Get Mystery Box with random crypto!

⁽⁽የቋሚ ቀውስ ፖለቲካዊ ስትራቴጂ⁾⁾ ቀውስን የቁጥጥር እና ትኩረት መበተኛ አድርጎ የመውሰድ ፖለ | አንሙት አብርሃም

⁽⁽የቋሚ ቀውስ ፖለቲካዊ ስትራቴጂ⁾⁾

ቀውስን የቁጥጥር እና ትኩረት መበተኛ አድርጎ የመውሰድ ፖለቲካ ለአንዳንዶች ከፖለቲካነት ይልቅ በሰዎች ደምና ውድመት የሚቆመር ኢ-ሰብዓዊነት ነው።

ለአንዳንዶች ግን አገርን ሙሉ ለሙሉ ለመቆጣጠር ፣ ተገዳዳሪን ለማስወገድና ለማዳከም፣ ተገዳዳሪ የተደረገን አካል አቅሞችና እሴቶችን በማውደም (Destruction) ለሚሠራ የDeconstruction እና Reconstruction ሥራ ቁልፍ ስትራቴጂካዊ መሣሪያ ተደርጎ ይወሰዳል።

"Permanent crisis justifies permanent control of everybody and everything by the agencies of the central government "

የሚፈጠር ቀውስ የሕዝብን ትኩረት ሰቅዞ በመያዝ ፣ ከቀውሱ ጀርባ የሚሠራውን የማፍረስና የመቆጣጠር ተግባር እንዳይመለከተው ፣ እንዳያጤነው ያደርጋል። ቢያጤነውና ቢመለከተውም በሙሉ አቅሙ ወደመከላከልና ማስቆም እንዳይመጣ ቀውሱ እረፍት አይሰጠውም።

ስለሆነም የተፈለገው ዓላማ እስኪሳካ ፡ ተገዳዳሪ ያሉትን አካል: ከአንድ ቀውስ ወደ ሌላ ቀውስ በማዘዋወር እረፍት ይነሱታል።
"ቋሚ ወይንም የተራዘመ ቀውስ" የቁጥጥርና ውድመት ሒደቱ የአመራር ዘይቤ ተደርጎ ይሠራበታል።

በኢትዮጵያ እየሆነ ያለውም ይሔው ነው !

የግለሰቦች ግድያ ማከናወን ➙የንፁሐን ጅምላ ግድያዎችና ሠፊ መፈናቀል➙ የማይረጋ የካቢኔ ሹምሽር ማከናወን ➙ ለሁለት አመት የዘለቀ ጦርነት ➙ በመሐል ብቅ በሚሉ ፋታዎች ወቅት የታጣቂ ጭፍጨፋ ማስፈፀም➙ ጦርነቱ ፋታ ሲሰጥ የተራዘመ ቀውስ ፍለጋ የእምነት ተቋማት ውስጥ መገኘት ➙ ሌላም ሌላም ቀውስና የታጣቂ ጭፍጨፋዎችን በቋሚነት ማስፈፀም፡ "በቋሚ ቀውስ ፖለቲካ" ስትራቴጂነት እየተሠራበት ነው።