Get Mystery Box with random crypto!

እንደ አጠቃቀምህ ነው ******************************** ስልክ ስገዛ ስልክ ለሚሸ | የሕይወት ምክር (PSYCHOLOGY)

እንደ አጠቃቀምህ ነው
********************************
ስልክ ስገዛ ስልክ ለሚሸጥልኝ ሰው እንዲሕ አልኩት ባትሪው ምን ያሕል ይቆያል? ልጁም ባትሪው በጣም አሪፍ ባትሪ ነው ነገር ግን ደግሞ ዎናው አጠቃቀምሕ ነው አለኝ አጠቃቀሜ ምን ሆነ ? ያው አወራበታለው ፋይል እላላክበታለው ኢንተርኔት እጠቀምበታለው ሌላ ምንም አላደርግም አልኩት እርሱም እነዚሕ ምን ምን እንደምትጠቀም ነው የነገርከኝ ነገር ግን በምን ያሕል መጠን በምን ያሕል ጊዜ የምትጠቀመው የሚለው ነው የባትሪውን ሕይወት ሚወስነው ሲለኝ ደነገጥኩ ሕይወት ሲል ሕይወቴ ትዝ አለኝ ለምሳሌ እኔ ፈጣሪዬን የኔ ሕይወት ምን ያሕል ይቆያል ብለው እንደ አጠቃቀምሕ ነው እንደሚለኝ ተሰማኝ፡፡


ይህች ዓለም በውስጥህ ገነትም ሲኦልም የመሆን እድል አላት ለካ ዎናው አጠቃቀማችን ነው አንዳንድ ሰው ጊዜ እንደ ቁንጣ ሲያጥረው አንዳንዱ ደግሞ ቀኑ አልመሽ ሰዓቱ አልሔድ አለኝ እያለ ጊዜውን በምን እንደሚያጠፋው ሁሉ ያስባል ሕይወት እኛው እንደተጠቀምንበት ነው የሚሆነው እዚህ ምድር ላይ ለሁሉም የራሱ እድል አለው የሕይወት እና የመኖር ጥበብ ሲገባህ ከራስህ አልፈህ ለሌሎችም መኖር ማሰብ ትጀምራለህ ካልሆነ ደግሞ ለራስህም መኖር አትችልም ፡፡


አንዱ ከሌላው ወይም እርሱ ከኔ ለምን ተለየ ካልክ ሕይወት ላይ ባለህ አረዳድና ሕወትን የምትጠቀመምበት መንገድ ነው ዋናው ጉዳይ የአዕምሮ፤የጊዜ፤የገንዘብ እና የጉልበት አጠቃቀማችን ነው በኑሮ የመለያየታችን ምስጢር ፡፡


አዕምሮህን እንዴት እየጠተቀምከው ነው? ስለ አዕምሮ አሠራር ምን ታውቃለህ? አዕምሮህ ውስጥ ስላለው የኃሳብ ሞገድ ምን ትረዳለህ? ሕልምሕስ በአዕምሮህ ውስጥ አለ ወይ? ጊዜ ምንድነው ለአንተ የጊዜ አሠራሩ ምን ይመስላል? ጊዜህን ምን ላይ እያዋልከው ነው? ገንዘብ እንዴት ነው የሚመጣው? ገንዘብን እንዴት ነው የምታሠራው? ለምን ጉዳይ ትወጣለሕ ትወርዳለህ ኃይልህን እያባከንክለት ያለው ጉዳይ ምንድነው? መስዋዕትነት የምትከፍልለት ጉዳይስ እንዴት ታየዋለህ? እነዚህን ጥያቄ ለራስህ ስታቀርብ አንድ የሚገለጽልህ ነገር ይኖራል::
ሁሉም ነገር እንደ አጠቃቀምህ ነው ……
አልዓዛር
https://t.me/alazarsayehiwotmiker
https://t.me/alazarsayehiwotmiker
https://t.me/alazarsayehiwotmiker