Get Mystery Box with random crypto!

እነዚህ የሕይወት መመሪያዎች ላንተ እጅግ አስፈላጊ እንደሆኑ አምናለው +++++++++++++++++ | የሕይወት ምክር (PSYCHOLOGY)

እነዚህ የሕይወት መመሪያዎች ላንተ እጅግ አስፈላጊ እንደሆኑ አምናለው
++++++++++++++++++++++++++++++
1. ትልልቅ የሕይወት ውሳኔዎችን ተረጋግተህ ደጋግመህ አስብ ወስነህ ደግመህ እንዳትጸጸት
2. ራስህን የምትረዳበት መንገድ አስተካክል ጥንካሬህን ወይም ድካምህን በሰው ልኬት አትለካው አንተ ከራስህ ዕቅድ ጋር ተወዳደር
3. ችግርን አግዝፈህ አትይ ለችግር ቦታ አትስጥ መፍትሔው ላይ ብቻ ትኩረት ስጥ ቅን ኃሳቦችን ብቻ ተቀበል አሉታዊ ኃሳቦችን በጣም ችላ በል
4. ለሁሉም ሰው ጥሩ ለመሆን አትሞክር
5. የምታደርገውን መልካም ነገር መልሱን ከሰው አትጠብቅ ስለ እግዚአብሔር ስትል ብቻ አድርገው ብድራቱንም ከርሱ ጠብቅ
6. ደምቀው አምረው ከሚታዩ ነገር ግን ውስጣቸው መከራና ስቃይ ከሆኑ ጉዳዮች ራስህን ጠብቅ ናቀውም
7. ደስታን ውጪ ካሉ ነገሮች ለማግኘት አትሞክር ሲሳካልኝ ደስተኛ እሆናለው አትበል ደስተኛ ስትሆን ነው ሚሳካልህ
8. ዓላማ እና ዕቅድ ይኑርህ የት መድረስ ምን መሥራት እንደ ማን መሆን ነው የምትፈልገው ይህን መጀመሪያ ለራስህ መልስ የዕውር ጉዞ እንዳይሆንብህ
9. በጣም ስለሠራህ ሳይሆን በጣም ስላሰብክ ነው ስኬታማ የምትሆነው እነዚህን አስብ ሕልሜ ምንድነው? እንደማን መሆን ነው የምፈልገው? ምን መሥራት ነው የምፈልገው?
10. ነገ እሠራለው ዛሬ ልረፍ አትበል ዛሬ ሠርቼ ነገ አርፋለው በል

መልካም ቀን ይሁንልን
አልዓዛር ሱፋ
https://t.me/alazarsayehiwotmiker
https://t.me/alazarsayehiwotmiker
https://t.me/alazarsayehiwotmiker