2022-03-03 01:42:39
ሰዎች በጣም ሊያሳዝኑሕና ልብሕን ሊሰብሩ የሚችሉት
1,በልብሕ ትልቅ ቦታ እና አክብሮት ሰጥተሀቸው ወርደው ሲገኙብሕ ነው እነዚሕን ሰዎች አትጥላቸው ነገር ግን በተደጋጋሚ ካደረጉት ያልተገነዛዘባችሁት ነገር አለ ራቃቸው ።
2,በዛን ሰሞን ስሜትሕ እና አዕምሮሕ አልተረጋጋም ስስ ሆነሕ ነበር ሰላም ወደሚሰማሕ ቦታ ሒድና በቅድሚያ ራስሕን አረጋጋ ስለ ራስሕ ለማሳመን ለመናገር አትሞክር የበለጠ ትጎዳለሕ መልካም መልካም ነገሮችን ብቻ አስብ ክፉ ኃሳቦችን ተቃወም።
3,ለሚጠሉሕ ወይም ለሚቀኑብሕ ሰዎች ተመቻችተሕ ተገኝተሀል ማለት ነው ራስሕን ጠብቅ ያንተ ወደሆኑትና ሰላም ወደሚሰጡሕ ሒድ ።
4,የሰውን ደካማነት ረስተሀል ለመፍረድ አትቸኩል አንተም እኔም በጣም ደካሞች ነን ስለዚሕ ቆይ ለምን ? እያልክ ሰውን አትመዝን ለምን?ላልከው ነገር መልስ አታገኝም ከሰው ምንም አትጠብቅ ፈራጅ እንዳትሆን ከዚሕ ጥያቄ ውጣ ።
5,አንተ እግዚአብሔርን ምን ያሕል እንደምታሳዝነው ሊያስረዳሕ ይሆናልና ይቅር በለኝ ብለሕ ንስሃ ግባ ።
6,ሰዎች ስለ አንተ የሚያወሩት 70 ወይም 80% ስለ አንተ ማንነት ሳያውቁ በመሰላቸው ነው ነገር ግን እነሱ ምንም ቢሉ አትገረም ንቀሕ ስቀሕ እለፈው አትናደድ ።
7,የምትቀናበት የምትጠላው ሰው ሲናገር ስላልጣመሕ ወይም ለመቃወም ስለምትፈልግ ይሆን? እንዲሕ ሲሆን ውስጥሕ እየተበላ እየተሸረሸረ ያልቃል ከዚሕ ፈጥነሕ ውጣ ሰውዬውን አዝለሕ ተራራ እየወጣሕ እንደሆነ አስበው ዓላማሕን እንዳያሰናክልብሕ ተወው ።
8,በቃ ከሆነ ምንም አዲስ ነገር የለውም ይሕ በሁሉም ሰው ሕይወት የሚፈጠር ነው ብለሕ እለፈው ።
መልካም ደስ የሚል ቀን ይሁንልን
አልዓዛር
https://t.me/alazaryehiwotmiker
https://t.me/alazaryehiwotmiker
https://t.me/alazaryehiwotmiker
551 views22:42