Get Mystery Box with random crypto!

አንሙት አብርሃም

የቴሌግራም ቻናል አርማ animutabraham — አንሙት አብርሃም
የቴሌግራም ቻናል አርማ animutabraham — አንሙት አብርሃም
የሰርጥ አድራሻ: @animutabraham
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.51K

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 11

2022-09-04 13:28:16 የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ለዛሬ እሁድ ነሐሴ 29/2014 ዓ/ም የማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ሳይካሔድ ቀረ።
ፓርቲው የጠራው ስብሰባ ያልተካሔደው ከ45ቱ ቋሚ እና 5 ተለዋጭ አባላቱ መካከል 15 ያሕል ብቻ በመገኘታቸው እና የስብሰባ ኮረም ባለመሟላቱ መሆኑ ታውቋል።

ይህም የሆነው በፓርቲው የጠቅላላ ጉባኤ እና ሪፎርም አጀንዳ ምክንያት በከፍተኛ አመራሮቹ መካከል በተፈጠረው አለመግባባት ምክንያት እንደሆነ አንዳንድ አባላት ገልፀዋል ።
561 viewsedited  10:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-03 16:16:05
665 views13:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-03 09:40:49 የአሜሪካው ልዩ መልዕክተኛ ወደ ኢትዮጵያ ሊያቀኑ ነው

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሐመር በሰሜን ኢትዮጵያ እንደ አዲስ የተቀሰቀሰውን ጦርነት አስመልክተው ለመነጋገር ወደ ኢትዮጵያ እንደሚያቀኑ ተገለጸ።

የፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ጽህፈት ቤት ዋይት ሐውስ ጠቅሶ ቢቢሲ እንደዘገበው አምባሳደር ማይክ ሐመር በዚህ ሳምንት ማብቂያ ላይ ወደ ኢትዮጵያ በሚያደርጉት ጉዞ ዋነኛው አጀንዳቸው የሰሜን ኢትዮጵያው ቀውስ ይሆናል።

ሰኔ ወር ላይ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛነት ኃላፊነታቸውን የጀመሩት አምባሳደር ሐመር፣ ከሳምንታት በፊት ወደ ኢትዮጵያ መጥተው አዲስ አበባ እና መቀለ ላይ ከኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት እና ከትግራይ አመራሮች ጋር መወያየታቸው ይታወሳል።

ባለፈው መጋቢት ወር የሰብአዊ እርዳታን ለማቅረብ ተደርሶ የነበረው የተኩስ አቁም ነሐሴ 18/2014 ዓ.ም. በተቀሰቀሰው ጦርነት ፈርሶ በበርካታ አካባቢዎች ውጊያዎች እየተካሄዱ መሆናቸውን ዘገባዎች ያመለክታሉ።

የትግራይ ኃይሎች እና መንግሥት በአማራ ክልል የሰሜን ወሎ ዞን እና የትግራይ ክልል በሚዋሰኑባቸው አካባቢዎች የተቀሰቀሰውን የአሁኑን ጦርነት በመጀመር አንዳቸው ሌላኛቸውን የሚከሱ ሲሆን፣ በአፋር ክልል በኩልም ግጭት መኖሩ ተገልጿል።  

ባለፉት ቀናት ጦርነቱ ወደ ተለያዩ አካባቢዎች መስፋፋቱ የተነገረ ሲሆን፣ መንግሥት "የህወሓት ኃይሎች ጦርነቱን በተለያዩ ቦታዎች ላይ ከፍተዋል" ሲል ከሷል።

የትግራይ ኃይሎችም አዋሳኝ ከሆኑት የአማራ ክልል ቦታዎች በተጨማሪ በኤርትራ በኩልም መጠነ ሰፊ ጥቃት ተከፍቶብናል ብለዋል።

ልዩ መልዕክተኛው አሁን የሚያደርጉት ጉዞ የተኩስ አቁም ፈርሶ ጦርነት ካገረሸ በኋላ ሲሆን ዋይት ሐውስ ስለ ሐመር ጉብኝት እንዳለው፣ ልዩ መልዕክተኛው ሁሉም ተፋላሚ ወገኖች ጦርነት አቁመው የሰላም ንግግር እንዲጀምሩ የፕሬዝዳንት ባይደንን መልዕክት ያስተላልፋሉ።

