2024-03-28 01:34:18
“ሙሽራ መስሎ ወጥቶ ቀረብኝ…”
ለእናት የልጅን መርዶ መስማት ምን ያህል ከባድ እንደሆነ መገመት አይከብድም።
በቅጽበት ምን እንደሚፈጠር በማይታወቅበት ጦርነት ውስጥም ቢሆን ልጅን ማጣት የሚያደርሰው የልብ ስብራት በቀላሉ አይሽርም።
እኝህ በእስራኤል የቦምብ ጥቃት ልጃቸውን ያጡ ፍልስጤማዊ እናትም “ማታ አብረን ራት በልተናል፤ ጠዋት ሲወጣም እንደ ሙሸራ አምሮበት ነበር” እያሉ በመብሰክሰክ ሀዘኑ መሪር ሆኖባቸዋል።
እስራኤል ባለፉት 24 ስአታት በጋዛ በፈጸምችው ጥቃት በጥቂቱ 76 ሰዎች ህይወታቸው ማለፉ ተገልጿል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁም አለማቀፉ ጫና ከ32 ሺህ በላይ ሰዎች ህይወት የቀጠፈውን ጦርነት እንደማያስቆመው ነው የተናገሩት።
አል ዐይን
10.7K views22:34