Get Mystery Box with random crypto!

አንድ ሰው በቀላሉ ገነትን ወደ ሲኦል መቀየር ይችላል ከጥቂት ዓመታት በፊት የሚ | የሕይወት ምክር (PSYCHOLOGY)

አንድ ሰው በቀላሉ ገነትን ወደ ሲኦል መቀየር ይችላል


ከጥቂት ዓመታት በፊት የሚገርም ነገር ተፈጥሮ ነበር የሆኑ ጥንዶች ወደ እኔ መጡ እግዚአብሔር ታላቅ ውበት እንደሰጣቸው ግልጽ ነው በሕይወት እንደነሱ የሚያምሩ ጥንዶች አላየሁም የቅዳሴውን ሥነ ሥርአት ካጠናቀቅን በኋላ ሊያነጋግሩን ፈለጉ ‹‹አንዳንድ ችግሮች ገጥመውን ነው ››አለኝ


እኔም ሰማኋቸው ነገሩ እንዲህ ነበር ባለትዳሮቹ የተጋቡት በፍቅር ነው ለዓመታትም በመቻቻል ሰላማዊ ሕይወትን ይኖሩ ነበር በቤተሰባቸው የነበረው ድባብ ገነት ነውን ያስብል ነበር ከዚያም በቅርቡ በእያንዳንዱ ጥቃቅን መጣላት ጀመሩ በቤታቸውም ውስጥ የነበረው ሰላም ደፈረሰ የከፋው ነገር ግን ትንሽ የ6ዓመት ወንድ ልጅ በመኖሩ ነው አስቀድሞም ወደኔ የመምጣታቸው ምስጢር እርሱ ነበረ ልጁ ከአያቶቹ ጋር ብቻ መሆን እንደሚፈልግና እራሱን ከነሱ እንዳገለለ ሊያናግራቸውም እንኳን እንደማይፈልግ ነገሩኝ ፡፡

‹‹የሚፈልገውን ሁሉ እንገዛለታለን እርሱ ግን ሁል ጊዜ ዝም ይላል መጫወቻ፤ልብስ ከረሜላ ስንገዛለት ከፊታችን ወስዶ አጨማዶ ይጥለዋል ከዚያም እኛን ብቻችንን ጥሎን ወደ አያቶቹ ይሄዳል፡፡ በጣም ጤነኛ ነው ሌላም ምንም ችግር የለበትም ግን ከኛ ጋር አንዳች ነገር ማድረግ አይፈልግም ምን ማድረግ እንዳለብን አናውቅም ይህ ሁሉ የሆነው ለምንድነው?>> እኔም ልጃቸው እንዲህ ያሉ ወላጆችን እንደማይፈልግ ግልጽ ነው ደጋግሞ እናት እና አባቱን ፈለገ ግን ሊያገኛቸው አልቻለም ፡፡
‹‹የወላጆቻችሁ ምርቃት ስለነበራችሁ ደስተኞች ነበራችሁ በጥምረታችሁም አንዳች ተቃውሞ አልነበራችሁም በተቃራኒው ጋብቻችሁን እንኳን ያሰናዱት እናንተ ከመተያየታቸችሁ በፊት ነበር የቤተሰባችሁም ቡራኬስለነበራችሁ በፍቅር ተጣምራችሁ በሕብረታቸውም ውስጥ ሰላም ነበር ቤታችሁም እንደ ገነት ነበር አሁን ግን በኃሳባችሁ ምክንያት ሁሉም ነገር ተበላሽቷል እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ አንዳችሁ ለሌላችሁ በቂ ነበራችሁ ሌላም አትመኙም አሁን ግን አንተ ወደ ሌሎች ሴቶች በዝሙት በመመልከት ልብህን አሳልፈህ ትሰጣቸዋለህ ሚስትህም ወደ ሌሎች ወንዶች በዝሙት በመመልከት ልቧን አሳልፋ ትሰጣቸዋለች አሁን ያለው ሕብረታችሁ በሥጋ ብቻ ነው እንጂ አዕምሮአችሁ በተለያየ አቅጣጫ እየባከነ ነው ፡፡


ከጋብቻ ቃል ኪዳናችሁ ወሰን ውጪ ስላልወጣችሁ እግዚአብሔር ይመስገን ልጃችሁ ይህ ሁሉ ይሰማዋል እናም እንዲህ ያሉ ወላጆችን አይፈልግም ምክንያቱም እርስ በእርሳችሁ መራራቃችሁ ብቻ ሳይሆን እራሳችሁን ከሱ በማግለላችሁ ጭምር ነው እናንተ እራሳችሁ በገዛ ኃሳባችሁ በቤታችሁ ውስጥ ሲኦልን ፈጠራችሁ እናት እና አባት እያሉን በቁማቸው እነሱን ማጣት እጅግ ያማል ወደ እርስ በእርሳችሁ ተመለሱ እንደ ቀድሞአችሁም ሁኑ ከዚያም ሁሉም ነገር ይስተካከላል፡፡
አባ ታድዮስ ዘሰርቢያ
አልዓዛር

https://t.me/alazarsayehiwotmiker

https://t.me/alazarsayehiwotmiker