Get Mystery Box with random crypto!

⁽⁽ሁሉም የኢትዮጵያ መሪዎች የየራሳቸውን ፓትርያርክ ሲሾሙ ስለነበር፡ እኔም የራሴን እሾማለሁ ነው | አንሙት አብርሃም

⁽⁽ሁሉም የኢትዮጵያ መሪዎች የየራሳቸውን ፓትርያርክ ሲሾሙ ስለነበር፡ እኔም የራሴን እሾማለሁ ነው የቀውሱ መነሻ። ሕዝቡን በራሴ ፓትርያሪክ በኩል እቆጣጠረዋለሁ፡ ቤተክርስቲያኗን እበርዛለሁ የሚል አላማ ነው።

ደርግ ገድሎ ፣ ወያኔ ከአገር አሰድዶ የየራሳቸውን ፓትርያሪክ ሾመዋል። የአሁኖቹ ደግሞ ለማሰደድም ለማስነወርም የቻሉትን ሁሉ ካደረጉ በኋላ ሳይሳካ ሲቀር፡ 'የብሔረሰቦች ሲኖዶስ' ብለው ዱርዬዎችን አሠማርተው እየደገፉ ነው።

በሁሉም የአገሪቱ ቋንቋዎች የምታሥተምረውን ቤተክርስቲያን በኦሮምኛ ለማገልገል የሚለው ሽፋን ነው። ስለኦሮምኛ ቋንቋ እያወሩ ስለብሔርሰብ ሲኖዶስ መቋቋም የሚያወሩህ እምነት ሳይሆን ፖለቲካ ስለሆነ ነው። ፓትርያርክ ሆኛለሁ የሚለው አቶ አካለወልድም ቢሆን የኦሮምኛ አገልግሎት አይችልም። በቋንቋው እያገለገሉ ያሉት እነአቡነ ናትናኤል ናቸው። እነሱ ሕገወጥነቱን እና ቤተክርስቲያንን የማፍረስ አላማን እያወገዙ ነው።

ከዚህ ቀደም በመሪዎች ጫና የቤተክርስቲያን ፓትርያርክ እና መሪዎች ሲለወጡ ከነበር እንኳ: ከእንግዲህ ተቋሟ ነፃነቷን የማስጠበቅ ግዴታ አለባት። የክርስቶስ አገልጋይ እንጂ የፌደሬሽን ምክርቤትም አይደለቸም።⁾⁾