ዋይት ሐውስ በሰጠው ማብራሪያ ላይ እንደተመለከተው አሜሪካ “ኤርትራን ተመልሳ ወደ ግጭቱ መግባቷን፣ ህወሓት ከትግራይ ውጪ ጥቃት መቀጠሉን፣ እና የኢትዮጵያ መንግሥትን የአየር ጥቃቶች ታወግዛለች” ብሏል።

ጦርነቱ ሲቀሰቀስ የትግራይ ኃይሎች በአማራ እና በአፋር ክልሎች ውስጥ ጥቃት መክፈታቸውን መንግሥት የገለጸ ሲሆን፣ በሰሜን ወሎ ዞን ውስጥ የምትገኘው የቆቦ ከተማንም መቆጣጠራቸው ተዘግቧል።

በዚህ ሳምንት ደግሞ የትግራይ ኃይሎች ከኤርትራ ጋር በሚያዋስኑ አካባቢዎች የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ሠራዊት በአራት አቅጣጫ ጥቃት ከፍተዋል ሲሉ ከሰዋል።
የጦርነቱን መቀስቀስ ተከትሎ የትግራይ አመራሮች የሰላማዊ ሰዎች አካባቢዎች ናቸው ያሏቸው ቢያንስ ሁለት ቦታዎች ላይ የአየር ጥቃት መፈጸሙን ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ መንግሥት ግን የአየር ጥቃቱ ያነጣጠረው ወታደራዊ ኢላማዎች ላይ መሆኑን በመግለጽ ሰላማዊ ሰዎች ከእነዚህ ቦታዎች እራሳቸውን እንዲያርቁ ማስጠንቀቁ ይታወሳል።  

በተጨማሪም በሰሜን ኢትዮጵያ ለተከሰተው ቀውስ ወታደራዊ መፍትሔ የለውም ያለ ሲሆን፣ ግጭት መልሶ ከማገርሸቱ በፊት ለአምስት ወራት የዘለቀው የሰብአዊ ዕርዳታ አቅርቦት የተኩስ አቁም አበረታች ነበር ብሏል።
ነገር ግን ለሰብአዊ አገልግሎት የቀረቡ እርዳታዎች ለወታደራዊ ጠቀሜታ እየዋሉ መሆናቸው አሜሪካን በጣሙን እንዳሳሰባት መግለጫው ጠቅሷል።

የተባበሩት መንግሥታት የዓለም ምግብ ፕሮግራም የጦርነቱን መቀስቀስ ተከትሎ የህወሓት ኃይሎች መቀለ ውስጥ ከሚገኘው ማዕከሉ በ12 ቦቴዎች የተጫኑ ከግማሽ ሚሊዮን ሊትር በላይ ነዳጅ በኃይል ወስደውብኛል ብሏል።  
የትግራይ አመራሮች ግን ነዳጁን ከወራት በፊት ለድርጅቱ በብድር የሰጡት መሆኑን በመግለጽ የቀረበባቸውን ክስ አስተባብለዋል።

ዋይት ሐውስ ጨምሮም ሁሉም ወገኖች ከግጭት እንዲታቀቡ ጠይቆ፣ ውጥረቱን በማርገብ በተለይ ሰብአዊ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች ሁሉ አቅርቦቱ መልሶ እንዲጀመር ጥሪ አቅርቧል።
ሁለት ዓመት ሊሆነው የተቃረበውን ጦርነት በውይይት ለማስቆም አሜሪካንን ጨምሮ የአፍሪካ ኅብረት እና ሌሎችም ባለፉት ስድስት ወራት ጥረት ቢያደርጉም ይህ ነው የሚባል ውጤት ሳይገኝ ጦርነቱ መልሶ አገርሽቷል።

ትግራይ ክልል ውስጥ ተቀስቅሶ ወደ አማራ እና አፋር ክልሎች የተስፋፋው ይህ ጦርነት በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እንደሞቱበት የሚታመን ሲሆን፣ በመቶ ሺዎች ደግሞ ከቀያቸው ተፈናቅለዋል።
በተጨማሪም በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ በሰሜን ኢትዮጵያ የሚገኙ ነዋሪዎች እርዳታ ጠባቂ ሆነዋል።  
666 views06:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 20:05:11 በወቅታዊ አገራዊ ሁኔታ ላይ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተሰጠ መግለጫ!

