Get Mystery Box with random crypto!

ኃያሉ ኃሳብ | የሕይወት ምክር (PSYCHOLOGY)

ኃያሉ ኃሳብ
ሕይወታችን በውስጣችን በምናሳድጋቸው ኃሳቦች ይወሰናል፡፡ ኃሳባችን ሰላማዊ የተረጋጋ የዋህ እና ደግ ከሆኑ ሕይወታችንም ይህን ይመለከታል ፡፡ በአንጻሩ ትኩረታችን በሕይወታችን ውስጥ ስላሉ ሁኔታዎች ከሆነ ሰላም እና መረጋጋት ወደሚያሳጣ የኃሳብ አዙሪት ውስጥ እንገባለን ፡፡


ክፉም ደጉም ነገር ሁሉ የሚመጣው ከኃሳባችን ነው ምክንያቱም ኃሳቦቻችን እውነት ይሆናሉ እነዚህ ኃሳቦቻችን በሌሎች ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ አላቸው ፍጥረት ሁሉ የመለኮታዊ ኃሳብ በዓለም በጊዜ እና በቦታ የመገለጥ ውጤት ነው፡፡

እኛ የሰው ልጆች የተፈጠርነው በእግዚአብሔር አምሳል ነው ይህም እጅግ ታላቅ ስጦታ ሆኖ ሳለ አንረዳውም የእግዚአብሔር ኃይል እና ሕይወት በውስጣችን ቢኖርም አናስተውለውም ፡፡ እኛ እጅግ መልካም ወይም ክፉ ልንሆን እንችላለን ይህም የሚወሰነው በውስጣችን በምንዘራው ኃሳቦች እና ምኞቶች ነው ፡፡


ኃሳቦቻችን ሰላማዊ የተረጋጋ እና መልካም ወደሆነው ያዘነበሉ ሲሆን በእኛ ላይ በጎ ተጽዕኖ ይፈጥራሉ ይህ ደግሞ በዙሪያችን ባሉ ሰዎች በአገራችንም ጭምር ላይ ሰላምን ያንጸባርቃል ይህ በምድር ላይ ብቻ ሳይሆን በጠፈር ላይ የሚሠራ እውነታ ነው፡፡ እኛ በአምላካችን መስክ ስንሠማራ ስምምነትን እንፈጥራለን በሁሉም ቦታ ሰላም እና ጸጥታ ይሠራጫል፡፡

ነገር ግን በውስጣችን የምንዘራው መጥፎ ኃሳቦችን ከሆነና ውስጣችን በክፋት ከተሞላ በዙሪያችን ሁሉ የምናጸባርቀው ክፉውን ይሆናል፡፡ መጥፎ ኃሳቦች በውስጣችን ያለውን ሰላም እና ጸጥታ ያፈርሳል ፡፡ስለዚህም በጣም መልካም ወይም በጣም ክፉ መሆን የምንችል ከሆነ በእርግጥ መልካሙን መምረጥ የተሻለ ነው፡፡


ሁሌም ቢሆን ስህተታችን ከራሳችን አስቀድመን ሌሎችን መለወጥ መሞከራችን ነው ሁሉም ሰው እራሱን ለመቀየር ቢጀምር ሰላም በዙሪያችን ይሰፍናል ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዲህ ሲል አስተምሮ ነበር እራሱን የማይጎዳውን ሰው ማንም ሊጎዳው አይችልም ዲያቢሎስም ጭምር


ስለዚህ የወደፊት ሕይወታችንን የምንነድፈው አርክቴክቶች እኛ ብቻ ነን ሕይወታችንን የምንነድፈው አርክቴክቶች እራሳችን ብቻ ነን፡፡

የሰው ልጅ በኃሳቡ የሥነ ፍጥረትን ተፈጥሮአዊ አሠራር ያፈርሳል ለምሳሌ በኖህ ዘመን የነበሩ ሰዎች በጎርፍ ያለቁት በክፉ ኃሳባቸው እና ዓላማቸው ምክንያት ነው ዛሬም ቢሆን ይህ በእኛ ዘንድ እውነት ነው ኃሳባችን ክፉ ነው ስለዚህ መልካም ፍሬን አናፈራም ሁላችንም መለወጥ አለብን፡፡

አልዓዛር ሱፋ መጋቢት 2014ዓ.ም
https://t.me/alazarsayehiwotmiker