Get Mystery Box with random crypto!

አዎንታዊ የማሰብ ሒደት OSITIVE THINKING አዎንታዊ ኃሳብ ማለት የማትፈልገው | የሕይወት ምክር (PSYCHOLOGY)

አዎንታዊ የማሰብ ሒደት OSITIVE THINKING
አዎንታዊ ኃሳብ ማለት የማትፈልገውን ትተህ የምትፈልገውን ማሰብ ነው

ለምሳሌ ሁሌ ስለኪሳራህ የምታስብ ከሆነ ወደ አንተ የሚመጣው ያው ኪሳራ ነው የበለጠ ኪሳራ ትሰበስባለህ ስለ ኪሳራ በማሰብ ከኪሳራ አይወጣም ስለዚህ መሥራት ስለምትፈልገው ሥራ እና ማግኘት ስለምትፈልገው ትርፍ ብቻ አስብ

በፍቅር እንድትኖር ስለ ፍቅር ብቻ አስብ
ለምሳሌ ሰው ሁሉ ደግ እና መልካም ነው ብለህ በልብህ ላይ ከሳልክ ሁሌም ወደ አንተ የሚመጣው መልካም አሳቢ ሰው ነው ለፍቅርኛህ ወይም ለሚስትህ ሁሌም መልካም ሴት እንደሆነች መልካም ነገሯን በማሰብ አንቺ ለኔ በጣም ጥሩ ሰው ነሽ በላት ያኔ ፍቅራችሁ ይደራል

በጠዋት ከእንቅልፍህ ስትነሳ አመስግን የተሰጠህ ላይ የምታተኩር ከሆነ የበለጠ ይጨመርልሃል ላለው ይጨመርለታል ነው የሚለው ይህ ማለት ሁሌ ያለው አንደሆነ የሚሰማውና እንዳለው የሚያምን ነው ይህ የበለጠ ይጨመርለታል

ስለ ነገ ስታስብ በጣም ደስ የሚል ቀን እንደሚመጣ አስብ የመጨረሻው ዘመን ደረሰ እያልክ የመጨረሻው ዘመን ሰውን አትሁን አንተን ወደዚህ ምድር ያመጣህ ጽድቅ እያሠራህ ሕልምህን እንድታሳካ በውስጥህ ባለው ጸጋህ ራስህን እንድትመራ እንጂ ዘመኑን እንድትቆጥር አይደለም መጨረሻም ዘመን ላይ ሁን መጀመሪያ ዘመን ላንተ ሁለቱም ያው ነው ኃላፊነትህን ብቻ አስብ ዘመኑን ለዘመኑ ተወው

መልካም ቀን ይሁንላችሁ
አልዓዛር የካቲት/2014 ዓ.ም