ኢትዮጵያ ለሰላም ያላትን የማይናወጥ አቋም በየጊዜው ስትገልፅና ይህንኑ አቋሟን በተግባር ስታረጋግጥ መቆየቷ የአደባባይ ሃቅ ነው፡፡

ሆኖም ስለሰላም የተዘረጉትን እጆች አሻፈረኝ በማለት ለ3ኛ ዙር በሃገራችን ላይ የጥፋት በትሩን የዘረጋው አሸባሪው የህወሓት ቡድን የከፈተውን ጦርነት ተገደን ለመመከት ወደመከላከል መግባታችን ይታወቃል፡፡

የህወሓት አሸባሪ ቡድን ወደ ስልጣን ከመጣበት ጊዜ ጀምሮ በኢትዮጰያውያን ላይ ተነግረው የማያልቁ እልፍ አዕላፍ መከራና ሰቆቃ ሲፈፅም የኖረ እኩይ እና ፀረ ህዝብ ቡድን በመሆኑ የጭካኔ በደሉ በበረታባቸው ኢትዮጵያውያን የጋራ ክንድ ከስልጣን የተወገደው ይህ የአሸባሪ ስብስብ አሁንም ከኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ጋር አብሮ አገራችንን የማፈራረስ ግብ አንግቦ ወረራ ፈፅሟል፡፡

ሆኖም በጀግናው የመከላከያ ሰራዊቻችንና የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች አኩሪ ተጋድሎ የአሸባሪው ቡድን የጥፋት ላንቃ እየተዘጋና ወረራውን በብቃት እየተመከተ ይገኛል፤ ለዚህም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትልቅ ክብርና አድናቆት አለው፡፡ ምንጊዜም ከመከላከያ ሰራዊታችን ጎን መሆናችንን በተግባር እያረጋገጥን ሃላፊነታችንን በብቃት እንወጣለን፡፡

በተመሳሳይ ዛሬም እንደ ትናንቱ በጦርነቱ ግንባር የአማራና የአፋር ንፁሃን ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን ጉዳት ለመከላከልና ጉዳት የደረሰባቸውን ለመደገፍ ያለንን ቁርጠኝነት ተግባራዊ በማድረግ እንቀጥላለን፡፡

ይህ እኩይ ቡድኑና ተላላኪዎቹ አልሆነላቸውም እንጂ በተደጋጋሚ አዲስ አበባንም ለማተራመስ የሽብርና የእርስ በእርስ እልቂት ውስጥ ለመክተት የማያባራ ሙከራዎችን ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡ አሁንም ይህንኑ ቅዠታቸውን ለመፈፀም ሲጥሩ ተስተውሏል፡፡

በተለይም በሃሰት ፕሮፖጋንዳ፤ ህዝብ ከህዝብ የሚያጋጩና አንድነታችንን የሚበትኑ የተፈበረኩ መረጃዎችን በማሰራጨት ፤ በከተማዋ ውስጥ የሽብር ቡድኖቹ የህወሓትና የኦነግ ሸኔን የተለያዩ የፅንፍ አስተሳሰብ የሚረጩ አባላትን በማስረግና የጥፋት ሴሎችን በማደራጀት ፤ ሰላማችንን ለማወክ፤ የጸጥታ ስጋት ለመፍጠርና የእኩይ እቅዳቸውን ለማሳካት በግልጽ እንቅስቃሴ እያካሄዱ ይገኛል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ለረጅም ዘመናት በዘረጋው የሌብነትና የዝርፊያ አደረጃጀቶችና አሰርጎ ባስገባቸው ተላላኪዎች ተጠቅሞ በተለያዩ ወንጀሎችና የኢኮኖሚ አሻጥር በመፈፀም፤ ህብረተሰቡን በማማረር መንግስት ላይ ጫና ማሳደር በሚለው ያረጀ ስልት ለመጠቀም ጥረት እያደረገ ይገኛል፡፡

ከእነዚህ ስልቶችም መካከል፤ በየቦታው ህገ ወጥነትን ማስፋፋትና የመሬት ወረራ እንዲካሄድ በማድረግ፤ የፖለቲካ ግብ ያላቸው የደረቅ ወንጀሎች እንዲስፋፉ በማድረግ፤ የኢኮኖሚ አሻጥር በመፈጸም የኑሮ ውድነት እንዲባባስና ህዝቡ አንዲማረር ለማድረግ የቀን ቅዠታቸውን ለማሳካት ግብ ያደረጉ እንቅስቃሴዎቻቸው በየአካባቢው መታየት ጀምረዋል፡፡

