Get Mystery Box with random crypto!

እወነተኛ እውቀት እውነተኛ እውቀት ማለት እውቀትን በኃሳብ ደረጃ በቃልም በተግባርም ማ | የሕይወት ምክር (PSYCHOLOGY)

እወነተኛ እውቀት


እውነተኛ እውቀት ማለት እውቀትን በኃሳብ ደረጃ በቃልም በተግባርም ማወቅ ነው ።

ይሕ ምን ማለት ነው ? የምታውቀው እውቀት በሦስቱም ደረጃዎች የማይረጋገጥ ከሆነ እመነኝ እውቀት ያለሕ ቢመስልህ እንኳን እውቀትሕ ምንም አይጠቅምም እንዴት....?


ስለ ሥራ ማወቅ እና ሥራን ማወቅ ይለያያል ስለ ሕክምና ማወቅ እና ሕክምናን ማወቅ የተለያዩ ነገሮች ናቸው ስለ መኪና ማወቅ ስለ ስልክ ወዘተ ማወቅ እውነተኛ ማወቅ አይደለም


ለምሳሌ እጃችን ላይ ስላለው ስልክ የምናውቅ ይመስለናል ግን እውቀታችን ተጠቃሚ እንጂ ሠሪ ስለማያደርገን እውቀታችን ቁንጽል ነው ማለት ነው ስለ ስልኩ ካሜራ እንጂ ሴቲንጉን አናውቀውም ሴቲንጉን እናወቀዎለን የሚሉ የስልክ ጠጋኞቻችን ሳይቀሩ ስልኩን መሥራት የሚያስችል እውቀት የላቸውም ግን ለምን?

እውነተኛ እውቀት ለግልም ለሀገርም እጅግ ጠቃሚ ነገር ነው ይሕ ሲኖረን ነው የፈጠራ ችሎታ የሚኖረን


ከዩኒቨርስቲ የሚወጡ ታዳጊዎች አብዛኞቹ የመቀጠር እንጂ ሥራ የመፍጠር እውቀት ይዘው ስለማይወጡ በየትኛውም መስክ የላቀ ወይም የፈጠራ ችሎታ አይገኝባቸውም


ደራሲና የስነ ምሕዳር ባለሙያ አለማየሁ ዎሴ አንድ ቀን ቃለ መጠይቅ ሲደረግለት እንዲሕ አለ ''ዩኒቨርስቲ ገብቼ የተማርኩት ትምሕርት አንድም ቀን ለሥራዬ አልጠቀመኝም '' ።

በርግጥም በዓለም ላይ ትልልቅ ተጽዕኖ ፈጣሪ የሆኑ ስኬታማ ሰዎች የቀለም ትምሕርቱን በአግባቡ የዘለቁ አይደሉም ነገር ግን ሁሉም ለኛ መምሕራኖቻችን ሁነው በመጽሐፋችን ታትመዎል ።
ለማያደርገን
ሞች አሉ ነገር ግን ሰው ለመታከም የሚፈልግባቸው ሃኪሞች በጣም ጥቂት ናቸው እነርሱም ከብዷቸው ለህክምና ወደ ውጪ የሚላኩት ታካሚዎች የትየለሌ ሆነዎል ሃኪም ጠፍቶ አይደለም አዎቂ ሀኪም ጠፍቶ እንጂ ስለ ሕክምናው የሚተማመንበት ሃኪም አጥቶ ነው ሕዝቡ የሚሰቃየው :

በሁሉም ዘርፍ ውስጥ smart and intelligent የሆኑ ሰዎችን ማግኘት ከባድ ነው አንድ ምርጥ አዎቂ ጥበበኛ ሰው ሲገኝ አቤት የሚሻማው መብዛቱ ይሕ የሁላችንም ትዝብት ይመስለኛል ።


ሀገር በቀል የሆኑ ትምሕርቶቻችንን መጣላችን ደግሞ ሁሌም የነጭ ተመራማሪዎች ባሪያ እንድንሆን ያስገድደናል


የእኛው አባቶች የሠሩትን የአክሱም እና ላሊበላ የድንጋይ ውቅር እኛ ለመጠገን እንኳን ሳይንሱ እውቀቱ ጠፍቶን ከጣለያን እና ከፈረንሳይ መጥተው መጠገናቸው የሚያሳየን እውቀት ምን እንደሆነ ነው ለኔ እውቀት በመማር ሳይሆን በምርምር የሚገኝ ነው እንድል ያደርገኛል ።


ለመንፈሳዊውም ሕይወት እንዲሁ ነው ስለ እግዚአብሔር ማወቅና እግዚአብሔርን ማወቅ በጣም የተለያዩ ነገሮች ናቸው እግዚአብሔርን የሚያውቁ ሰዎች በኃሳባቸው በቃላቸውና በሥራቸው እርሱን የሚመስሉት ናቸው ።


ለዚሕም ነው ቅዱስ ዩሐንስ አፈወርቅ '' የምታውቀውን መንፈሳዊ ሕግ በሥራ እስካልገለጥከው ድረስ አታውቀውም '' የሚለው


በቀን 7 የጸሎት ሰዓት አለ ብትል የጸሎት ጥቅም ምንነት ብትዘረዝር ነገር ግን ለ1 ሰከንድም ቢሆን ከልብ ካልጸለይክ ጸሎት ምን እንደሆነ አታውቅም ማለት ነው ።


ከተማርከውና ካነበብከው በላይ ጸሎት ስትጸልይ ብዙ ነገሮች ይገለጽልሃል ብዙ ምሥጢራትን ትረዳለህ ።

እንደኔ እንደኔ ምንም ነገር ከማድረግሕ በፊት ማወቅህ ልክ እና ጠቃሚ እንደሆነ እወቅ

ትክክለኛ የሆነ ለብዙ ሰው መትረፍ የሚችል እውቀት ባላቸው ሰዎች እቀናለው

አልዓዛር

ግንቦት 18/14