Get Mystery Box with random crypto!

ይህን የምታደርግ ከሆነ ከማንም ጋር መኖር ትችላለሕ | የሕይወት ምክር (PSYCHOLOGY)

ይህን የምታደርግ ከሆነ ከማንም ጋር መኖር ትችላለሕ


ወንድሜ የሰዎችን ፍላጎት መረዳት ያስፈልግሃል በአንድ ሀገር በተደረገ ጥናት ከ 500 የሥልክ ጥሪዎች ውስጥ 3990 ጊዜ የተጠቀሰ ቃል ቢኖር ''እኔ'' የሚለው ቃል ነው ሰው እኔ ሳይል ውሎ አያድርም ለዚህም ነው ሰዎች ፎቶ ሲያዩ በቅድሚያ የራሳቸውን ፎቶ በቅድሚያ የሚያዩት


ሰዎችን ባላቸው ነገር እንዳላቸው ጸጋ አክብረህ ስትይዛቸው እጃቸውን ከፍ አድርገው ሳይቀር ኪሳችን ውስጥ ግባ ይሉኃል ያምኑሃል ቅድሚያ ይሰጡሃል ''ንግግራችሁ በጨው የተቀመመ ይሁን…’’ የሚለው ቃልም የዚህን ጽንሰ ኃሳብ ይጋራል እኔነት በውስጥ ታምቆ ያለ መግነጢሳዊ እምቅ ኃይል ነው እሱን መነካካት ስትጀምር ወዳጆችህ ሁሉ በአንዴ ጠላት ይሆኑብሃል


ለሰው እኔነቱን ነጥቀህ አንተነትህን ልታሸክመው እንደምትፈልግ ካሰበ ጉረኛ ራስ ወዳድ አካባጅ …ወዘተ ብሎ ከጀርባህ የኃሜት በር ይከፍታል ከእድገትህ ውድቀትህን መመኘት ይጀምራል ስለዚህ አንተነትህን ከእሱነቱ ጋር አስማምተህ ሒድ
ብዙ ሰዎች ከሚያከብሯቸውና ከሚናፍቋቸው ሰዎች ፍቅር የሚይዛቸው በዚሁ ነው


ሰዎች የተፈጠሩበትን ትልቅነት በሌላ ሰዎች ፊት ጎልቶ ሲያዩት ደስታ ይፈጥርላቸዎል ለሰው የተፈጠረበትን ታላቅነቱን ከማየት በላይ ደግሞ ደስታ ሚፈጥርለት ነገር የለም ስለዚህ አንተም ይህን ተረድተህ እርሱነቱን ተቀበልለት አክብርለት ውደድለት

አልዓዛር መጋቢት 1/2014 ዓ.ም
https://t.me/alazarsayehiwotmiker
https://t.me/alazarsayehiwotmiker
https://t.me/alazarsayehiwotmiker