ይህ ከህዝብ ልብ ተተፍቶ የወጣ ሃይል ፤ በህዝብ ውስጥ ሊሸሸግ የሚስችለው አንዳችም እድል እንደሌለው የታወቀ ቢሆንም በማናቸውም ሁኔታ የዚህ እኩይ ተግባር ተሳታፊ ሆነው ያገኘናቸው አካላትም ሆኑ ሰዎች ላይ የማያዳግም ህጋዊ እርምጃ የምንወስድ ይሆናል፡፡
የከተማችን ነዋሪዎችም ወቅታዊ የኑሮ ጫናን ለማቃለል ለበዓል የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን የከተማ አስተዳደሩ በበቂ ሁኔታ በህብረት ስራ ማህበራት በኩል እንዲቀርብ የማድረግ ስራ እየተሰራ መሆኑን በማወቅ ፤ ለህገወጦች እቅድ ተጋላጭ ከመሆን ራሱን እንዲጠብቅ ማሳሰብ እንወዳለን!

በተለይም ቀጣዮቹ ሳምንታት በርካታ ሃይማኖታዊና ህዝባዊ በዓላት የሚከበሩበት ወቅት በመሆኑ እነዚህ በአላት በሰላም እንዲጠናቀቁ የከተማችን ነዋሪ ልክ እንደከዚህ ቀደሙ አካባቢውን ብሎም ከተማውን በንቃት ተደራጅቶ እንዲጠብቅ ፤ ከፀጥታ ሃይሉ እና ከሰላም ሰራዊቱ አደረጃጀት ጋር በመተባበር እንዲንቀሳቀስ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

በየአካባቢው በህገወጥ ድርጊት የተሰማሩ፤ ፀጉረ ልውጦችን፤ የሽብር ወሬ የሚነዙና የኢኮኖሚ አሻጥር ለመፈፀም የሚንቀሳቀሱ እንዲሁም የተለያዩ ህዝባዊና መንግስታዊ አገልግሎቶች እንዲስተጓጎሉ የሚያደርጉ አካላትን ለፀጥታ ሃይሉ በመጠቆም እንዲሁም በማጋለጥ አገራዊ ሃላፊነታችንን እንድንወጣም የከተማ አስተዳደሩ ጥሪውን ያቀርባል፡፡

በመጨረሻም የከተማችን ህዝብና አስተዳደር ከግንባር እስከ ደጀን ለሰራዊታችን አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን እያረጋገጥን ፤ ሁላችንም በየተሰማራንበት ውጤታማ በመሆን የእኩይ ሴራዎችን እያከሸፍን ፤የመዲናችንን ሰላም ዘላቂነት በማረጋገጥና ኢትዮጵያን ለመጠበቅ ከምንጊዜውም በላይ በተደራጀና በተቀናጀ አመራርና ከህዝባችን ጋር እጅና ጓንት ሆነን መስራትን አጠናክረን የምንቀጥል መሆኑን እናረጋግጣለን፡፡

እውነትና ሃቅ ከኢትዮጵያ ጎን ነው፡፡ ኢትዮጵያ የያዘቸውን ምንጊዜም የማይናወጥ የፍትሃዊነትና ፤የሰላማዊነት አቋም የአሸናፊነት ጋሻዎቻችን ናቸው፡፡
ከሩቅ ታሪካዊ ጠላቶቻችን እስከ ቅርብ ባንዳዎች ድረስ ኢትዮጵያን ሊያፈርሱ፣ የሞከሩት ሁሉ አሸንፈን መልሰናቸዋል። ዛሬም እንመልስላቸዋለን!!

አዲስ አበባ በኢትዮጵያውያን የጋራ ትብብርና አንድነት ሃላፊነቷን በብቃት ትወጣለች!!
ኢትዮጵያ ድል እያደረገች ትቀጥላለች!!
አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር
ነሃሴ 22 ቀን 2014 ዓ.ም
አዲስ አበባ
305 views17:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 12:42:21
393 views09:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 18:03:25 ሁመራ ከተማ በተረጋጋ ሁኔታ እንደሚገኝ ነዋሪዎች ገለፁ

