እና የ"መልሶ መበየን" ስትራቴጂ የሚከተል መሆኑ አንድ ጉዳይ ነው።
አውዳሚ ቀውሶች መፈልፈልን ጨምሮ ከፕሮጀክቱ ⁽⁽ማሳኪያ⁾⁾ እና ⁽⁽ማስጠበቂያ⁾⁾ መንገዶች ውስጥ ጦርነት፣ ጭፍጨፋ፣ የጅምላ ማፈናቀልን የመሠሉ ስልቶችን የሚከተል መሆኑ አውዳሚነቱንና አፍራሽነቱን የከፋ አድርጎታል።
ፕሮጀክቱ እንዲሳካ "የኃይል አማራጭን" ጭምር ተዘጋጅቶበት፡ በጠረጴዛው ላይ አስቀምጦ የሚንቀሳቀስ በመሆኑ ከእስካሁኑም የባሰ ውድመት ወደፊት ይጠበቃል።
መደበኛ እና ኢ-መደበኛ ሠራዊትን ያቀናጀው የኃይል አማራጭ፡ ኦሮሚያ ክልልን በታሪክ ከፍተኛ የታጠቀ ሠራዊት ባለቤት አድርጎታል። ዛሬም በሐረርጌ ሚሊሻዎችን ሲያስመርቅ ውሏል።
በዚህ ወቅት ከሁሉም ክልሎች ጋር የወሰንና ድንበር ቅራኔ ውስጥ የገባው በአውዳሚ ስልቶች በሚመራው ፕሮጀክት አላማ የተነሳ ነው።
እነ'ቤኒሻንጉል ጉሙዝ የማኦኮሞንና ካማሺ ዙሪያ ወረዳዎችን አስረክበው ዝም ያሉት፡ "አሶሳ የእኛ ነው" በሚለው የጨፌው ፕሮጀክት፡ ወደፊት ክልሉ እንደማይኖር ተረድተውት ሊሆን ይችላል።
እነሐረሪ የተበሉ እቁቦች የሆኑት፣ ድሬዳዋን፡ "ዙሪያዋን የማስተካከል" ሥራዎች የሚሠሩት ፣ በሌሎችም ክልሎች በኢ-መደበኛው ሠራዊት የሚሠራው "አጥቅቶ በር የማስከፈት" ተልዕኮ ክልሎችን በር ዘግቶ ለቅሶ ውስጥ ከቷቸዋል።
አንዳንዶች ወረዳ ተወሮባቸው አዲስአበባ ላይ በሚታደላቸው የባሕል ማዕከል መሥሪያ ካርታ እየተፅናኑ ቀጥለዋል።
ሌላም ሌላም..
መፈናቀልን እንጂ መንቀሳቀስን በሚከለክለው የፕሮጀክቱ አካል ፡ "በኦሮሚያ የሚኖረውን ሌላ ሕዝብ ማስወጣት" እና "ወደ አዲስአበባ እና ኦሮሚያ የሚመጣን ሕዝብ መግታት" በዋና አላማነት እየተሠራበት ነው።
እንደ ማውደሙ፡ ሕዝብን "ማስወጣቱም" ሆነ "አለማስገባቱ" የሚመለከተው ሰሜኑን መሆኑ ግልፅ ከሆነ ቆየ።
ከጭፍጨፋ ተርፈው ተፈናቅለው አዲስአበባ መድረስና መጠለልም ክልክል ነው።
በደብረብርሐን እና በጎጃም መስመሮች እንጂ፡ በናዝሬት ወይ በሐዋሳ አሊያም በአንቦ መስመሮች መታወቂያ እየቀሙ ከመንገድ መመለስ የለም።
ምክንያቱም "ፕሮጀክቱ" :መውጣት እንጂ መግባትን የሚከለክለው "ባሕላዊ-ሰሜንን" ነው።
እነ'ተመስገን ጥሩነህ እና መሠል ብዐዴናውያን ፡ የመጡበት ክልል ማሕበረሰብ "የፀጥታ ስጋት ስለሆነ መግባት የለበትም" ተብሎ ሲመሰቃቀል፣ ልክ ነው ብለው ያስፈፅማሉ።
"ፕሮጀክቱን የማደናቅፍ" አቅም ያለው የኃይል ሚዛን የተፈጠረ ሲመስል፡ ሰበብ ይቀመጥላቸውና ፡ እሥርና ማሳደዱን ከታዘዙት አስበልጠው ይሠሩታል።
ያደጉባትን ቤተክርስቲያን "አፍርሰን እኛን እናስመስላት" ሲባሉ፡ እሺ ብለው ጎዳና ላይ የሠራዊት ልምምድ ያደርጋሉ።
አሉልህ ደግሞ፡ የሆኑ "አማራዎች" !
ይሔ ስርዓት እና መንግስት አንድ ነገር ከሆነ ፡ ⁽⁽አማራዊ ጥቅማችን አይሳካም⁾⁾ ብለው ገትረው የቆሙ! እንዲህ ያለ "የፕሮጀክቱ ስትራቴጂካዊ አጋርነት" በዘርህ አይድረስ!!
ሚሊዮኖች ተፈናቅለው በየድንኳኑ በተቀመጡባት አገር፡ የተፈናቀለ ሕዝብ ያነሳት ይመስል፤ "ፕሮጀክቱ" ስትራቴጂካዊ ተግባር አድርጎ በፈጠረው "የሸገር ከተማ አስተዳደር" በተባለው የአዲስአበባ ዙሪያ፡ "ሕገወጥና የጨረቃ ቤት" በሚል "የብሔር ማፅዳት" እየተፈፀመ መሆኑን የሚኮንን የመንግስት ሹመኛ ጠፍቷል።
የሚሆንባቸውን እያዩ ያሉት ክልሎች "ስለምትበለፅገዋ ኢትዮጵያ" እና "የኢትዮጵያዊነት ሱስ"፡ በሚነገራቸው "የማቆያ ወግ" ታጥነዋል። Because Some are CONVINCED, others are CONFUSED!
Such a Destructive ⁽⁽Nation building project⁾⁾ !!
ሁሉም ቀውሶች እና ውድመቶች "ፕሮጀክቱን" የሚያገለግሉ ናቸው።
እነ'ዲማ ነገዎ፣ ሌንጮ ለታ፣ ወዘተዎች የ50 ዓመታት ናፍቆትና ስሌት በስተርጅና እያስኬዱት መሆኑ እድለኛ ያስብላቸው ይሆን!?
673 views20:06