ዶቼ ቬለ DW ዛሬ ቀን ላይ ያነጋገራቸው አንድ የከተማዋ ነዋሪ በህወሓት እና በኢትዮጵያ በመከላከያ ሰራዊት መካከል ዉጊያ ካገረሸ ወዲህ በአካባቢው በረከት እና ሸረሪና በሚባል ቦታ ጦርነት እየተካሄደ መሆኑን ገልፀዋል።እሳቸው የሚኖሩበት ሁመራ ከተማ ግን በተረጋጋ ሁኔታ ህይወት በተለመደው ሁኔታ እየቀጠለ መሆኑን ተናግረዋል።
ነዋሪው እንደሚሉት ጠዋት ላይ የመሳሪያ ድምጽ ከሩቅ ይሰማ የነበረ ቢሆንም በአሁኑ ጊዜ ግን ምንም ነገር እንደሌለ ገልፀዋል።
በአካባቢው ውጊያው የተደጀመረው ሌሊት ሲሆን፤ እሳቸው ግን የሰሙት ጠዋት 12 ሰዓት ላይ ነው። የእሳቸው የእርሻ ቦታ በረከት አካባቢ ሸረሪና የሚባል ቦታ መሆኑንም ተናግረዋል ።
ነዋሪው አያይዘውም ህብረተሰቡ ወደ ውጊያ ቦታ ለመሄድ ነቅሎ ነው የወጣው መከላከያ በቂ ነው ያለው ተብሎ ከምድራዊ ከምትባል ቦታ ነው የተመለስ ነው።
ማህበረሰቡ ለሰራዊቱ የተለያዩ ምግብ እና ውሃ ጭኖ እያደረሰ መሆኑንም ነዋሪው በስልክ ገልፀዋል።
ያም ሆኖ በሚኖሩበት በሁመራ ከተማ «ህይወት እንደ ቀጠለ ነው። ሁሉ ነገር እንደበፊቱ ነው።» ብለዋል ነዋሪው
413 views15:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 17:52:50
438 views14:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 14:22:01
546 views11:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 17:33:36 የወልዲያ ከተማ ወቅታዊ ሁኔታ

ከወልዲያ ከተማ ሸሽተው መርሳ ከተማ ከደረሱ በርካታ ነዋሪዎች ወደ ከተማዪቱ የሚመለሱም እንዳሉ ለዶይቸ ቬለ (DW) የዐይን እማኞች ተናገሩ። ከተማዋን ለቅቀው ከወጡት መካከል አንዳንዶች ዛሬ ከሰአት በኋላ ወደ ወልደያ በመመለስ ላይ ነበሩ ሲሉም አክለዋል። ከቀኑ ዐሥር ሰአት አካባቢ ዶይቸ ቬለ በስልክ ያነጋገራቸው አንድ የወልዲያ ነዋሪ «የባጃጅ እና የሰዎች እንቅስቃሴ» መኖሩን ተናግረዋል። መብራትም፣ ኔትወርክም እንዳለ እኚሁ ነዋሪ አክለዋል። በብዛት ሰዉ ከከተማዪቱ ወጥቶ የነበረው ትናንት ማታ እና ዛሬ ጠዋት እንደነበር፤ በአሁኑ ወቅት ግን ወደ ከተማዪቱ የሚገባም የሚወጣም እንዳለ የዐይን እማኙ ተናግረዋል።

መርሳ ከተማ እንደደረሱ የተናገሩ አንድ ግለሰብ ደግሞ ከራያ ቆቦ ተፈናቅለው በወልደያ በኩል መርሳ ከተማ መግባታቸውን ገልጠዋል። ከቅዳሜ አንስቶ ቀኑን ሙሉ በእግር እንደተጓዙ የተናገሩት እኚሁ ተፈናቃይ፦ ወልዲያ የገባሁት እሁድ ጠዋት ነው ብለዋል። እስከ ትናንት ድረስ በርቀት ተኩስ ይሰሙ አንደነበረም ነዋሪው አክለዋል።

ሌላኛው የወልዲያ ከተማ ነዋሪ መሆናቸውን ለዶይቸ ቬለ የተናገሩ ግለሰብ፦ ሰዎች «ተራ ወሬ ሰምተው ነው የኼዱት» እንጂ ከተማው ውስጥ ምንም የለም ብለዋል። ሆኖም «ከተማ ውስጥ ያለውን ነዋሪ በድምፅ ማጉያ እየዞረ የሚያረጋጋ የለም» ሲሉም አክለዋል።

ደሴ ከተማ እንደገቡ ለዶይቸ ቬለ የተናገሩ አንዲት ነዋሪ በበኩላቸው፦ «እስከ ሦስት ሺህ ብር ድረስ ከፍለው የመጡም አሉ» ብለዋል። «የራሳችን መኪና ስለነበረን ቀጥታ ነው የመጣነው» ሲሉ እንዴት ደሴ ከተማ እንደደረሱ አብራርተዋል። ደሴ ከተማ ተፈናቃዮችን ለማስተናገድ ከአቅሟ በላይ ነችም ብለዋል።

የአማራ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ የሰሜን ወሎ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዲያቆን ተስፋሁን ባታብልን ጠቅሶ ዛሬ ከሰዓት በኋላ በይፋዊ የፌስ ቡክ ገፁ ባሰራጨው ዘገባ «ወልድያ በጠላት እንደተያዘች የሚሰራጨው መረጃ ሐሰት መኾኑን ዞኑ አረጋግጧል» ብሏል።
462 views14:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 16:31:12 ከደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ምክር-ቤት የተላለፈ ወቅታዊ መልዕክት።

የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ምክር ቤት ወቅታዊ የፀጥታ ስጋትን አስመልክቶ የሚከተሉትን ውሳኔዎች አስተላልፏል።
1ኛ. በከተማ አስተዳደሩ በተፈናቃይ መጠለያ ጣቢያ ውስጥ የሚኖር ተፈናቃይ ከምሽቱ 12:00 ሰዓት በኋላ ወደ መጠለያ ጣቢያውም ሆነ ወደ ከተማው መግባት ክልክል ነው።
2ኛ. በከተማው የሚገኙ ሁሉም አይነት ተሽከርካሪዎች ከምሽቱ 2፡00 ሰዓት በኋላ መንቀሳቀስ ክልክል ነው ይህን ሲያደርግ የተገኘ ባለባጃጅ ህጋዊ እርምጃ ይወሰድበታል።
3ኛ. በከተማው የሚገኙ መጠጥ ቤቶች ምግብ ቤቶች ምሽት ጭፈራ ቤት እስከ ምሸት 2:00 ሰአት ብቻ አገልግሎት እንዲሰጡ ወስኗል።
4ኛ. በከተማው በሚገኙ የንግድ ቤቶች የምርት የዋጋ ጭማሪ ማድረግ በጥብቅ የተከለከለ ነው።
5ኛ. ከተፈቀደላቸው የፀጥታ ሀይሎች ውጭ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ ፈፅሞ የተከለከለ ነው
6ኛ. ከመንግስት ዕውቅና ውጭ የሚደረጉ ማናቸውም አይነት ውይይቶችና ስብሰባ ማድረግ በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡
7ኛ. የጠላትን ሀሳብና እንቅስቃሴ በመደገፍ አሉባልታና ወሬን ማሰራጨት በህብረተሰቡ ላይ ሽብር መንዛት በጥብቅ የተከለከለ ነው።
8ኛ. አዳር የሚሰሩ በከተማችን ያሉ ፍብሪካዎችና ድርጂቶች ድርጁቱ በሚሰጣቸው ህጋዊ መረጃ ና በፀጥታ መዋቅሩ የተረጋገጠ የይለፍ ከያዘ ብቻ መንቀሳቀስ ይችላል፡፡
9ኛ. መላው የከተማው ማህበረሰብ በአደረጃጀት አካባቢውን ቀንና ሌሊት ከሰርጎ ገቦች በንቃት መጠበቅ አለበት።
10ኛ. በከተማ አስተዳደሩ ፀጉረ ልውጥ ሲያጋጥም በፍጥንት ለህግ አካል ጥቆማ በመስጠት በህግ ቁጥጥር ስር እንዲውል ማድረግ ከማህበረሰቡ ይጠበቃል።
11ኛ. የከተማው ባለሆቴሎች እና አልጋ አከራዮች ማንነቱ ያልታወቀ የታጠቀ ግለሰብ በድርጅታችሁ ሲያጋጥማችሁ ለህግ አካላት ጥቆማ እንድትሰጡ።
12ኛ. በከተማ አስተዳደሩ ያላችሁ የቤት አከራይዎች የምታከራዩትን ግለሰብ ማንነትት መታወቂያ በመጠየቅ ለይታችሁ እንድታከራዩ የተከራዩንም መረጃ በፎርም በመሙላት ለከተማው ሰላምና ፀጥታ መምሪያ እንድታሳውቁ መልዕክት አስተላልፏል።
ይህ የውሳኔ ሀሳብ ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን ከላይ በዝርዝር የተቀመጡትን የውሳኔ ሀሳቦች የሚጥስ ማንኛውም አካል ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድበትም የከተማ አስተዳደሩ አስታውቋል።
የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር
ነሐሴ 24/12/2014 ዓ.ም
478 views13:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